Afar Tigray

Afar Tigray


" በአፋር በኩል ጦርነቱ አልቆመም "

የአፋር ክልል መንግስት ህወሓት በሰላም ወዳዱ የአፋር ህዝብ ላይ በድጋሚ እያካሄደ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ማቆም አለበት ሲል አስጠንቅቋል።

ክልሉ ፥ " አሸባሪው ህወሓት በኪልበቲ ረሱ /ዞን ሁለት/ በአብአላ በኩል ከታህሳስ 10/2014 ጀምሮ በከፈተው አዲስ ግንባር በተከታታይ እየተኮሰ ባለው ከባድ መሳሪያ ንፁሀን ዜጎችን መጨፍጨፉን ቀጥሏል " ብሏል።

አክሎ ፥ " አሸባሪው ህወሀት ካሁን በፊት በከፈታቸው ግንባሮች በምድር ድሮኖቹ ሽንፈት ገጥሞት ቢወጣም ቡድኑ በኪልበቲ ረሱ አብአላ እና መጋሌ በኩል በከባድ መሳሪያ የታገዘ ድብደባ በንፁሃን ላይ በመፈፀም በርካቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገለዋል፣ ቆስለዋል፣ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ በጥቃቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለስደት ተዳርገዋል " ብሏል።

የአፋር ክልል፥ " የትግራይን ህዝብ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር ለማናከስ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪው ህወሀት በትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆነው በዚሁ አካባቢ የትግራይን ህዝብ ከጎረቤቱ ጋር በማናከስ፣ ጉርብትና እንዲሻክር እና ጎረቤቶችን በማጣላት የራሳቸውን እድሜ ለማራዘም አፋር እና ትግራይ ጎረቤት ህዝቦችን እያናከሰ ይገኛል " ሲል አሳውቋል።

"ጎረቤታሞች በሰላም ውሎ እንዳያድር ትልቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነው" የሚለው የአፋር ክልል " የትግራይ ህዝብም ይሄንን የጀንታውን እብደት ሊቃወም ይገባል፤ በቃቹህ ሊሉ ይገባል። " ሲል አስገንዝቧል። ቡድኑ በንፁሀን የአፋር ህዝብ ላይ በተለይም በኪልበቲ ረሲ ዞን አብአላ እና መጋሌ በኩል የከፈተውን በጥብቅ ሊያወግዝ ይባልም ብሏል።

ህወሓት በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት በተለየ መልኩ ተደራጅቶ በመምጣት ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ በርካታ ንፁሀን ላይ ጉዳት አድርሷል፣ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እና የግለሰብ የንግድ ተቋማት እና መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል ሲል የአፋር ክልል አሳውቋል።

ክልሉ ፥ " አሸባሪው ህወሀት ካሁን በፊት ጦርነት በከፈተባቸው የአፋር አካባቢዎች በጣም በተደራጀ ሁኔታ ተደጋጋሚ እና ፋታ የማይሰጥ ጥቃት በመክፈት ወደ ፊት ገፍቶ ለመሄድ የሞት ሽረት ትግሉን እያደረገ ይገኛል " ሲል ገልጿል።

" ህወሓት በከባድ መሳሪያ ንፁሀንን የመግደል የመጨፍጨፍ ተግባሩን አሁንም አላቆመም፣ በአፋር በኩል ጦርነቱ አልቆመም፣ ንፁሀን ሴት፣ ህፃናት እና አዛውንት አሁንም ሰለባ እየሆኑ ነው" ብሏል የአፋር ክልል።

ክልሉ የዓለም ህብረተሰብ የህወሓትን ድርጊት እንዲያወግዝ ጥሪ አቅርቧል።

ህወሓት በሚቆጣጠረው የትግራይ ቴሌቪዥን በኩል ባወጣው መግለጫ የአፋር ልዩ ኃይል በህዝባችን ላይ ተከታታይ ግፎችና ጭፍጨፋዎች እየፈፀመ ሰንብቷል፤ ትላንት ጥር 7 በምላዛትና በዳንደ ጥቃት ፈፅሟል፤ ሲል ክስ አሰምቷል። ነገር ግን ወስጀዋለሁ ባለው የመከላከል እርምጃ መበታተኑን ትንኮሳው ስላልቆመ ግን የአፋር የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የሀይማኖት ጎሳ መሪዎች ከድርጊቱ እንዲቆጠብ እንዲያደርጉ ሲል አሳስቧል።

@tikvahethiopia


Report Page