ዕውቀትህ ትልቅ ነው

ዕውቀትህ ትልቅ ነው


Zema 4 Christ‎ | Kebur Qen

ሁልጊዜ ፡ ሳስበው ፡ ደስ ፡ የሚለኝ ፡ ነገር

የእኔ ፡ ሁለንተና ፡ ከአንተ ፡ አልመሰወር

መንገዴን ፡ ሃሳቤን ፡ ፍለጋዬን ፡ ሁሉ

መርምረህ ፡ አወቅህ ፡ ሕይወቴን ፡ በሙሉ (፪x)


ሰዎች ፡ ስለ ፡ እኔ ፡ ሚያውቁት ፡ የተወሰነ ፡ ነው

የሚናገሩት ፡ ሁሉ ፡ ሚያዩትን ፡ ብቻ ፡ ነው

. (1) . ፡ ከአንተ ፡ ጨለማ ፡ ይሰውረኛል ፡ ብል

ሌሊት ፡ በዙሪያዬ ፡ ብርሃን ፡ ይሆናል (፪x)


ከመንፈስህ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ

ከፊትህስ ፡ ርቄ ፡ የት ፡ እሸሻለሁ (፪x)


በሁሉ ፡ ቦታ ፡ ትኖራለህ

ዕውቀትህ ፡ ለእኔ ፡ እጅግ ፡ ትልቅ ፡ ነው

ልደርስበት ፡ የማልችል ፡ ከፍ ፡ ያለ ፡ ነው (፬x)


ከመንፈስህ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ

ከፊትህስ ፡ ርቄ ፡ የት ፡ እሸሻለሁ

Report Page