ጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በሽታ (neonatal jaundice)

ጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በሽታ (neonatal jaundice)

✍️ ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም

Doctors Online

___


ልጄ ከተወለደ 6 ቀኑ ነው። የልጄ አይኑ እና ቆዳው ቢጫ ሆኗል ፤ እጅግ አሳስቦኛል። የሰፈር እናቶች የአሞራ በሽታ ነው አሉኝ አትጨነቂ ጎበዝ የባህል ሀኪም አሉ ሆድ ላይ በሚታሰር ነው የሚታከመው በዘመናዊው ህክምና አይታከምም አሉኝ አለችኝ። ለቤተሰብ ግንዛቤ ያክል ካነበብኩት ትንሽ ጀባ ልበላችሁ።


ስለ ጨቅላ ህፃናት ቢጫ መሆን በሽታ (neonatal jaundice) ቤተሰብ ሊያውቁት የሚገቡ ነገሮች ምንድናቸው?


የጨቅላ ህፃን ቢጫ መሆን የሚከሰተው በህፃኑ ደም ውስጥ ቢሊሩቢን የሚባል ኬሚካል ከመጠን ባለፊ ሲበዛ እና ሲጠራቀም ነው። ከተወለዱ ጨቅላ ህፃናት እስክ 60 በመቶ የሚከሰት ነው። እንደ ምክንያቶቹ ከቀላል እስክ ከባድ ሊሆን ይችላል።


አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ሲሆኑ በቂ የሆነ የእናት ጡት በማጥባት የሚስተካከል ሲሆን መጠኑ ከፍ ያለ ከሆነ ግን በፍጥነት ህክምና ካላገኘ በህፃኑ እድገት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል። የህድገት ውስንነት ወይም የዘገመ ህድግት እንዲሁም ለሚጥል በሽታ መጋለጥ ያስከትላል።


የሚከሰትበት ምክንያቶች?


ይህን ችግር የሚያመጡ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋና ዋናዎቹን ልጥቀስ ፦


ባጠቃላይ ይህ ችግር - የተፈጥሮአዊ ለውጥ ችግር እንዲሁም - በሌላ ህመሞች ምክንያት የሚመጣ ችግር ብለን ልንከፍለው እንችላለን


የተፈጥሮአዊ ቢጫነት (physiologic jaundice)


ይህ የተለመደው ወይም በብዛት የሚታየው አይነት የቢጫነት አምጪ ምክንያት ከሚያመጡት ምክንያቶች ዋና ዋናዎቹ :-

- በቂ የእናት ጡት በደንብ አለመጥባት


- የጨቅላ ህፃናት ጨጏራ ውስጥ የሚያስፈልጉ ጠቃሚ ተህዋሲያን ቁጥር ማነስ


- ከጊዜያቸው በፊት የተወለዱ ህፃናት የደም ህዋሳታቸው ኬሚካሉን ማጣራት አቅም ማጣት


- የአንዳንድ የጡት ወተት ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች በጨቅላ ህፃናት የመጀመሪያዎቹ ቀናት መፈጨት ወይም መብላላት አለመቻል፡፡


- እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ብዙ ጊዜ በብዙ ጨቅላ ህፃናት ላይ የሚያጋጥም እና በራሱ ጊዜ የሚጣፋ ቢጫነት ነው። ይህም ከ10 እስከ 14 ቀናት ባለው ጊዜ በራሱ የሚጠፋ ሲሆን። የእናት ጡት በደንብ በማጥባት እና ፀሐይ በማስመታት መታከም የሚችል ነው።


በሌሎች ህመሞች ምክንያት የሚመጣ ቢጫነት (pathologic / organic cause)


ብዙ ህመሞች የጨቅላ ህፃን ቢጫነትን ሊያመጡ ቢችችሉም ዋናዎቹ የሚባሉት

- በቫይረስ / በባክቴሪያ የሚመጡ የጨቅላ ህፃናት ኢንፌክሽን


- የእናትና የጨቅላው ህፃን የደም አይነት ልዩነት በተለይ እናት ደም አይነት O ከሆነ


በጨቅላ ህፃናት ጭንቅላት ላይ የደም መጠራቀም


ምልክቶቹ ምንድናቸው?


ይህ ችግር ያጋጠማቸው ጨቅላ ህፃናት ከሚታይባቸው ምልክቶች ዋና ዋናዎቹ የሚባሉት :-


- የአይናቸው ነጩ ክፍል ቢጫ መሆን


- የህፃኑ ቆዳ በጣም ቢጫ መሆን


- ህፃኑ ሲያለቅስ በጣም የመረረ እና ድምፁ በጣም ከተለወጠ


- መነጫነጭና በደንብ አለመተኛት


- መጥባት ማስቸገር ወይም ማቆም


- ንቁ አለመሆንና መተኛት


- የደማቸው Bilirubin መጠን ከ14 ሚግ /ዴሲሊትር በላይ መጨመር


- መጠኑ እጅግ ሲጨምር ወይም ሳይታከም ከቆየ የሰውነት ማንቀጥቀጥ የፊት አካባቢ ያሉ ጡንቻዎች ስራ ማቆም

- እነዚህ ምልክቶች ከታዩ ባፋጣኝ ወደ ጤና ተቀም መተው በደማቸው ውስጥ የሚገኘው የbilirubin መጠን መለካት ይኖርበታል፡፡


ህክምናው ምንድነው?


- ህክምናው እንደ በሽታው ምክንያት እና እንደ ደረጃዎቹ የሚሰጥ ሲሆን። ቀላል ለሚባሉት በቂ የእናት ጠት ማጥባት በቂ ሲሆን።


- በተለይ በበሽታ የሚመጣ የጨቅላ ህፃናት ቢጫነት ከሆነ ህፃኑን ቶሎ ወደ ጤና ተቋም በማምጣት አንደ ደረጃው ህክምና የሚሰጥ ሲሆን


በተለየ ቀለም (ሰማያዊ) ብርሀን ህክምና (phototherapy)


ነገር ግን መጠኑ ከፍ ያለ ከሆነ ከ25ሚግ/ዴሲሊትር በላይ ከሆነ የህፃኑን ደም ሙሉ በሙሉ በመቀየር ወይም exchange transfusion ይታከማል ፡፡

ለማንኛውም ከልጆ ጤና የሚበልጥ ነገር የለምና የቅርብ ክትትል እንዲሁም ሕክምና ያድርጉ።


ፈጣሪ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን


✍️ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም


መረጃውን ጠቃሚ ከመሰልዎት በቀናነት ያጋሩት


ዶ/ር መሐመድ በሽር ፤ የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም



Via: Hakim


Doctors Online 🇪🇹

Report Page