የአሳ ዘይት

የአሳ ዘይት

Dr, Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

ለዘመናት በጠቀሜታው ሲወደስ የኖረውን የአሳ ዘይት የተረጋገጡ ጠቀሜታዎች እናያለን፤ ተከታተሉን፡፡

 

የአሳ ዘይት

የአሳ ዘይት በጣም ከሚዘወትር የንጥረ-ነገር ሰፕሊመንት አንደኛው ነው፡፡ በኦሜጋ 3 የበለጸገ መሆኑ ለጤና ተመራጭ ያደርገዋል፡፡ የአሳ ዘይት - ዘይት ካላቸው የአሳ አይነቶች የሚዘጋጅ ነው፡፡

ባለለፉት አመታት በተለይ ባደጉት ሀገራት የአሳ ዘይት በጠቀሜታው በጣም የሚደነቅ እና በብዙ የህክምና ባለሙያዎች የሚመከር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በውስጡ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ- ምግቦችን በመያዙ በተለይ የልብ በሽታን ለመከላከል ሁነኛ እንደሆነ ይነገራል፡፡

 

የአሳ ዘይት ጥቅሞች

-        የደም ግፊትን ለመቀነስ

-        መጥፎ የኮሌስትሮል አይነትን ለመቀነስ

-        በደም ስር እና ጉበት ውስጥ የሚከማችን እና የሚጋገር ስብን ለመቀነስ

-        የልብን ጤንነት ለመጠበቅ

-        የልብ ምት አመታትን ለማስተካከል

-        የልብ ድካምን እና የጭንቅላት ውስጥ ደም መፍሰስን ተጋላጭነት ለመቀነስ

-        የልብ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ላይ ድንገተኛ ሞትን ለመከላከል

-        አንዳንድ የስነ-አእምሮ በሽታዎችን ለማከም

-        የድብርትን ስሜት ለመቀነስ

-        ክብደት ለመቀነስ

-        የአይንን ጤንነት ለመጠበቅ

-        የሰውነትን ሴሎች መቆጣት ለመቀነስ

-        ለጤናማ ቆዳ

-        በእርግዝና ወቅት እና ለህፃናት ሁለንተናዊ ጤንነት

-        ልጆች ላይ ትኩረትን ለማስተካከል

-        የአስምን እና የአለርጂ ምልክቶችን ለመቀነስ

-        የአጥንትን ጤንነት ለመጠበቅ


የአሜሪካ የልብ ማህበር ማንኛውም ሰው በሳምንት ቢያንስ ሁለት ጊዜ የአሳ ዘይት እንዲወስዱ ይመከራል፡፡ በቀን ከ3 ግራም በላይ መውሰድ ግን አይመከርም፡፡ የአሳ ውጤቶችን መመገብም የአሳ ዘይት ከመውሰድ አይተናነስም፡፡

 

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

        የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia

 

 

 

 

 

Report Page