#200M
ኢትዮጵያ ክብረወሰን ሰበረች!
በአለም አቀፍ ደረጃ በህንድ ተይዞ የነበረው 66 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል ክብረ ወሰን ዛሬ ኢትዮጵያ ከ234ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በሰፊ ቁጥር መስበሯ ይፋ ሆኗል።
ቢቢሲ በድረገጹ እንዳስነበበው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ በአገር አቀፍ ደረጃ በርሃማነትን ለመቀነስ ያለመ አካሄድ መሆኑን ገልጾ፤ 1 መቶ ሚሊዮን ህዝብ በነፍስ ወከፍ ቢያንሰ ሁለት ይተክላል በሚል የታሳቢ ቢሆንም ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ስራቸውን እዚያው በማድረግ እየተከሉ መሆናቸውን ጠቅሷል።
ለዚህም በተባበሩት መንግስታት አየር ንብረት ትንቢያ በሚሊኒየም መባቻ የአገሪቷ አየር ንብረት 35 በመቶ ማሽቆልቆሉን ገልጾ፤ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ከ4 በመቶ በላይ ማገገም ያሳየ እንደሆነ በመረጃው ተጠቅሷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በዛሬው ዕለት በአገሪቱ ከ1ሺ በላይ ጣቢያዎችን በማስጀመር የችግኝ ተከላው ከጠዋቱ 12 ሰዓት መጀመሩና በአንድ ማዕከል የቆጠራ ሂደት መደረጉ ለዕቅዱ መሳካት የራሱ የጎላ ድረሻ እንዳለውም በመረጃው ሰፍሯል።
ይህ በሳይንሰና ኢኖቬሽ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አስተባባሪነት የሚከናወነው ቆጠራውን ይፋ የማድረግ አሰራር የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃንም በትብብር መንፈስ መስራት በመቻላቸው አስፈላጊ ምስሎችና ቪዲዮዎች እንዳያመልጡ መደረጋቸውን ለህዝቡ መነሳሳትን እንደፈጠረም ተገልጿል።
እኤአ በ2016 በህንድ አገር በ8 መቶ ሺህ በጎ ፈቃደኛ የተደረገው የችግኝ ተከላ ከ50ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል በአለም አቀፍ ደረጃ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በሰፊው ከማሻሻሉም በላይ የተሳተፈው የሰው ቁጥር በአገር አቀፍ ደረጃ መሆኑ ለየት ያደርገዋል ሲል መረጃው ያትታል።
በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ቀን በአገሪቷ በሰሞኑ አንዳንድ አካባቢ ተከስቶ የነበረውን ችግር በማስረሳት ወደ አንድ እንዲመጣ ከማረጉም በላይ አሁን እየታየ ያለውን አላስፈላጊ ግጭትና ጥላቻን የማስቀረት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ታምኖበታል ሲል ነው ቢቢሲ የዘገበው።
Via #ENA