ደን other9 ጎንቻ...2

ደን other9 ጎንቻ...2


Eid Mubarak!

ግልጽ የደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ እነገት ቀበሌ ልዩ ስሙ ሟርተኝ ከተባለ ቦታ የለማ የአዲስ አንባ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ደን

1 የፈረንጅ ፅድ
2.ከረንስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን /TIN/ ያላቸው፣
ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
የሚሸጡት ችግኞች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና የሚሸጡ ችግኞች የመሸጫ መነሻ ዋጋ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከተራ ቁጥር ከ1-3 ድረስ ለእያንዳንዳቸው የማይ መለስ ብር 150.00 ( አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ብቻ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ እነገት ቀበሌ ልዩ አዲስ አንባ ቀንቦጭ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ማግኘት ይቻላል፡፡
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ) ለሁሉም ለተራ ቁጥር 1፣2፣3፣ ለእያንዳንዳቸው የሞላችሁትን ዋጋ 2% ብቻ በ ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጂ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጐንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ገጠር መሬት አስ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀ ጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጎ/ሲ/እ/ወ/ገጠ/መሬ/አስ/አጠ/ጽ/ቤት ኃላፊ ቢሮ ቁጥር 1/አንድ / በ16/ አሥራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3 ፡30 ሰዓት ታሽጐ 4 ፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ያወጡትን ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡
ለአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈውን ችግኞች ወረዳው ድረስ በመምጣት በራሱ ትራንስፖርትና ማንኛውም ወጪ በራሱ ሸፍኖ መውሰድ የሚችል፡፡
መ/ቤቱ ጨረታ አሸናፊውን በነጠላ ዋጋ ይለያል፡፡
ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ አቤቱታ ወይም ቅሬታ ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጪ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
መ/ቤቱ አሸናፊ ድርጅቱ የአሸነፈውን ዕቃዎች 20% ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ችግኞችን ማለትም የፈረንጅ ፅድ፣ ዲከረንስ እና ባህርዛፍ በባለሙያ እየተረጋገጠ የምናስረክብ ይሆናል፡፡
የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓላት ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡
አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
አሸናፊው ድርጅት ሮያሊቲ 13% እና ሌሎች ክፍያዎችን መከፈል የሚችል መሆን አለበት፡፡
ሽያጭ ፈጻሚው አካል ሽያጩን ለመገምገም ለማፅደቅ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና አሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስከሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ፀንቶ የሚቆይበት ለ40 ቀን ይሆናል፡፡
ተጫራቾች በሞሉት የጨረታ ፖስታ ላይ ከታሸገ በኋላ ጐንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ እነገት ቀበሌ የአዲስ አንባ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ደን ተብሎ በጉልህ ከተጻፈ በኋላ ለዚህ ተግባር ከተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ገጠ/መሬ/አስ/አጠ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0586640163/0960841820 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ እነገት ቀበሌ

ልዩ ስሙ ሟርተኝ ከተባለው

ቦታ የሚገኘው የአዲስ አንባ ገብርኤል

ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 14 ቀን 2012

Deadline: June 6, 2020


© walia tender

Report Page