Agri 4

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላፊነቱ የተወሰነ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአምራችና ከጅምላ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት1፡- የኤፍ ኤስ አር መኪና/ለ2ኛ ጊዜ/
ሎት2፡- ፈሳሸ የምግብ የሱፍ ዘይት /ለ2ኛ ጊዜ/
ሎት3፡- ልዩ ልዩ የጓሮ አትክልት ዘሮች/ለ3ኛ ጊዜ/
ሎት4፡- ልዩ ልዩ የእንሰሳት መድኃኒቶችና መገልገያ ቁሳቁሶች/ለ3ኛ ጊዜ/
ሎት5፡- ኤፍ ኤስ አር መኪና እና ፒካፕ መኪና ጎማ/ለ2ኛ ጊዜ/
ሎት6፡- የነቀዝ መከላከያ ከረጢት /ፒክስPICS/ /ለ2ኛ ጊዜ
ከላይ የተዘረዘሩትን የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦች በሀገር ውስጥ ገበያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አምራቾች እና የጅምላ አከፋፋዮች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
ከላይ በተዘረዘሩ የንግድ ዘርፍ/ዘርፎች/ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው።
በበጀት ዓመቱ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት /ቲን ነምበር/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የቫት ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚገዙትን ልዩ ልዩ እቃዎች ሸቀጦች/ዝርዝር መግለጫ የያዘ ጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት /ለሚሸጣቸው ሸቀጦች የማይመለስ ብር 50/ ሃምሳ ብር/ በመክፈል በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃሏየተ. ጽ/ቤት ማግኘት ይችላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ዋጋ 2% / ሲፒኦ/ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/ቢድ ቦንድ በሁለት ፈራሚ የተረጋገጠ በደ/ብርሃን እና ኢአ ባሉ ባንኮች በዩኒየኑ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዶክመንት ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በሁለት ፖስታዎች ተለያይቶ በአንድ ፖስታ ታሽጎ በደ/ ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ.የተ. ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጭምር እስከ 10 ኛው ቀን/ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8 ፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላየተ. ጽ/ቤት በ10 ኛው ቀን / የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን 8 ፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ከዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደ/ብርሃን ከተማ በጠባሴ አካባቢ ከመልዕክት አካዳሚ ጐን ከመኪና ማሰልጠኛው ፊት ለፊት በሚገኘው የወደራ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ.የተ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0116814115 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የወደራ ሁስገብ
የገበሬዎች ህ/ ስ/ ማህበራት ዩኒየን ኃላ/ የተ ደ/ ብርሃን
_______________________________
Category : Agriculture, Agricultural Raw Material and Supplies, Food and Beverage, Food Items Supply, Medical Equipment and Supplies, Veterinary Drugs and Equipment, Purchase., Vehicle and Spare Parts, Vehicle Purchase, Tyre and Battery
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 10 ቀን 2012
Deadline :2020-03-28