AP

AP


#ምዕራብ_ወለጋ


አሶሼትድ ፕሬስ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ ይዞት በወጣው ዘገባ በትላንቱ ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለዋል።


ከጥቃቱ ያመለጠው የጊምቢ ወረዳ ነዋሪ አብዱል ሰኢድ ጣሂር ለአሶሼትድ ፕሬስ በሰጠው ቃል ፥ " 230 አስከሬኖችን ቆጥሪያለሁ። ይህ በህይወታችን ያየነው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ነው ብዬ እሰጋለሁ " ብሏል።


አክሎም " ሟቾችን የጅምላ መቃብር ውስጥ እየቀበርናቸው ነው፣ አሁንም አስከሬን እየሰበሰብን ነው። የፌደራል ሰራዊት ደርሰዋል ነገር ግን ከቦታው የሚለቁ ከሆነ ሌላ ጥቃት ሊደርስ ይችላሉ ብለን እንሰጋለን " ሲል አስረድቷል።


ሻምበል የተባሉ ሌላ የአይን እማኝ ለደህንነታቸው ሲሉ የመጀመሪያ ስማቸውን ብቻ የገለፁ " በአካባቢው ያለው የአማራ ማህበረሰብ " ሌላ ዙር የጅምላ ግድያ ከመከሰቱ በፊት ወደ ሌላ ቦታ እንዲወሰድ ይፈልጋል " ብሏል። " 


ነዋሪዎቹ የዛሬ 30 አመት አካባቢ በሰፈራ ፕሮግራም የሰፈሩ መሆናቸውን ገልጾ " እንደ ዶሮ ነው የተገደሉት " ሲል የጥቃቱ አስከፊት ገልጿል።


ሁለቱም የአይን እማኞች ጥቃቱን መንግስት በሽብርተኛ ድርጅትነት የፈረጀውን " ሸኔ " እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ የሚጠራውን የታጠቀ ኃይል እንደፈፀመው ገልፀዋል።


የኦሮሚያ ክልል መንግስትም ትላንት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን " ሸኔ " የፌዴራል የጸጥታ ሃይሎች የጀመሩትን ዘመቻ መቋቋም ባለመቻላቸው ነው " ንፁሃንን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ መግደሉን መግለፁ ይታወሳል።


የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጥቃቱን አልፈፀምኩም ሲል አስተባብሏል።


የታጣቂ ኃይሉ ቃል አቀባይ ነው የተባለው ኦዳ ተርቢ ፥ " ጥቃቱ የተፈጸመው የአገዛዙ ወታደሮች እና የአካባቢ ሚሊሻዎች በቅርቡ ያደረግነውን ጥቃት ተከትሎ ጊምቢ ከሚገኘው ካምፓቸው ሲያፈገፍጉ ነው " ብሏል።


" ቶሌ ወደሚባል አካባቢ አምልጠው በአከባቢው ህዝብ ላይ ጥቃት ፈጽመው ንብረታቸውን አውድመዋል ፤ ለOLA ድጋፍ በመስጠታቸው ለመበቀል ነው " ሲል አክሏል።


" ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት የእኛ ተዋጊዎቻችን ወደዚያ አካባቢ እንኳን አልደረሱም " ሲል የታጣቂ ቡድኑ ቃል አቀባይ ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግሯል።


@tikvahethiopia

Report Page