የእጩነት ጥሪ - A Call for Nomination!

የእጩነት ጥሪ - A Call for Nomination!

Click here to get application Link.

የእጩነት ጥሪ ለፕሬዝዳንትነት

ዘ-ኢንስፓየር ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሴሽን በኢትዮጵያ ውስጥ በወጣቶች የስብዕና ልማት ስራዎችን ለመስራት በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በቀን 05/11/2011 ዓም በመዝገብ ቁጥር 2813 ዳግም ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት ተሰጥቶታል። ላለፉት በርካታ ዓመታትም ሰፋፊ ወጣት ተኮር የበጎ ፈቃድ የልማት ስራዎችንም ሲሰራ ቆይቷል። 

ማህበራችን በስሩ በርካታ ፕሮግራሞች የሚመራ ቢሆንም አንዱ እና ዋነኛው የሆነው የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ (Youth Network Ethiopia) ኢኒሼቲቭ/የቴሌግራም ግሩፕ ነው። ይህ መረብ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን እና ወጣቶችን በማስተሳሰር ለአዎንታዊ ልማት የሚጠቅሙ ትምህረቶችን ፥ ስልጠናዎችን ፥ የልምድ ልውውጦችን ፥ የሰላም ውይይቶችን ፥ የማማከር አገልግሎቶችን በማዘጋጀት ላለፉት ሁለት ዓመታት ያለማቋረጥ በቀን ለሶስት ሰዓታት ያህል የበይነ መረብ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን (Digital Voluntarism) ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም በርካታ ወጣቶች ጠቃሚ ስልጠናዎች ፥ የበይነ መረብ ወዳጅነት ፥ የምክር አገልግሎት አግኝተዋል። ከዚህ በተጨማሪ የትስስር መረቡ በተለያዩ የአለማችን ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያዊ እንደራሴዎች ፥ ወጣቶች ካሉበት ቦታ ሆነው ለሀገራቸው የበጎ ፈቃድ ስራዎችን መስራት አንዲችሉ  አመቻችቷል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች የተነቃቁ ወጣት በጎ ፈቃደኞችን በአምባሳደርነት በመሾም በየዩኒቨርስቲያቸው የትስስር መረባችንን ዓላማ በአካል / ፊት ለፊት ወጣቶችን በመበሰብሰብ ስልጠናዎችን እንዲያሰባጥሩ በማድረግ ሰፊ ስራ ተሰርቷል። ይህ ከአርባ ሺህ በላይ አባላትን በስሩ ይዞ ዘወትር የስልጠና ስራዎችን ለሚሰራው የትስስር መረብ ፕሬዚደንት ሆኖ/ና የሚመራ/ የምትመራ ሀላፊ በማስፈለጉ ጥቆማ እንድታደርጉ እናሳስባለን::

ውድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ አባላት ለትስስር መረባችን የተሻለ የወደፊት ጉዞ ለማድረግ በመጣር ላይ የምንገኝ  ሲሆን በትስስር መረባችን ግንባር ቀደም ፥ ጠንካራ እና ብቃት ያለው አመራር እንዲኖረን አስፈላጊ መሆኑን ለመረዳት ችለናል። ስለሆነም የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ ፕሬዝዳንትነት ዕጩነት ጥሪውን በይፋ በመክፈታችን ደስ እያለን በመላው ኢትዮጵያ የወጣቶቻችንን ፍላጎት እና ጥቅም እውን ለማድረግ ስራዎቻችንን በልህቀት ለመምራት  ቁርጠኛ የሆነ ባለራዕይ መሪም በመፈለግ ላይ ነን። እጩ ተወዳዳሪው የተረጋገጠ የአመራር ልምድ ፣ ጠንካራ የተግባቦት ክህሎት እና የኢትዮጵያን ወጣቶች የሚገጥማቸውን ተግዳሮቶች በጥልቀት የተረዳ መሆን ይኖርበታል። እና እርስዎ ወይም እርስዎ የሚያውቁት ሰው እነዚህ ባህሪያት ያለው/ት እና በኢትዮጵያውያን ወጣት ህይወት ላይ አወንታዊ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ፍላጎት ካሎት እድሉን እንዲጠቀሙ በአክብሮት እንጋብዛለን!

ማስታወሻ

  •  የትስስር መረቡ እጩ ፕሬዚደንት ለመሆን ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ አባል መሆን ይጠበቅበታል!
  •  ቢያንስ ለስድት ወር በትስስር መረቡ ተሰዋትፊ የነበረ መሆን ይገባዋል
  •  የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያለው /ያላት
  •  ከዚህ ቀደም በአመራርነት ልምድ ያለው / ያላት
  •  በበጎ ፈቃድ ተግባር የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
  •  በትስስር መረቡ በበጎ ፈቃደኝነት ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/ች
  •  ከየትኛውም የእምነትም ቢሆን የብሔር መድሎ የራቀ/ች
  •  እድሜ 22-35 ድረስ
  •  የመግባባት ክህሎት ያለው / ያላት
  •  የትስስር መረቡን ዓላማ የሚያውቅ / የምታውቅ 

ተጠሪነት

  • የኢትዮጵያ ወጣቶች ትስስር መረብ የኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሴሽን ፕሮግራም እንደመሆኑ ፕሬዚደንቱ በቀጥታ ለማህበሩ ዳይሬክተር ተጠሪ ይሆናል!

ተግባር 

  •  ተግባር የማቀድ የማሰራት እና ሪፖርት የማድረግ ሀላፊነት
  •  የትስስር መረቡን ደንብና መመሪያ ለመማር እና በደንቡ መሰረት ለመምራት ዝግጁ መሆን ይኖርበታል
  •  የትስስር መረቡን በመወከል ከየትኛውም መንግስታዊ እንዲሆም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ጋር አጋርነት መፍጠር መቻል
  •  የትስስር መረቡን ስራ ማላቅ / ከፍ ማድረግ
  •  የአባለት ቁጥር መጨመር ላይ መስራት
  •  አዳዲስ እሳቤዎችን መዘርጋት ለበላይ ዓመራሮች በማሳወቅ  ወደስራ ማስገባት
  •  በሁሉም ዩኒቨርስቲ የሚገኙትን አባላቶቻችንን ማሳተፍ ለተጠቃሚነታቸው መስራገት
  •  ለትስስር መረቡ እድገት በተለይም የቁጥር መጨመር ላይ ስልት መንደፍ
  •  የተለያዩ ለትስስር መረባችን አስፈላጊ የሆኑ ስልጠናዎችንን ማመቻቸት ከትስስር መረቡ ዓመራሮች ጋር የመቆራኘት ዝግጁነት አብሮ የመስራት ልማድ ማዳበር ይጠበቃል
  •  ለማህበሩ አቻ ተጠሪ ከሆኑ አመራሮች ለምሳሌ የአምባሳደሮች መሪ - Head of Ambassadors ጋር በአብሮነት የመስራት መቻል::

Dear members of Youth Network Ethiopia, as we strive towards a better future for our group, it is vital that we have strong and capable leadership at the forefront of our Network. In light of this, we are thrilled to officially open the call for nominations for the position of President of the Youth Network Ethiopia. We are seeking a visionary leader who is committed to advancing the rights and interests of young people across Ethiopia. The ideal candidate must have a proven track record of leadership, strong communication skills, and a deep understanding of the challenges facing the youth of Ethiopia. And should be member of youth network Ethiopia at list for six month If you or someone you know possesses these qualities and is passionate about making a positive difference in the lives of young Ethiopians, please consider submitting a nomination. Nominations can be submitted to the electoral commission by April 29/2023 and must include a completed nomination form, a detailed resume, and a personal statement outlining your vision for the future of Youth Network Ethiopia. We look forward to receiving your nominations and working together to build a brighter future for all young Ethiopians.


Sincerely,

Liyuneh Tamirat

Executive Director

The Inspired Ethiopian Youth Association


Report Page