ወተት መጠጣት

ወተት መጠጣት

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐


ወተት መጠጣት ለልጆች እንጂ ለአዋቂ ያን ያህል እንደማይጠቅም ይታመናል፡፡ ይህ ስህተት ነው፤ ወተት በማንኛውም እድሜ ላይ ያሉ ሰዎች አያሌ ጠቀሜታ አለው፡፡


ወተት

“በቀን አንድ ብርጭቆ ወተት!!” በብዙ ዶክተሮች የሚመከር ነው፡፡ ለዘመናት ወተት እጅግ ጤናማ ፈሳሽ ነው፡፡ በውስጡ ያለው ካልሺየም በቀላሉ በሚገኝ ሌላ የምግብ አይነት ውስጥ አይገኝም፡፡ ለሰውነት እድገት እና ጤንነት አስፈላጊ ንጥረ-ነገር ይይዛል፡፡ ወተት የማይወዱ ከሆነ እርጎ፣ አይብ እና ሌሎች የወተት ተዋጽኦ መጠቀም ይቻላል፡፡


ወተት ለምን ይጠቅማል?

1.      ካልሺየም

-         ወተት በውስጡ የሚይዘው የካልሺየም መጠን ከፍተኛ ነው፡፡ ለዚህም ነው በቀን አንድ ብርጭቆ ወተት የሚመከረው፡፡


2.      አስፈላጊ ንጥረ-ነገሮች

-         ሌሎች ንጥረ-ነገሮች እንደ ፕሮቲነተ፣ ቫይታሚን ኤ፣ ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ12፣ ዲ፣ ኮሊን፣ ፖታሺየም እና ማግኒዢየም ይይዛል፡፡


3.      ከአካላዊ እንቅስቃሴ በኋላ

-         ከአካላዊ እንቅስቃሴ በኋላ ወተት መጠጣት አቅምን እና ብርታትን ይጨምራል፡፡ እንዲሁም ለጡንቻ መጠንፈር የሚጠቅም ንጥረ-ነገርም አለው፡፡


4.      ክብደት ለመቀነስ

-         አዳዲስ ጥናቶች ወተት ውስጥ የሚገኘው ሊኖለኒክ አሲድ ስብን ለማቅለጥ ይረዳል፡፡


5.      ለጠንካራ አጥንት

-         ወተት ውስጥ ያለው ካልሺየም እና ቫይታሚን ዲ ለአጥንት ጥንካሬ እና ጤንነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሁልጊዜ ወተት መጠጣት የአይንት መሳሳትን እና ኦስቲዮአርትራይቲስን ለመከላከል ይጠቅማል፡፡


6.      በሽታ የመከላከል አቅም

-         በተለይ ወተት ላይ እርድ ጨምሮ መጠጣት በሽታ የመከላከል አቅምን በመጨመር ወቅቶች ሲቀያየሩ ለመቋቋም ይረዳል፡፡


7.      ጉንፋን እና የአፍንጫ መታፈን

-         ለጎሮሮ ቁስለት ሙቅ ወተት እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ትንሽ ኦቾሎኒ መጨመር በተለይ ለህፃናት ይጠቅማል፡፡


8.      ለውብ ቆዳ

-         ከድሮ ጀምሮ ወተት በባህላዊ መልኩ ውበትን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡ የተለያዩ የፊት ቅባቶች ከወተት ይሰራሉ፡፡ በተለይ ለፊት ጥራት ተመራጭ ነው፡፡


9.      ለፀጉር ጤንነት

-         ወተት ከሙዝ እና ከማር ጋር በመቀላቀል ፀጉርን መቀባትና ለከ15-20 ደቂቃ ማቆየት፣ መታጠብ ለደረቅ ፀጉር መፍትሔ እንደሆነ ታይቷል፡፡


10.  የደም ግፊት

-         የላም ወተት በውስጡ በሚይዘው ፖታሺየም የደም ግፊትን ያስተካክላል፡፡



ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

            ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

        የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia



Report Page