Attention

Attention


#ትኩረት

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ ችግር ተባብሶ ከፍተኛ ውድመት እየደረሰ ይገኛል።

በትላንትናው ዕለት በዚሁ አካባቢ ስላለው ሁኔታ ቤተሰቦቻችን መልዕክት መላካቸው አይዘናጋም።

ዛሬ ደግሞ አጣዬና ጀውሀ እንዲሁም የኤፍራታና ግድም ወረዳ ቀበሌዎች በታጠቁ ኃይሎች ዝርፊያና ውድመት ቃጠሎ እየደረሰባቸው ሲሆን የሚመለከተው አካል ትኩረት እንዲሰጥ እየተጠየቀ ነው።

የሰሞኑን ሁኔታ በተመለከተ አል ዓይን ኒውስ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ ፤ የፀጥታ ችግሩ ከአራት ቀናት በፊት መከሰቱንና ተባብሶ መቀጠሉን አመልክቷል።

ነዋሪዎቹ ችግር የተፈጠረው ቅዳሜ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ/ም ምሳ ሰዓት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በጀውሀ ከተማ ለጸጥታ ስራ በተሰማራ የአማራ ልዩ ሀይል ላይ ጥቃት በመክፈታቸው ነበር ብለዋል።

በጥቃቱ የጀውሀ አስተዳዳሪን እና የአማራ ልዩ ሀይል አባላትን ጨምሮ በድምሩ የ30 ሰዎች ህይወት ማለፉን አመልክተዋል።

ሁኔታው እሁድ ዕለት ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም ትላንት በጀውሀ፣ ሰንበቴ፣ ሸዋሮቢት ከተማ እና ቀወት ወረዳ ስር ወዳሉ ቀበሌዎች መስፋፋቱ ተገልጿል።

ግጭቱን ለመቆጣጠር ተጨማሪ የአማራ ልዩ ኃይል ከአጣዬ አቅጣጫ ወደ ጀውሀ እና ሸዋሮቢት በመጓዝ ላይ እያለ ሰንበቴ ላይ ከመንገድ ዳር ባደፈጡ ታጣቂዎች ተኩስ እንደተከፈተባቸው ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።

ይሄንን ተከትሎ ግጭቱ ከጀውሀ አልፎ ወደ ሰንበቴ እና አጣዬ ሊስፋፋ መቻሉን ተገልጿል።

ዛሬ ሌሊትም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደ አካባቢው መግባቱን ተከትሎ ረፋድ ላይ ግጭቱ የረገበ ቢሆንም ከምሳ ሰዓት ጀምሮ ግን ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ እና ጦር መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ወደ አጣዬ ከተማ ገብተው ጥቃት መክፈታቸውን እና በዚህም ከፍተኛ ውድመት መድረሱን የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የሰሞኑን ግጭት መነሻ በተመለከተ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ያናጋገራቸው የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች ግጭት የተቀሰቀሰዉ አንድ ሰው እንዲፈተሸ ሲጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ በተተኮሰ ጥይት የአንድ ኦሮሞ ተወላጅ ነዋሪ ቤት ጉዳት ስለደረሰበት መሆኑን ገልፀዋል።

ትላንት የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሰንበቴ ከተማ በአሁኑ ጭንቅ ውስጥ መግባቷን ዱኣ ወይም ፀሎት እንደሚያስፈልጋትና የሚመለከተው የመንግስት ባለድርሻ አካላትን ልዩ ትኩረት እንደምትፋግ አሳውቆ ነበር።

ከሰሞኑን በዚህ ቀጠና በተከሰተው ግጭት ምክንያት ወደ ከአዲስ አበባ ደሴ እና ከሰሜን ኢትዮጵያ ከተሞች ወደ አዲስ አበባ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።

NB. እስካሁን የመንግስት አካላት በጉዳዩ ዙሪያ የሰጡት ዝርዝር ማብራሪያ የለም።

@tikvahethiopia

Report Page