"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል"

"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል"

@YeBiruk ዲያቆን ቡሩክ ይርጋ ዘውብ

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

       አሜን

✍"በቸርነትህ ዓመታትን ታቀናጃለህ"

📖መዝ 64፥11


     ቀናችንን በጸሎት እንጀምር


  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

✍️"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል"

📖1ኛ ጴጥ 4፥3

  ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

 

❖ መስከረም 1 ቀን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የኢትዮጵያውያን የዘመን መለወጫ በዓል ነው፡፡


❖ ይህንን ምክንያት አድርገን በዚህ ጽሑፍ የዘመን አቆጣጠርን ምንነትና ታሪክ፣ የኢትዮጵያን የዘመን አቆጣጠር እንዲሁም የዘመን መለወጫ በዓልና አዲስ ዓመት ሊኖራቸው የሚገባውን መንፈሳዊ ትርጉምና ፋይዳ አስመልክተን አንዳንድ ነገሮችን እንመለከታለን፤ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን፤ እንግዲህ በአጠቃላይ ዋናዎቹ የጊዜ / የዘመን/ መስፊሪያዎች ዕለት፣ ወር እና ዓመት ናቸው፡፡


❖ ሦስትቱም ተመላላሽ ክስተቶችን / ለምሳሌ የፀሐይን መውጣት/ መሠረት ያደረጉ ናቸው፤ እነዚሀ ተመላላሽ ክስተቶች አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪከሰቱ የሚፈጁት ዘመን ወይም ጊዜ ዓውድ ይባላል፡፡


❖ ዓውድ ማለት ዙሪያ፣ ክብ፣ እንደ ቀለበት ዙሮ የሚገጥም ማለት ነው፤ ስለዚህዓውድ ማለት ክስተቶቹ አንድ ጊዜ ከተከሰቱ በኋላ ደግመው እስኪመጡ ድረስ ያለው ጊዜ ማለት ነው፡፡


❖ በዚህ መሠረት ከላይ ያየናቸው ሦስት መስፈሪያዎች/ ዕለት፣ ወርኀ፣ ዓመት/ ዓዕዋዳት / ዓውዶች/ የሚወጡበት ጊዜ ዓውደ ዕለት፣ ዓውደ ወርኀ፣ ዓውደ ዓመት ይባላሉ፡፡


❖ መጀመሪያ ላይ ሰዎች እነዚህን ሦስቱን መስፈሪያዎች /ዓዕዋዳት/ /በተለይም ቀንና እና ወርን/ለየብቻቸው ይጠቀሙባቸው ነበር፤ ከዚህን ያህል ቀን፣ከዚህን ያህል ወር በኋላ /በፊት/ እያሉ ጊዜን ይለኩ ነበር፡፡


❖ እነዚህ ሦስቱን በቅንብር/በቅንጅት/ ለመጠቀም ሲፈለግ ግን የዘመን አቆጣጠር ስሌት ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም አንድ ወር 29 ከግማሽ ቀን ነው፤ እንዲሁ እንዳለ ለመቁጠር ቢፈለግ የመጀመሪያው ወር ጠዋት ላይ ቢጀመር ሁለተኛው ወር ምሽት ላይ ይጀምራል፣ ሦስተኛው ደግሞ ድጋሚ ጠዋት ላይ ይጀምራል፤ ይህን ለመቅረፍ ወሩን ሙሉ ሰላሳ ቀን ቢያደርጉት ከትክክለኛው ወር /የጨረቃ ዐውድ/ ግማሽ ቀን ይተርፋል፤ 29 ቀን ብቻ ቢያደርጉት ደግሞ ግማሸ ቀን ይጎድላል፡፡


❖ አንድ ዓመት 365 ከሩብ ዕለታት አሉት፤ ዓመትን በወራት ለመቁጠር ቢፈለግ፤ዓመቱን 12 ወር ቢያደርጉት የዓመቱ /የዕለታት ቁጥር /29.5X12=354/ ብቻ ይሆናል፡፡


❖"ይህም ከትክክለኛው ዓመት /365-354=11/ ዕለታት ያህል ያንሳል፤ 13 ወር ቢያደርጉት ዓመቱ /365X13=385.5/ ቀናት ይሆናል ይህም ከትክክለኛው ዓመት /383.5-365=19/ ቀናት ያህል ይበልጣል፡፡


❖ ስለዚህ እነዚህን መስፈሪያዎች በቅንጅት ለመጠቀምይህንን አለመጣጣም የሚፈታ ቀመር /የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት/ ያስፈልጋል፤ በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የዘመን አቆጣጠሮች ተዘጋጅተዋል፤ ከእነዚህ መካከል የአይሁድን፣የሮማውያንን እና የሀገራችንን አቆጣጠሮች በአጭሩ እንመለከታለን፡፡


❖ የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር የአይሁድ ዘመን አቆጣጠር እያንዳንዳቸው 29 እና 30 ዕለታት ያሏቸው 12 ወራት አሏቸው፤ እነዚህ የዓመቱ 12 ወራት በአጠቃላይ 354 ያህል ብቻ ዕለታት ይኖሯቸዋል፡፡


❖"ይህም በትክክለኛው ዓመት በ11 ዕለታትያህል ቢያንስም አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፤ ልዩነቱ በሁለት ዓመታት 22 ዕለታት፣ በሦስት ዓመት ደግሞ 33 ዕለታት ያህል ይሆናል፡፡


❖ ስለዚህ በየሦስት ዓመቱ ከአስራ ሁለተኛው ወር ጳጉሜን በፊት አንድ ሌላ ወር ይጨምሩና የዓመቱን የወራት ቁጥር ዐሥራ ሦስትያደርጉና ልዩነቱንያስተካክሉታል፡፡


ተ.ቁ    የግብጽ ወሮች    የኢትዮጵያ ወሮች 

1        ቱት/ዩት         መስከረም 

2        ባባ/ፓከር        ጥቅምት 

3        ሀቱር            ኅዳር 

4      ኪሃክ/ከያክ         ታኅሳሥ 

5       ጡባ/ቶቢር        ጥር 

6      አምሺር/ሜሺር       የካቲት 

7       በረምሃት          መጋቢት 

8       በርሙዳ          ሚያዝያ 

9       በሸንስ            ግንቦት 

10      ቦኩሩ            ሰኔ 

11      አቢብ            ሐምሌ 

12     መስሪ             ነሐሴ 

13      ኒሳ/አፓጎሜኔ       ጳጉሜን


❖ የኢትዮጵያውያንና የግብጻውያን ዘመን አቆጣጠር የሀገራችን ኢትዮጵያ እና የጥንት ግብጻውያን /ዛሬም ድረስ የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን Yየምትጠቀምበት/ የዘመን አቆጣጠር ተመሳሳይ ነው፤ሁለታችንም እኩል ሰላሳ ቀናት ያሏቸው12 ወራት አሉን፡፡


❖ እነዚህ 12 ወራት / 12X30=360/ ቀናት አሏቸው፤ እነዚህ ቀናት በትክክለኛው ዓመት በ/365.25-360=5.25/ ቀናት ያንሳሉ፤ ይህንንም 5 ቀናት/ በ4 ዓመት አንድ ጊዜ 6 ቀናት/ ያሏትን 13ኛ ወር በመጨመር ያስተካክሉታል፤ የኢትዮጵያውያን እና የግብጻውያን ወሮች ስም እንደሚከተለው ነው፡፡  

 

📌 የሮማውያን ዘመን አቆጣጠር


❖ የጥንት ሮማውያን የመጀመሪያው የዘመን መቁጠሪያ 30 እና 31 ቀናት ያሏቸው 10 ወራት ብቻ ነበሩት፤ በአንድ ዓመት ያሉት ቀናት ቁጥር 304 ብቻ ነበር፡፡


❖ ሮማውያን ይህን ያዘጋጀው የሮማ ከተማን የመሠረተው ሮሙለስ እንደሆነ ይናገራሉ፤ በ713 ዓመት ቅ.ል.ክ ኑማ ፓምፒለስ /Noma Pompilos/ የተባለ የሮማ ንጉሥ ሌሎች ሁለት ተጨማሪ ወራት ጨመረበት፡፡


❖ ጁሊያን የዘመን አቆጣጠር /Julian Calander/ የሮማው ንጉሥ ጁልየስ ቄሳር ለሲጃነስ የተባለ እስክንድርያዊ ሥነ ከዋክብት ተመራማሪን አማክሮ ጥንታዊውን የሮማውያን ዘመን አቆጣጠር አሻሽለው 30 እና 31 ቀናት ያላቸው11 ወራትና 28 ቀናት የአራት ዓመቱ 29 ቀናት ያሉት አንድ ወር ያለው የዘመን አቆጣጠር አዘጋጀ፡፡


❖ አሁን ምዕራባውያን የሚጠቀሙበት የጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠርም በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከተደረጉበት የቀናት ማስተካከያ በስተቀር ይኸው የጁልያን አቆጣጠር ነው፡፡


❖ እነዚህ ሁሉ ልዩ ልዩ አቆጣጠሮች መኖራቸው እንደ እውነቱ ከሆነ የሚያስከፋ አይደለም፤ ሁሉምዓላማቸው አንድ ነውና፤ ሦስቱን የጊዜ መስፈሪያዎች ማጣጣም፤ ጥያቄ ሊሆኑ የሚገባቸው የሚከተሉት ሁለት ነጥቦች ናቸው፡፡ 


፩. የዘመን ቁጥር ልዩነት


❖ ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ የዘመን አቆጣጠር መለያየትን መነሻ እንዲህ በማለት ያብራራሉ፤ «ክብ የሆነ ነገር ሲከብ ከየትኛውም ቦታ መጀመር ይቻላል፤ የዘመን አቆጣጠር /ዓውደ ዓመትም/ ይኸው ነው፡፡


❖ ዋናው ነገር አንድ ታላቅ ታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ አንድ ታላቅታሪካዊ ድርጊት ፈልጎ እርሱን መነሻ ማድረግ ነው፤ የዘመን አቆጣጠሮቹም ልዩነት መንስኤው ይኸው ነው» ይላሉ፡፡


❖ ባሕረ ሐሳብ፣ ጌታቸው ኃይሌ፣ ገጽ.65/ ለምሳሌነትም ሮማውያን የሮም ከተማ የተቆረቆረችበትን ጊዜ መነሻ ማድረጋቸውን/ በኋላም


ታላቁ እስክንድር የነገሠበት ዘመን የዘመን ቆጠራ መነሻ ሆነው እንደ ነበር ይጠቅሳሉ።


❖ መሐመድና ተከታዮች ከመካ ወደ መዲና ያደረጉትን ስደት መነሻ የሚያደርገው ኢስላማዊ የዘመን አቆጣጠርም ሌላው ተጠቃሽ ነው፡፡


❖ የአይሁድን አቆጣጠር ትተን ከላይ ያየናቸው ሁለቱ የዘመን አቆጣጠሮች /የምዕራባውያኑ የጁልስ ጎርጎርዮሳዊ አቆጣጠርና የኢትዮጵያና የግብጽ አቆጣጠር/ ሁለቱም ዘመንን የሚቆጥሩት ከክርስቶስ ልደት መነሻ አድርገው ነው፤ ይሁን እንጂ እኛ ዛሬ 2002 ዓ.ም ነው ስንል እነርሱ ደግሞ 2009 ዓ.ም ነው ይላሉ፡፡


❖ በመካከሉ የ7/8 ዓመታት ልዩነት አለ፤ እንግዲህ ጥያቄው ትክክለኛው የትኛው ነው? የሚለው ነው፤ ጉዳዩ መጻሕፍትን ሊያጽፍ የሚችልና በእርግጥም የተጻፉበት ቢሆንም ለማሳያ ያክል ሁለት ነገሮች እንመልከት


1. አሁን ባለው የምዕራባውያን አቆጣጠር ሄሮድስ የሞተው 4 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው፤ ሄሮድስ የሞተው ጌታ ተወልዶ በስደት ሦስት ዓመት ያህል በግብጽ ከቆየ በኋላ ነው፡፡


❖ ይህ ማለት በእርሱ አቆጣጠር ጌታ የተወለደው በ7 ዓመት ቅ.ል.ክ ነው ማለት ነው፤ እንግዲህ ጌታ በትክክል በተወለደበት በአንድ ዓ.ም እነርሱ ጌታ ሰባት ዓመት ሆኖታል ይላሉ ማለት ነው፤ ስለዚህ ትክክለኛውን ቁጥር ለማግኘት አሁን ካላቸው ቁጥር ላይ ሰባት ዓመት መቀነስ አለባቸው፡፡


2. ፍላቪየስ ጆሴፈስ የተባለው የአይሁድን ታሪክ የጻፈው ሊቅ እንደ መሰከረው ጌታ የተወለደበት ዓመት ነው ተብሎ በወንጌል ላይ የተጻፈው የቆጠራ ዓመት /ሕዝቡ ሁሉ የተቆጠረበትን ዘመን /ሉቃ.2.1/ በጎርጎሪያን ዘመን አቆጣጠር «7 ዓመተ እግዚአ /A.D/ ላይ ነው፡፡» በማለት መረጃ ትቶልናል ይህ ማለት ደግሞ ከምዕራባውያኑ ዘመን አቆጣጠር ላይ 7 ዓመቶች የግድ መቀነስአለበት ማለት ነው፤ ያ ሲደረግ ደግሞ የኛን ዘመን አቆጣጠር ያመጣል፡፡ 


፪. የዘመን መለወጫ ቀን ልዩነት


❖ ሁለተኛው ጉዳይ የዘመን መለወጫ ወርና ዕለት ልዩነት ነው፤ እኛ መስከረም 1 አዲስ ዓመት ስንጀምር እነርሱ በ January 1 / በእኛ ታኅሣሥ 23/ አዲስ ዓመት ይጀምራሉ፡፡


❖ ይህ ከየት የመጣ ልዩነት ነው? የእኛ እና የግብጻውያን አቆጣጠር እዚህ ጉዳይ ላይ ከአይሁድ አቆጣጠር ጋር ይስማማል፤ በአይሁድ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ኒሳን የሚባለው /በእኛ መጋቢት/ ሚያዝያ/ ነው፡፡


✍️«ይህ ወር የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ፣ በዚህም ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን የአንድ ዓመት ተባዕት ላይ ወስደው ይረዱ፤ ተብሎ የተሰጣቸውን የፋሲካ በዓል የሚያከብሩት በዚህ ወር ነው፤ ይሁን እንጂ አዲስ የዓመት በዓል አድርገው የሚያከብሩት

📖ዘፀ 12፥1-14


✍️ «የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁናችሁ፤ በዚሁ በመለከት ድምጽ የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ መስዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የተለመደ ተግባራችሁን አታከናውኑበት» ተብሎ የተሰጣቸው የሮሽ ሆሻና፣/የመለከት በዓል ወይም በዓለ መጥቅዕ/ ተብሎ የሚጠራው በዓል ነው፡፡

📖ዘሌ 13፥23-25


❖ ይህም ማለት አዲስ ዓመት የሚያከብሩት በሰባተኛው ወር በኢታኒም ወር /በእኛ መስከረም ጥቅምት/ ነው፡፡


❖ በቤተ ክርስቲያናችንም ትምህርት ዓለም የተፈጠረው መጋቢት 29 ቀን ነው፤ መስከረም ደግሞ ከመጋቢትጀምሮ ሲቆጠር ሰባተኛው ወር ነው ይህም ከአይሁድ ዘመን አቆጣጠር ጋር ተመሳሳይ ነው፤ አይሁድስ ቢሆኑ የመጀመሪያው ወር እያለ አዲስ ዓመትን ለምን በሰባተኛው ወርያከብራሉ ለሚለው ጥያቄ ሁለት ዓይነት ምላሾች /ምክንያቶች/ ይሰጣሉ፡፡


❖ የመጀመሪያው ምክንያት «ሰባተኛው ወር ኖኅ ከመርከብ የወጣበት ወር በመሆኑ ይህ የአዲስ ዓመት መጀመሪያ ተደርጎ መከበር በመጀመሩ ነው» የሚል ነው፡፡


❖ በዘመን መለወጫ ዕለት ልጃገረዶች አበባ እና ለምለም ሣር መያዛቸው ርግቢቱ ለኖኅ ካመጣችው ለምለም ወይራ /ቄጠማ/ ጋር ተያይዞ የተጀመረ መሆኑን ይናገራሉ፡፡


❖ ሁለተኛው ደግሞ መስከረም የቀንና የዕለቱ ርዝመት እኩል የሚሆኑበት ወር በመሆኑ ነው የሚል ነው፡፡


❖ የመስከረም1 ቀን ስንክሳር «የተባረከ የመስከረም ወር የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው፤ የቀኑ ሰዓትም ከሌሊቱ ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው» ይላል፤ እዚህ ላይ ማስተዋል የሚገባው ሌላው ጉዳይ በቤተክርስቲያናችን ትምህርት እመቤታችን ጌታን የጸነሰችው መጋቢት 29 ቀን ነው፡፡


❖ ይህም ቅዱስ ጳዉሎስ ፣የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት ተወለደ» /ገላ.4.4/ እንዳለው የ5500 ዘመኑ ፍጻሜ /ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ/ ነው፡፡ ጽንሰትን መጋቢት 29 ካልን በኋላ ልደትን ታህሣሥ 29 ቀን እናከብራለን፡፡


❖ ከመጋቢት 29 እስከ ታህሣሥ 29 ድረስ 9 ወር ከ5 ቀን ነው /ጳጉሜን ጨምሮ/ ጳጉሜ 6 በምትሆንበት ጊዜ ደግሞ ታህሣሥ 28 ቀን ልደት ስለሚከበር አሁንም በመሐሉ ያለው ጊዜ 9 ወር ከአምስት ቀን ይሆናል፡፡


📌 የዘመን ቆጠራ ለቤተክርስቲያን


❖ የዘመን ቆጠራ ከጌታችን ልደት በፊት የነበረው ሃይማኖታዊ ፋይዳ የሰው ልጆች ሁሉ /በተለይ አበውና ነቢያት/ በተስፋ ይጠብቁት የነበረውን የጌታችንን መምጣት የቀረውን ጊዜ ለማወቅ ነበር፡፡


❖ ተስፋው ከተፈፀመ በኋላ ደግሞ የዘመን ቆጠራ ዋና አገልግሎቱ በዓላትና አጽዋማት በዓመቱ የሚወሉበትን ዕለት ለማወቅ ነው፤ እነዚህ በዓላት እግዚአብሔር በተለያዩ ዘመናት ለሰው ልጆች ያደረጋቸው ድንቅ ነገሮችና ውለታዎች የሚታሰቡባቸው ናቸው፡፡


❖ በመጀመሪያ እነዚህ በዓላት ሁሉ መጀመሪያ በተደረጉባቸው ቀናት ይከበሩ ነበር።


🔘ለምሳሌ


❖ ስቅለት መጋቢት 27፣ ትንሳኤ መጋቢት 29፣ ልደት ታኅሣስ 29፣ የቅዱስ ሚካኤል በዓል ኅዳር 12፣ ወዘተ. . . ማለት ነው፤ አጽዋማቱም እንዲሁ፡፡ 

የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት የነበረው ዲሜጥሮስ ግን አንዳንድ በዓላትና አጽዋማት መጀመሪያ በተፈጸሙባቸው ዕለታት እንዲውሉ ይመኝ ነበር፡፡ 


❖ በተለይም ነነዌ የዐቢይ ጾም መጀመሪያ፣ እና የጾመ ሐዋርያት መጀመሪያ ሁል ጊዜ ሰኞ እንዲውሉ፤ ደብረ ዘይት፤ ሆሳዕና፤ ትንሳኤ ጰራቅሊጦስ ከእሁድ እንዳይወጡ፣ ርክበ ካህናት፣ ጾመ ድኅነት፣ ከረቡዕ፤ ዕርገት ከኀሙስ ስቅለት ከዓርብ እንዳይወጡ ይመኝ ነበር፡፡


❖ ከዚህ በኋላ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ መጥቶ «ዲሜጥሮስ ሆይ ይህ ሁሉ በሐሳብ አይፈጸምም፤በተግባር ቢያደርጉት ካልሆነ» ብሎ ሱባኤ እንዲገባ ነገረው፡፡


❖ ዲሜጥሮስም ሱባዔ ገባና የተመኘውን ሊያደርግበት የሚችል ቀመር ተገለጠለት፡፡ ቀመሩን በመጠቀምም ግብጻውያን እነዚህ በዓላት የሚውሉቸውን ቀናት በየዓመቱ እየወሰኑ ማክበር ጀመሩ፡፡


❖ በ325 የተደረገው የኒቅያ ጉባኤም ትንሳኤ ሁል ጊዜ እሁድ እንዲከበርና በዓሉ የሚከበርበትን ዕለት የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንድታስታውቅ በመወሰኑ ይህ ቀመር ተስፋፍቷል፤ ቀመሩ ወደ ሃገራቸንም መጥቷል፤ ስሙም ባሕረ ሐሳብ ይባላል፡፡


❖ ቀመሩን እኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘነው ትምህርቱን በድጋሚ ካስፋፋው 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ከነበረው ከግብጻዊው ዲያቆን ከዮሐንስ አቡሻክር በመሆኑ የአቡሻክር ትምህርትም ተብሎ ይጠራል፡፡

📚/ባሕረ ሐሳብ፣ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ፣ገጽ 19/


❖ የእኛ ሀገር ሊቃውንትም አስፋፍተውታል፤ አራቀውታልም፤ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያናችን ይህንን ቀመር በመጠቀም በየዓመቱ የሚውሉትን ተለዋዋጭ በዓላት እና አጽዋማት መቼ እንደሚውሉ ትወስናለች፡፡ 


✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝


✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉ


ም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"

📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ


        ወስብሐት ለእግዚአብሔር

               ይቆየን 


🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴


Share 

─────────────────

    

         Channel 

https://telegram.com/Tewahedo12


    FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)

 http://facebook.com/Tewahedo12  


 YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)

https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw


 ─────────────────

Report Page