Acc 6

ህዳሴ ቴሌኮም አ . ማ
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር LT/ET/HO/03/2020
1. ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የውጪ ኦዲተር አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 - 6፡00 እንዲህም ከሰዓት በኃላ ከ7፡30 - 10፡00 ድረስ “ህዳሴ ቴሌኮም አ.ማ” ደብረዘይት መንገድ ጠብመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት ከበእምነት ምግብ ቤት ጎን በሚገኘው ቤተሳይዳ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድመቶ/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት
አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም የታሸገ መሆን አለበት፡፡
በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም:: የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የውጪ ኦዲተር አገልግሎት የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 / አስር ሺ ብር / የባንክ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ ለሕዳሴ ቴሌኮም ኢማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓም እስከ ከጠዋቱ በ4 ፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 306 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ. ም ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 306 ይሆናል::
6 ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0114-653711 ፋክስ ቁጥር 0114-663649 መጠቀም ይችላሉ።
8. ህዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር
_______________________________
Category : Accounting and Auditing, Auditing Related, Purchase.
Posted Date : ሪፖርተር እሁድ መጋቢት 6 ቀን 2012
Deadline :2020-04-07
back to Accounting and Auditing
back to home