Addis Ababa Police

Addis Ababa Police


የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ በትራፊክ መብራቶች እና በመስቀለኛ መንገዶች ላይ የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ንግድ እና የልመና ተግባራት ላይ በተሰማሩ ግለሰቦችና #ገንዘብ_በሚሰጡና በሚገበያዩ አሽከርካሪዎች ላይ በህጉ መሰረት ጠንካራ እርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠነቀቀ።


በልመና ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ የሚሰጡ እና ግብይት የሚፈፅሙ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቋል።


በሚኒስትሮች ም/ቤት የወጣው የትራንስፖርት መቆጣጠሪያ ደንብ ቁጥር 395/2009 #በትራፊክ_መብራት ላይ ወይም #በመስቀለኛ_መንገድ ላይ በልመና ተግባር ለተሰማሩ ሰዎች ገንዘብ የሰጠ ወይም ግብይት የፈፀመ አሽከርካሪ ቅጣት እንደሚጣልበት ይደነግጋል፡፡


" ይህን እንጂ #የአሽከርካሪዎች ደንብ አክባሪ አለመሆን በእነዚህ መንገዶች ላይ የሚከናወኑ ህገ-ወጥ ንግድና የልመና ተግባራት እንዲስፋፉ ምክንያት ሆኗል " ሲል ፖሊስ ገልጿል።


የትራፊክ ደንቡ አለመከበር #ለትራፊክ_አደጋ መጨመር እና ጤናማ የትራፊክ ፍሰት እንዳይኖር እንቅፋት ከመፍጠሩ ባሻገር በተለይ የትራፊክ መብራቶች ባሉባቸው ጎዳናዎች የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች የሚፈፀምባቸው ቦታዎች እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ አስረድቷል።


ትራፊክ ፖሊሶች በቁጥጥርና በማስተናበር ስራ ላይ በሚያተኩሩበት ወቅት በትራፊክ መብራት እና በመስቀለኛ መንገድ ላይ በልመና እና በህገ ወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎች መሃል መንገድ ድረስ በመግባት ለትራፊክ ፍሰቱ እንቅፋት እየሆኑ እና ራሳቸውን ለአደጋ እያጋለጡ እንደሚገኙ የገለፀው ፖሊስ " እስካሁን ባለው ሁኔታ ለእነዚህ ሰዎች ገንዘብ በሚሰጡ እና ግብይት በሚፈፅሙ አሽከርካሪዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር እና የሚወሰደው እርምጃ አጥጋቢ ነው ባይባልም የችግሩን መስፋትና መልኩን መቀየሩን ተከትሎ በቀጣይ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል " ብሏል።

ስለሆነም ህብረተሰቡ በተለይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ መብራት ላይ የሚደረግ ልመና እና ህገ ወጥ ንግድ ለአደጋ አጋላጭ መሆኑን ተገንዘበው ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ እና ባለድርሻ አካለትም በትራፊክ መብራት አካባቢ የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ ተግባራትን ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ህጋዊ ኃላፊነታቸው እንዲወጡ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

@tikvahethiopia

Report Page