Audit 2

የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
አይናጌ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ደርጅት በኢፌዴሪ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ በመለያ ቁጥር 1544 በኢትዮጵያ ነዋሪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅትነት ተመዝግቦ በደቡብ ክልል በስልጤ ዞን የተለያዩ የልማት ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ግብረሰናይ ድርጅት ነው፡፡ ስለሆነም እኤአ ከሀምሌ 2019 እስከ ሰኔ 2020 ድረስ ያለውን የ ዓመት አጠቃላይ ገቢና ወጪውን እንዲሁም የፕሮግራም አፈጻጸም ጥራቱን በውጪ ኦዲተር ማስመርመር የሚፈልግ ሲሆን ይህንን ጨምሮ ከአሸናፊው የኦዲት ድርጅት ጋር ለተከታታይ 3 ዓመታት ውል ገብቶ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ከዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ የኦዲት ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ፤
የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
የዘመኑ ግብር ስለመከፈላቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
ከፌዴራል ወይም ከክልል ኦዲት መ/ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤
ከአሁን በፊት ባከናወናቸው የኦዲት ሥራዎች ከኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ የመልካም ሥራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
ሌሎች ድርጅቶች ስለመሥራታቸው የሚያሳይ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች መረጃውንና የምትሠሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቢሯችን ድረስ በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ወይም አዲስ አበባ ቦሌ መድሃኒአለም ጀርባ በሚገኘው አጋር ድርጅታችን ቻይልድ ፈንድ ኢትዮጵያ ማስገባት የምትችሉ መሆኑንእናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- _ የኦዲት ድርጅቱ ለሚልከው ባለሙያ ማንኛውንም የምግብ፣ የአልጋ፣ የትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ተመሳሳይ ወጪዎችን በራሱ ይሽፍናል፡፡
አድራሻ፡- ስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ ቅስት ከተማ ከቦዜ ት/ቤት ፊት ለፊት (ከአዲስ አበባ ሆሳእና በሚወስደው መንገድ ከቡታጅራ ከተማ 12 ኪሜ ርቀት ላይ) ስልክ ቁጥር፡- 0468820034/ 0468820140/0468820440
አይናጌ ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ደርጅት
በኢፌዴሪ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት
ኤጀንሲ
Posted: አዲስ ዘመን ሚያዝያ 11፥2012
Deadline: May 1, 2020
©walia tender