Acc 12

የቫት ደረሰኝ ምርመራ በዝርዝር ምዝገባ ኦዲት ማድረግ /
የአገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ከጥቅምት 01/2011 ዓ/ም እስከ ጥር 30/2012ዓ/ም ድረስ ያለውን የቫት ደረሰኝ በዝርዝር ምዝገባ ተደርጎ ምርመራ/ኦዲት ማድረግ/የአገልግሎት ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ በአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው አስፓልት 500 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ከቀኑ 8.00 ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 15 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8.00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8 ፡30 ባህርዳር በሚገኘው በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል ፡፡
3. በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ መሟላት ያለበት ፡-
3.1 በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድና ለዘመኑ ስለመታደሱ ማረጋገጫ እና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
3.2 ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ገቢ ግብር ለመክፈላችሁ ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣት ማረጋገጫ፣
3.3 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን/እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት/ቫት/
3.4 የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን የሚያዘው ማስከበሪያ ከብር 500 ሺህ መብለጥ የለበትም፡፡
4. የጨረታ አሸናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ከ ሶስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት ሰባት የስራ ቀናት ውስጥ ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 በመቶ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና /ፐርፎርማንስ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡ከላይ በተገለጸው ቀን ውል ያልፈጸመ እንደሆነ ግዥ ፈፃሚው አካል የጨረታ ማስከበሪያ የመውረስ መብትይኖረዋል፡፡
5. አሸናፊ ከተለየ በኋላ በአሸናፊነት ያልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸናፊው ጋር ውል ከተያዘ በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
6. ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት የስራውን ትክክለኛነት እና የጥራት ደረጃ በድርጅቱ ባለሙያዎች በማረጋገጥ ትክክለኛነቱን ሲያሟላ ብቻ ሊረከብ ይችላል፡፡
7. በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡
8. የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
9. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
10. በጨረታ ሠነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ፊርማና ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
11. ድርጅቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው አቅራቢ የጨረታውን ይዘት ሳይቀይር ከግዥ አገልግሎቱ ጠቅላላ መጠን ላይ 50 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
12. ሻጭ ስራውን አስረክቦ ሲጨርስ የሚጠይቀውን ክፍያ በባንክ እንዲላክለት ከፈለገ የባንክ መላኪያው ከሚላከው ገንዘብ ላይ ይቀነሳል፡፡
13. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
14. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡በመሆኑም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ ድርጅቱ ሀላፊነት አይወስድም
15. ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል ቢሮ ቁጥር 18 በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር በመደወል 058-218-09-58 ወይም ፋክስ ቁጥር፡-058-218-07-11/542 በመላክ ይችላሉ፡፡
የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
_______________________________
Category : Accounting and Auditing, Auditing Related, Consultancy., Financial Consultancy
Posted Date : በኩር ሰኞ መጋቢት 14 ቀን 2012
Deadline :2020-04-06