የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አጫጭር መረጃዎች !

የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አጫጭር መረጃዎች !

KIDUS YOFTAHE


- ታሪካዊው የአዲስ አበባ ስታዲየም ከ 274 ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታ ያስተናግዳል ።


- በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉ ጨዋታዎች በሱፐር ስፖርት በቀጥታ የሚሰራጩ ይሆናል ። 


- ፕርሚየር ሊጉ ሰበታ ከተማ ከ ድሬድዋ በሚያደርጉት ጨዋታ ከምሳ ሰዓት በፊት ይጀምራል ።


- ኢትዮጵያ ቡና እና ወላይታ ዲቻ የውጭ ሀገር ተጫዋቾች የሌላቸው ብቸኞቹ ክለቦች ናቸው ።



- ከትላላልቅ የተጨዋቾች ግዢ በኋላ ፈረሰኞቹ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ከሶስት ዓመታት በኋላ ወደ ቀድሞ ክብራቸው ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል ።


- በሀገር ውስጥ ተጫዋቾች ራሳቸውን በማጠናከር ለሊጉ ዋንጫ የሚጠበቁት ፋሲል ከነማ እና ጊዮርጊስ በሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ ይገናኛሉ ። 



- ከብሔራዊ ቡድን ስንብት ማግስት ልምድ ያላቸውን ተጫዋቾች ያሰባሰበውን ሰበታ ከተማ የተረከበው አብርሀም መብርሀቱ የውድድር ዓመቱ ክስተት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ።


- ሰበታ ከተማ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና አዳማ ከተማ በአዲስ አሰልጣኞች እየተመሩ የውድድር ዓመቱን የሚጀምሩ ክለቦች ናቸው ።


- ኢትዮጵያ ቡና ፣ ወላይታ ድቻ ፣ ሰበታ ከተማ እና ሲዳማ ቡና የውጭ ሀገር ግብ ጠባቂዎች የሌላቸው ብቸኞቹ ክለቦች ናቸው ።


ትውስታ !


- የድሬድዋ ከተማው ኤልያስ ማሞ የባለፈው የውድድር ዓመትን የመጀመሪያ ግብ ማስቆጠር የቻለው ተጫዋች ነበር ።


- የሰበታ ከተማው አዲስ ተስፋዬ ፈጣኑን የቀይ ካርድ በመጀመሪያው ሳምንት የተመለከተ ተጫዋች ነበር ።


- አስራ ሶስት ጎሎች በባለፈው የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት ላይ መቆጠር ችለው ነበር ።


በአሰልጣኝ አብርሀም መብርሀቱ የሚመራው ሰበታ ከተማ የዘንድሮው የውድድር ዓመት ክስተት ይሆናል ተብሎ ይታመናል ።


ከሰበታ በተጨማሪም ወደ ፕርሚየር ሊጉ ካደጉ በኋላ በየአመቱ ትልቅ ተፎካካሪነታቸውን እያሳዩ የሚገኙት የጣና ሞገዶቹ ዘንድሮ ላይ ብርቱ ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል ።


የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጀመሪያ ሳምንት መርሐ ግብሮች


Report Page