የኢየሱስ መንገድ

የኢየሱስ መንገድ

Solicious18 Wallpapers™
ዳዊት ጌታቸው | የኢየሱስ መንገድ

በዚህች ምድር ስኖር ብርቱ ሰልፍ ቢኖርም

ንፋስ ማዕበሉ ሊጥሉኝ ቢጥሩም

እምነቴን ሊፈትን ዙሪያዬን ቢዞርም

የጠራኝ ክርስቶስ ስለኔ አሸንፏል ሁሉንም


እሮጣለሁ ይህን የጽድቅ ጎዳና

እሮጣለሁ ይህን የሕይወት መንገድ

ወስኛለው መስቀሉን እያየሁ ልሄድ

ከኢየሱስ ሌላ ላልወድ

ወደ ኋላም ከቶ ላልሄድ


ግብ ግብ ከኔ ጋር ብዙ ቢያዝለኝም

ነፍስን በሚያደክም ትግል ውስጥ ብኖርም

ስጋዬን እየጎሸምኩ ወደ ፊት እሄዳለሁ

የምኖርለትን ዓላማ እያየሁ


እሮጣለሁ ይህን የጽድቅ ጎዳና

እሮጣለሁ ይህን የሕይወት መንገድ

ወስኛለው መስቀሉን እያየሁ ልሄድ

ከኢየሱስ ሌላ ላልወድ

ወደ ኋላም ከቶ ላልሄድ


በፀጋው ጉልበት እታመናለሁ

ብወድቅም እንኳን ዳግም እቆማለሁ

ግን እስከ ፍፃሜ መስቀሉን እያየሁ

የኢየሱስን መንገድ እኖረዋለሁ


ኢየሱስን ነው ዓይኔ የሚያየው

ኢየሱስን ነው ተስፋ የማደርገው

መስቀሉን ብቻ ነው ትኩር ብዩ የማየው

እስከ ፍጻሜ ለክብር እሮጣለሁ


ዳዊት ጌታቸው | የኢየሱስ መንገድ

💌 Tensae Berhanu


Written By: Dawit Getachew

Release Date: August 1, 2020


የኢየሱስ መንገድ | ዳዊት ጌታቸው የመዝሙር ቪድዮ



Report Page