Audit 45 Poessa2

Audit 45 Poessa2


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፋ/ ስ/ ፋ/ ስ/IFRS 001/2012

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀቱን በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS) በመለወጥ ተግባራዊ ለማድረግ የጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተዘረዘሩትን የቴክኒክ መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችን አወዳድሮ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች (IFRS) የአማካሪ አገልግሎት ግዥ በመፈጸም ስራው ሙሉ በሙሉ ተሰርቶ እስኪጠናቀቅ ማሰራት ይፈልጋል።

ስስዚህ፡- የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች በጨረታው እንዲሳተፉ እንጋብዛለን።

በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
በመንግስት ግዥ ላይ ለመሳተፍ በግዥ ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ማስረጃ /ክሊራንስ/ ማቅረብ የሚችል፣
ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100/ አንድ መቶ ብር በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተመሰከረ ቼክ /cpo/ ወይም የባንክ ዋስትና በኤጀንሲው ስም ማስያዝ አለባቸው።
.ተጫራቾች ሰነዳቸውን በሁለት ፖስታ ቴከኒካልናፋይናንሽያል ዋናውና ኮፒ ብለው ለየብቻው ማቅረብ አለባቸው።
ተጫራቾች ለሚጫረቱበት 60,000/ ስልሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ የተመሰከረ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና በኤጀንሲው ስም ማስያዝ አለባቸው።

ተጫራቾች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ጠዋት 2፡30-6፡30 ከሰዓት ከ7፡30-9፡00 ሰዓት ድረስ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የማወዳደሪያ ዋናውና ኮፒ ፖስታ በማለት ሰነዳቸውን ማስገባት ይችላሉ።

ጨረታው የሚከፈትበት በ11 ኛው ቀን በ4 ፡00 ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን በ4 ፡15 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
በጨረታው አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማያስሩ የጨረታ አሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ሲፒኦ አይመለስም።
ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% ሲፒኦ በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል የመፈራረም ግዴታ አለባቸው።

አድራሻ አራት ኪሎ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በስተጀርባ የቀድሞ ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ህንጻ ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 157 03 33 /01 156 44 14/011 155 03 66 በፋክስ ቁጥር 011 155 03 66

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ


Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 22 ቀን 2012

Deadline: June 8, 2020


© walia tender

Report Page