Agri 3

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የየም ልዩ ወረዳ እ/ዓ/ ሀብት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ማስተከል ይፈልጋል::
የጨረታው መለያ ቁጥር 001/2012

ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የሥራ ፈቃድና የዘመኑን የሥራ ግብር አጠናቀው የከፈሉበት ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የንግድ መለያ ቁጥር /Tin number/ ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ከአሁን በፊት የምጥን መኖ ማሽን በመገጣጠም በቂ ልምድ ያለው እንዲሁም ማሽኑን ቦታው ድረስ ገጣጥሞ ማስረከብ የሚችል። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ/ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ተከታታይ ለ15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የ ማይመለስ ለእያንዳንዱ 100.00 ብር / አንድ መ ቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው ፋይናሽያልና ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በመጨረሻው ቀን እስከ 4 ሰዓት ድረስ የምልዩ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል።
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15 ኛው ቀን 4 ፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4 ፡30 ሰዓት በፋ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት ውስጥ ይከፈታል::
ጽ/ቤቱ የተሻለ ሁኔታ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አሸናፊው ከተረጋገጠ በኋላ ወዲያወኑ ሌሎች ያስያዙት የጨረታ ማሰከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ይመለሳል።
ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ከቫት ውጭና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ለይቶ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
የዘገየ ጨረታና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም::
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብና ዋጋ ላይ ስምና ፊርማቸውን፣ ቀንና የድርጅቱ ማህተም ማሳረፍ ይኖርባቸዋል፡፡
አሸናፊው ተጫራችሙሉ በሙሉ በውሉ መሠረት ማጠናቀቃቸው ከተረጋገጠ በኋላ ሙሉ ክፍያ ይከፈላቸዋል፡፡
የጨረታ መክፈቻው በበዓላትና በእረፍት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን ላይ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስተጓጉለውም፡፡
በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
ተጫራቾች የሥራ ፈቃዳቸው ያልተሟላ መረጃና የዋጋ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም፡፡
ለጨረታ ከቀረቡ ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% መጨመር/ቀንሶ/ መግዛት መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተደራጁ አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት ተሻሽሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 98/2004 በደንቡ መሠረት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
ጨረታውን ያሸነፈ አቅራቢ/አካል/ እስከ የም ልዩ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሣጃ ድረስ ዕቃውን ማቅረብ ይኖርበታል::
የመወዳደሪያ ቋንቋ በአማርኛ ሲሆን የሚፈልገውን ዝርዝር ዕቃ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ የሚችል።
የየም ልዩ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ሣጃ ከተማ ሲሆን ከአ/አ 240 ኪሜ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ ላይ እንገኛለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0474518006 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ደ/ ብ/ ብ/ ሕ/ ክ/ መ/ የየም
ልዩ ወረዳ እ/ ዓ/ ሀብት ጽ/ ቤት
_______________________________
Category : Agriculture, Agricultural Machinery, Purchase.
Posted Date : አዲስ ዘመን መጋቢት 10 ቀን 2012
Deadline :2020-04-02