የስክሪን ብርሃን እና የልጆች አይን

የስክሪን ብርሃን እና የልጆች አይን

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

በዚህ ወቅት ብዙ ወላጆች የሚቸገሩበት ጉዳይ የልጆች ስልክ፣ ታብሌት ወይም ኮምፒዩተር ይዞ መቆየት ነው፡፡ ዛሬ ከእነዚህ ስክሪኖች የሚወጡት ጨረር እንዴት አይንን እንደሚጎዳ እናያለን፡፡

 

የስክሪን ብርሃን እና የልጆች አይን ጤንነት

 

የልጆችን ስክሪን የሚያዩበትን ሰዓት መወሰን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ውጪ እንዲጫወቱ፣ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ፣ ጥሩ እንቅልፍ እንዲያገኙ እንዲሁም ከሌሎች ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲፈጥሩ ያስችላቸዋል፡፡ ሌላው ዋነኛው ነጥብ ደግሞ የአይንን ጤንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው፡፡

 

ከዚህ በታች እንዴት የስክሪን ብርሃን አይንን እንደሚጎዳ እናያለን፡፡

ብዙ ወላጆች የሞባይል እና ሌሎች ስክሪኖችን ለገጅም ጊዜ ማየት ጉዳት እንዳለው ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ከዚህ በታች አንዳንድ የሚጠበቂ እና አስደንጋጭ ውጤቶችን እንመለከታለን፡፡

 

1.      ብዙ ጊዜ በቤት ውስጥ መሆን እና ሩቅ ነገርን ያለማየት ችግር (Near Sightedness)

 

-         አንደኛው ችግር ስክሪን ብዙ ጊዜ መጠቀም ልጆችን ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ያደርጋቸዋል፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ የፀሐይ ብርሃን ለአይን ጤንነት አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ ልጆች ውጪ እንዲጫወቱ ማድረግ ከአካላዊ ጤናቸው ባለፈ ለአይን ጤንነትም ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡

 

-         እንዲሁም ሌሎች ጥናቶች እንዳከሉት ልጆች በቤት ውስጥ ብዙ ሲቆዩ የሩቅ ነገርን ያለማየት ችግር (Near Sightedness) ተጠቂ ይሆናሉ፡፡ ምክንያቱ በትክክል ባታወቅም የተለያዩ መላምቶች አሉ፤ ከእነዚህም ተመራማሪዎች በፀሃይ ጨረር ውስጥ ያለው ዩቪ ብርሃን ለጤናማ አይን እድገትአስፈላጊ እንደሆነ አሳይተዋል፡፡ ተያይዞም ባለፉት 30 ዓመታት የሩቅ ነገርን ያለማየት ችግር (Near Sightedness) በልጆች ላይ እጅጉን እንደጨመረ ታይቷል፡፡

 

2.      የአይን መድከም

 

-         አይናችን እረፍት ይፈልጋል፡፡ ልጆች ደግሞ አንድ ነግር ሲይዙ ቶሎ ላተዉ ስለሚችሉ ለብዙ ሰዓታት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ ትኩረት የሚፈልግ ነገር በተለይ ከስክሪን የሚወጣው ብርሃን አይንን የበለጠ ያደክማል፡፡

 

3.      የአይን መድረቅ እና መቆጣት

-         ረጀረመረ ሰዓት ስክሪን ላይ ማሳለፍ የአይን ድርቀት እና መቆጣትን ያስከትላል፡፡ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ በማንኛውም እድሜ ላይ ያሉ ሰዎች ስክሪን ላይ ሲቆዩ ትኩረታቸው ስለሚወሰድ አይናቸውም ብዙ አይከድኑም፤ ይህም የአይን መድረቅን ያመጣል፡፡ ለጥሩ እይታ አይን ላይ ቀጭን የእምባ ሽፋን በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ይህ ችግር ህፃናት ላይ ሲሆን ይብሳል ምክንያቱም የአዋቂ አይን ተብሎ የሚሰራ ስክሪን ስለሚጠቀሙ፡፡

 

4.        የአይን ትኩረትን ለመቀያየር መቸገር

 

-         አንድ ነገር ላይ ለገጅም ጊዜ አትኩሮ መቆየት እይታን አስተካክሎ ሌሎች ነገሮችን ለማየት በተለይ የርቀትእይታ ላይ ያስቸግራል፡፡ ይህ ጊዜያዊ ችግር ነው በጥቂት ሰዓታት፣ ቀናት አሊያም ሳምንታት ወደ ቀድሞ እይታ ይመለሳል፡፡

 

5.      ከእይታ በላይ እንቅልፍ ላይ ያለው ችግር

 

-         የእንቅልፍ ጊዜን መሻማት ሌላኛው ህፃናት ላይ የሚፈጥረው ችግር ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ከስልክ፣ ታብሌት፣ ኮምፒዩተር ወይም ሌሎች ባለ ስክሪን እቃዎች የሚወጣው ሰማያዊ ጨረር በተለይ ማታ ማታ መጠቀም የአእምሮን የእንቅልፍ ስርዓት ያዛባል፡፡ እነዚህን የስክሪን መብራቶች አእምሮአችን እንደ ቀን ስለሚያይ ሰውነት የእንቅልፍ ጊዜውን ይለውጣል፡፡ በተጨማሪም የቪዲዮ ጌሞች ስለሚያጓጉ ልጆች የእንቅልፍ ጊዜያቸውን መስዋት አድርገው ይቀመጣሉ፡፡

 

ምን ማድረግ አለብን?

·        ስክሪን የሚጠቀሙበትን ጊዜ መገደብ

-         ልጆች በዚህ እቅድ እንደሚመሩ ማረጋገጥ

-         ልጅዎ ውጪ እንዲጫወት ማበረታታት

-         ስልክ ወይም ታብሌት መጠቀም የማይችሉባቸውን ቦታዎች መለየት

-         በተለይ ከመኝታ በፊት መኝታ ቤት ውስጥ ስልክ እንዳይጠቀሙ ማድረግ

-         ወላጆች ለልጆች ሞዴል መሆን አለባቸው፤ እነርሱም ቢሆን ስልክ የሚጠቀሙበትን ጊዜ መገደብ አለባቸው

 

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

         የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia

 

 

 

Report Page