Attention

Attention


#ትኩረት_የሚሻ_የፀጥታ_ጉዳይ 


በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ እና በአፋር ተላላክ ወረዳ በአንድ ግለሰብ ሞት ምክንያት የተቀሰቀሰ ግጭት ወደ ተኩስ ልውውጥ ተቀይሮ ለሰዎች ሞት እና መቁሰል ምክንያት ሆኗል።


አሁን ያለው ሁኔታ እጅግ ልዩ ትኩረት የሚፈልግ ነው ተብሏል።


የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ ሰኢድ ኢብራሂም የተፈጠረው እንዲህ ሲሉ ያስረዳሉ ፦


" ችግሩ የተከሰተው ባለፈው ማክሰኞ ዕለት አንድ የአፋር ብሄረሰብ ተወላጅ እዚህ አርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ መዲና ከተማ ገበያ ነበር እዛ ገበያ ውሎ ሲመለስ መሃል መንገድ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገደለ።


ማን እንደገደለው አልታወቀም ከዚህ ከአርጎባ ብሄረሰብ የሀገር ሽማግሌዎችም የመንግስት አካላትም ወንጀል ስለተፈፀመ ይሄን አጣርተን ሰላም እንዳይደፈርስ ጥረት ማድረግ አለብን እያሉ ከአጎራባች አፋር ወረዳ ተላላክ ጋር ግንኙነት እያደረጉ ነበር በመሃል ሀሙስ ጥዋት ወደ አርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ መሬት የአፋር ታጣቂዎች በብዛት መጥተው በመስኖ ስራ እና በእንስሳት እርባታ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች ላይ ተኩስ ከፈቱ።


የፀጥታ ኃይሉ ይህን ለማረጋጋት ወደ ቦታው ሄደ ፣ በብዛት ስለነበር የመጡት ከዛ በኃላ ወዲያው ግጭት ተፈጥሯል። ትላንት እና ከትላንት ወዲያ ሙሉ ቀን ተኩስ ነበር ዛሬም ተኩስ አለ።


በትክካ ስልክ ስለማይሰራ ምን ያክል ጥፋት ምን ያክል ሞት ደረሰ የሚለው ባይታወቅም እስካሁን አንድ ሰው ሞቷል ትላንት ሁለት የቆሰሉ አሉ " 


መዲናን ጨንሮ በተለያዩ ቦታዎች ባለፉት ቀናት ተኩስ የሚሰማ ሲሆን ግጭቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከቄያቸው እየሸሹ መሆኑ ተገልጿል።


ከአፋር ክልል ተላላክ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ኃላፊ አሊ ከታይሳ ጉዳዩን እንዲህ ሲሉ ያስረዳሉ ፦


" ይሄ ነገር በሴራ የተደረገ ነገር ነው። ህብረተሰቡ የተዋለደና አብሮ ያደገ ነው። ከላይም ከታችም በሰላም በኩል ሞዴል የነበሩ ናቸው። እስከ ዛሬ የንብረት ስርቆት ቢፈፀም ፣ ሰው ቢደበደብ የፈለገ ነገር ቢሆን እስከ መጋደል ድረስ የደረሱ አልነበሩም።


ለገበያ የመጣውን ሰውዬ ተገደለ። ማን ገደለው የሚለውን ጥናት ላይ እያሉ ሰው የሞተባቸው ተኩስ ከፈቱና ሰው ሞተ። በአፋር በኩል ገበያ ሄዶ ከሞተው ሰው በተጨማሪ ትላንት አንድ ሰው ሞቷል። ለማስቆም ብዙ ጥረት አድርገናል ከማክሰኞ፣ እሮብ ጀምሮ ብዙ ጥረት ተደርጓል በአፋርም ከአማራም በኩል ፤ ግን ሊቆም አልቻለም።


ገበያ የሄደውን ሰው የገደለውን አካል ከአርጎባ በኩል ቶሎ ፈልጉ፣ ጥናት አድርጉና ያንን ያደረገውን አካል ያዙ ብለናል ፈጠን ብለው ያንን ሰው አስረው ቢሆን አፋር አይነቃነቅም ነበር። ያ ሰውዬ በሰዓቱ ቶሎ ተደርሶበት አልተያዘም። " 


አሁን በአካባቢው ያለው ችግር አፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት በአርጎባ ብሄረሰብ ወረዳ በኩል አለ።



የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ኃላፊ ሰኢድ ኢብራሂም ፦


" ጉዳዩ ከግለሰብም አልፎ ወደ ሌላ መልኩን ቀይሮ እጅግ አሰቃቂ የሆነና መጥፎ ጉዳት ሊያደርስ በሚችል ሁኔታ ላይ ነው ያለው። ከፍተኛ ተኩስ ነው ያለው ከዛም ከዚህም ኃይል እየተጨመረ ነው። በተለይ የክልሉ መንግስትም፤ የፌዴራል መንግስትም ይህን ጉዳይ መኃል ገብቶ ካላስቆመው ቀጠናው በጣም አስጊ ነው፤ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ግጭት ተፈጥሮ አያውቅም ሌሎች እንዳይጠቀሙበት ጥንቃቄ እና ትኩረት ያስፈልገዋል "

(ከቪኦኤ ሬድዮ የተወሰደ)

@tikvahethiopia

Report Page