ፀጋው ነው (Tsegaw New) - በረከት ተስፋዬ

ፀጋው ነው (Tsegaw New) - በረከት ተስፋዬ

Bereket Tesfaye‎ | Liqe Kahenie


አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ

ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x)


ሁልጊዜ ፡ ችኩል ፡ ነው ፡ ሲያዩት ፡ ደፋር ፡ መሳይ

ዶሮ ፡ ሳይጮህ ፡ በፊት ፡ ሶስት ፡ ጊዜ ፡ ክህዶታል

በሰው ፡ አይን ፡ ቢሆን ፡ ይህ ፡ ሰው ፡ ከሀዲ ፡ ነው

የፀጋው ፡ ጉልበት ፡ ግን ፡ ዳግም ፡ ሰው ፡ አረገው


አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ

ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x)


ቢሆንማ ፡ ኑሮ ፡ በክብር ፡ በዝና

በገንዘብም ፡ ብዛት ፡ ብዙ ፡ ብልጥግና

እንዴት ፡ እሆን ፡ ነበር ፡ እርቆኝ ፡ መዳኔ

ግን ፡ እንዲያው ፡ ወደደኝ ፡ አሰበኝ ፡ መድህኔ

እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው

የተረሳውን ፡ ሰው ፡ እንዲህ ፡ ሚያስታውሰው


አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ

ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x)


በማይመስል ፡ ነገር ፡ መስራት ፡ የሚችል

የአለምንም ፡ ጥበብ ፡ በኔ ፡ ሚያሳፍር

ልጁንም ፡ ገለጠው ፡ በእኔው ፡ ሁኔታ

እኔን ፡ ውዳቂውን ፡ አከበረ ፡ ጌታ


አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ

ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x)


በራሴ ፡ አልቆምኩም ፡ ሚስጥሩ ፡ ገብቶኛል

ጸጋን ፡ አትረፍርፎ ፡ እየሱስ ፡ ሰጥቶኛል

ከቶ ፡ ዝም ፡ አልልም ፡ አዜምለታለሁ

ላከበረኝ ፡ ጌታ ፡ ክብር ፡ እሰጣለሁ

እንደ ፡ ሰው ፡ አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ ልዩ ፡ ነው

የተረሳውን ፡ ሰው ፡ እንዲህ ፡ ሚያስታውሰው


አዝ:- ፀጋው ፡ ነው ፡ እኔን ፡ የሚያቆመኝ

ምህረቱ ፡ ነው ፡ እንዲህ ፡ የሚያዘምረኝ (፪x)

Report Page