የወንድ ዘር ፈሳሽ ቶሎ ማፍሰስ (Premature Ejaculation)

የወንድ ዘር ፈሳሽ ቶሎ ማፍሰስ (Premature Ejaculation)

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

 

በእናንተ ጥያቄ መሰረት በፆታዊ ግንኙነት ወቅት የወንድ ዘር ፈሳሽ ቶሎ ስለማፍሰስ ጠለቅ ያለ ጥንክር አዘጋጅተንላችኋል፡፡

 

የዘር ፈሳሽ ቶሎ ማፍሰስ (Premature Ejaculation) ምንድነው?

በግንኙነት ወቅት የወንድ ዘር ፈሳሽ ቶሎ ማፍሰስ ወይም ቶሎ መርጨት (Premature Ejaculation) የምንለው አንድ ወንድ የወሲብ አጋሩ ሳይረካ የወንድ ዘር ፈሳሽ  ሲያፈስ ወይም ሲረጭ ነው፡፡ ይህ ብዙ ሰው ላይ የሚታይ የተለመደ የሚባል ችግር ነው፡፡ እንደየምንጮቹ ቁጥሮች ቢለያዩም ከ3 ወንዶች አንዱ ላይ እንደሚታይ ይገመታል፡፡

 

አንድ ሰው ላይ በተደጋጋሚ እስካልተከሰተ ድረስ የሚያሳስብ አይደለም፡፡ ነገር ግን የሚከተሉትን ካስተዋሉ የችግሩ ተጠዊ ኖት፤

-         ሁልጊዜ ወይም በአብዛኛው ወሲብ ላይ በአንድ ደቂቃ ውስጥ የወንድ ዘር ፈሳሽ ከፈሰሰ

-         በአብዛኛው ጊዜ ፈሳሹ እንዳይወጣ መያዝ ካልተቻለ

-         በዚሁ ምክንያት ፍርሃት እና ጭንቀት ከተሰማ፤ ተያይዞም ፆታዊ ግንኙነቶችን ማስወገድ

 

አካላዊ እንዲሁም ስነ-አእምሮአዊ ምክንቶች ከችግሩ ጋር ሊያያዙ ይችላል፡፡ ብዙ ወንዶች ሁኔታው ምቾት ስለማይሰጣቸው ሊያወሩም ሆነ መፍትሔ ለማግኘት ወደ ጤና ተቛም ሲሄዱ አይስተዋልም፡፡ ነገር ግን የወንድ ዘር ፈሳሽ ቶሎ ማፍሰስ የተለመደ እና መታከም የሚችል ነው፡፡ ሀኪሞት የሚወስዱት መድሐኒት ሊዝሎት ይችላል፤ በተጨማሪም የምክር አገልግሎት እና የተለያዩ የወሲብ አይነቶች ይረዳሉ፡፡

 

ምልክቶች

ዋነኛው ምልክት ወሲብ ላይ ከአንድ ደቂቃ በላይ የወንድ ዘር ፈሳሽ ማፍሰስን /መርጨትን ማቆየት ወይም ማዘግየት አለመቻል ነው፡፡ ይህ ችግር በማንኛውም የወሲብ አይነት ላይ በተጨማሪም ማስተርቤሽን (Masturbation) ላይም ሊታይ ይችላል፡፡

 

የወንድ ዘር ፈሳሽ ቶሎ ማፍሰስ ለሁለት ይከፈላል፤

1.      ከድሮ ጀምሮ የነበረ

-         ከመጀመሪያ ወሲባዊ ግንኙነት ጀምሮ ሁልጊዜ ችግሩ ከነበረ እና ካለ

2.      ከጊዜ በኋላ የመጣ

-         ይህኛው አይነት ከዚህ ቀደም መሰል ችግር የሌለበት ሰው ላይ ሲከሰት

 

በጣም ብዙ ወንዶች የወንድ ዘር ፈሳሽ ቶሎ ማፍሰስ ምልክቶች ሊታይባቸው ቢችልም እነዚህ ምልክቶች ብቻ የችግሩ ተጠቂ መሆናቸውን ግን አያሳይም፡፡ ምክንያቱም በርካቶች ጊዜያዊ የሆነ ምልክት ብቻ ነው ያላቸው፤ አንዳንዴ ብቻ የዘር ፈሳሽ ቶሎ ሊፈስ ቢችልም ሌሎች ጊዜአት ግን የተለመደ ወይም ጤነኛ ይሆናሉ፡፡

 

ሃኪሞት ጋር መቼ መሄድ አለቦት?

ወሲብ ነክ ጉዳዮችን ማውራት ለብዙ ወንዶች የሚያሳፍር ቢሆንም ሁኔታው መፍትሔ ስላለው በአብዛኛው ወሲባዊ ግንኙነቶች ላይ ቶሎ የወንድ ዘር ፈሳሽ የሚፈስ ከመሰሎት ሃኪሞን ቢያማክሩ ይመረጣል፡፡

 

የንግግር ህክምና ብቻውን ውጤታማ ሲሆን ይታያል፡፡ ለምሳሌ ከሃኪሞ አንዳንድ ጊዜ መሰል ሁኔታዎች ሊፈጠሩ እንደሚችል መስማት በራሱ እፎይታ ሲሰጥ በጥናቶች ታይቷል፡፡ መዘንጋት የሌለበት የተለያዩ ጥናቶች እንደሚሉት ከሆነ ነገር ወሲብ ከተጀመረበት እስከ የወንድ ዘር ፈሳሽ የሚፈስበት ጊዜ በአማካይ 5 ደቂቃ ነው፡፡

 

 የወንድ ዘር ፈሳሽ ቶሎ መፍሰስ በምን ምክንያት ይመጣል?

የዘር ፈሳሽ ቶሎ መፍሰስ ትክክለኛ ማክንያቱ እስካሁን አይታወቅም፡፡ ተመራማሪዎች ውስብስብ የስነልቦና እና አካላዊ ምክንያቶች አንድ ላይ እንደሚያመጡት ይናገራሉ፡፡

 

ስነልቦናዊ ምክንያቶች፤

·        ወሲባዊ ግንኙነት በአፍላነት እድሜ መጀመር

·        ፆታዊ ጥቃት

·        ለሰውነት አቋም የሚሰጥ የተዛባ ወይም ጥሩ ያልሆነ አመለካከት

·        ድብርት

·        ስለሁኔታው ብዙ መጨነቅ

·        በወሲብ ግንኙነት ለሚፈጠረው ነገር የተጠያቂነት ስሜት መሰማት

·        ሌሎች ምክንቶች፤

-         የብልት አለመቆም

-         ጭንቀት

-         ከወሲብ አጋር ጋር ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት

 

አካላዊ ምክንያቶች፤

·        የሆርሞን መዛባት

·        አእምሮ ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች መጠን መዛባት

·        በዘር

 

ተጋላጭነት

-         የብልት አለመቆም

-         ጭንቀት ወይም ውጥረት


 

ተያይዞ ምን ሊመጣ ይችላል?

የዘር ፈሳሽ ቶሎ መፍሰስ በግል ህይወት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ ለምሳሌ፤

·        ጭንቀት እና ግንኙነቶች ላይ ችግር መፈጠር

·        መውለድ አለመቻል

 

 

ምርመራ

ሃኪሞት ስለወሲብ ህይወት እንዲሁም በአጠቃላይ ስለጤና ይጠይቃል፤ አካላዊ ምርመራም ሊደርግ ይችላል፡፡ ከዘር ፈሳሽ ቶሎ መፍሰስ በተጨማሪ የብልት አለመቆም ችግር የሆርሞን መጠንን ለመለካት የደም ምርመራ እና ሌሎች ምርመራዎች ይታዘዛሉ፡፡

 

አንዳንዴም ሃኪሞ ወደ የሽንት ቧንቧ ስፔሻሊስት ወይም የስነ-አእምሮ ሃኪም ሊመራ ይችላል፡፡

 


ሕክምና

የባህሪ ወይም የልምድ ለውጥ፣ የሚቀቡ ማደንዘዣዎች፣ የሚዋጥ መድሐኒት እና የንግግር ህክምና አማራጮች ናቸው፡፡ ማስተዋል ያለብን ነገር ግን ህክምናውን መምረጥ ጊዜ የሚወስድ ነው፤ ለአንድ ሰው ሁለት ወይም ከዛ በላይ የህክምና መንገድ መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ የባህሪ እና የሚዋጡ መድሐኒቶችን አንድ ላይ መውሰድ ውጤታማ ሆኖ ታይቷል፡፡

 

የባህሪ ወይም ልማድ መንገድ

አንዳንድ ጊዜ ከጥቂት ሰዓታት በፊት ማስተርቤት ማድረግ በግንኙነት ወቅት የዘር ፈሳሽ ቶሎ እንዳይፈስ ይረዳል፡፡ እንዲሁም ለትንሽ ጊዜ ወሲባዊ ግንኙነትን በማቆም ሌሎች የፍቅር ጨዋታዎች ላ ማዘውተርም እንደሚረዳ ብዙ ጥናቶች መስክረዋል፡፡

 

የታችኛው የወገብ ጡንቻዎችን ማጠንከር

ደካማ የመቀመጫ ጡንቻ የዘር ፈሳሽ ቶሎ እንዲፈስ እና ለመያዝ እንዲከብድ ከፍተኛ ተፅዕኖ አላቸው፡፡ የኪጋል እንቅስቃሴ  (Kegel Exercise) እነዚህም ጡንቻዎች ለማጠንከር ይረዳል፡፡

ይህን እንቅስቃሴ ለመስራት፤

·        ጡንቻዎቹን መለየት - የታችኛው የወገብ ጡንቻዎችን ለመለየት ውሃ ሽንት በሚሠኑበት ወቅት መሐል ላይ ለማቆም መሞከር ወይም አየር ነፊንጢጣ በኩል ሊወጣ ሲል ለመያዝ መሞከር፡፡ ጡንቻዎቹን ከለዩ በኋላ የተመቾትን መንገድ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡

·        እንቅስቃሴውን መቀጠል - እነዚህን ጡንቻዎች ለ3 ሴኮንዶች መያዝ እና ለቀጣይ 3 ሴኮንዶች መልቀቅ፡፡ ይህን በቀን ውስጥ ቆሞ፣ ተቀምጦ፣ እየትመዱ ወይም ተኝቶ በተደጋጋሚ መስራት ውጤታማ ነው፡፡

·        አሰራሩን ማስተካከል - የኪጋል እንቅስቃሴ የሚጠበቀውን ውጤት እንዲያመጣ የመቀመጫ ጡንቻን ብቻ ማሰራቶን እርግጠኛ ይሆኑ፡፡ የሆድ፣ የዳሌ ዌም የመቀመጫ ጡንቻዎችን ማላላት አያስፈልግም፡፡ እንዲሁም በእንቅስቃሴው ጊዜ ዘና ብሎ በደንብ መተንፈስ እንጂ ትንፋሽ መያዝ አይመከርም፡፡

·        እንቅስቃሴውን በቀን ደጋግሞ መስራት (ቢያንስ 10 ጊዜ)

 

ማቆም - መያዝ (The Pause-Squeeze Technique)

በብዙዎች የሚመረጥጠ ባይሆንም ለእርሶ እና ለወሲብ አጋሮ ይህን መንገድ እንዲሞክሮ ሃኪሞ ሊመክር ይችላል፡፡ የሚከተለውን ይመስላል፤

1.       የዘር ፍሬ ፈሳሽ ሊፈስ እንደሆነ እስኪሰማ ድረስ እንደተለመደው ወሲብ ማድረግ

2.      ፈሳሹ ሊፈስ ሲል የወሲብ አጋሮ ለጥቂት ሴኮንዶች የብልቱን ጫፍ በደንብ እንዲይዙ ማድረግ፣ የመፍሰስ ስሜቱ ሲጠፋ መልቀቅ

3.      እንደአስፈላጊነቱ ከላይ የተቀመጠውን መድገም

ይህንን ደጋግሞ በማድረግ ለውጥ ሊመጣ ይችላል፡፡ ከጊዜ በኋም የዘር ፍሬን መያዝ እንደ ስራ ሳይሆን የተለመደ እና ቀላል ነገር ይሆናል፡፡

ይህ መንገድ ህመም ሳመጣ ወይም ካልተመቸ ሌላው አማራጭ የዘር ፈሳሽ ሊመጣ ሲል ወሲብን ቆም አድርጎ ከዛ ደግሞ መቀጠል፤ ይህ መንገድ አቁሞ-መቀጠል (Stop-Start Technique) ይባላል፡፡

 

ኮንዶም

ኮንዶም መጠቀም የወንድ ብልትን ስሜት ስለሚቀንስ የዘር ፈሳሽ ቶሎ እንዳየፈስ ይረዳል፡፡ ለዚሁ የሚጠቅምም ኮንዶም በአደጉት ሃገራት ይገኛል፡፡

 

መድሐኒቶች (እነዚህ መድሐኒቶች ሃኪም ጋር ቀርበው ብቻ የሚታዘዙ ናቸው)

-         የሚቀባ ወይም የሚረጭ የማደንዘዣ ወይም የሚስተኛ መድሐኒት

-         የሚዋጡ መድሐኒቶች

 

የምክር አገልግሎት

ይህ መንገድ ስለ ወሲባዊ ህይወት እና ሌሎች ተያያዥ ነገሮች ከባለሙያ ጋር የሚያወሩበት ነው፤ በዚያም ውስጥ እንዴት ጭንቀትን ማስወገድ እንደሚቻል መማማር ይቻላል፡፡ ብዘ ጊዜ ከመድሐኒቶች ጎን ለጎን ሲሰጥ ውጤታማ ነው፡፡

 

መዘንጋት የሌለበት ነገር ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር ከወሲብ ጓደኛ ጋር ስለሁኔታው በግልፅ ማውራት እና በጋራ መፍትሔ መፈለግ አስገላጊ ነው፡፡

 

 

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

         የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia

 

 

 

Report Page