ወርኀ ጽጌ ምስጢረ ጽጌ

ወርኀ ጽጌ ምስጢረ ጽጌ

ዳረጎት ሚዲያ

ወርኀ ጽጌ ምስጢረ ጽጌ ...የአበባ ወር የአበባ ምስጢር

ኹላችንም እንደምናውቀው ከመስከረም ፳፮ እስከ ኀዳር ፮ ድረስ ያለው ወቅት በአንድ በኩል አበቦች ጌጠኛ ሸማ ሆነውላት በልብስነታቸው ምድር የምትደምቅበት ጊዜ በመሆኑ በሌላ በኩል ድንግል ማርያም ፲፰ ዓመት እንኳ በቅጡ ባልደፈነው የአበባነት እድሜዋ ከሄሮድስ ጥፋት ለመሸሽ ልጇን አዝላ ተሸክማ፣ ወደ ግብጽ የተሰደደችበት በረሃ ለበረሃ የተንከራተተችበት ‹‹በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል›› ያሰኘ ወደር የሌለው ጽዋትወ መከራን በልጇ የተነሳ የተቀበለችበት ወቅት በመሆኑ ወርኀ ጽጌ (የአበባ ወቅት) በመባል ይታወቃል፡፡ 

ክርስቲያኖች ነገረ ስደቷን በመዘከር ማኀሌተ ጽጌን በመቆም በመጾም በመፀለይ የበረከት ፍሬ ለቃሚ በዚያን ጊዜ የሆነውን ስቃይ ኀሳር ለልጇና ለወዳጇ ለኢየሱስ ክርስቶስ አሳስባ ምሕረት እንድታሰጣቸው በመለመን የምልጃዋ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

ክርስቲያኖች ነገረ ስደቷን በመዘከር ማኀሌተ ጽጌን በመቆም በመጾም በመፀለይ የበረከት ፍሬ ለቃሚ በዚያን ጊዜ የሆነውን ስቃይ ኀሳር ለልጇና ለወዳጇ ለኢየሱስ ክርስቶስ አሳስባ ምሕረት እንድታሰጣቸው በመለመን የምልጃዋ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ በዚህ ወቅት ከዚህ በተጨማሪ በወርኀ ጽጌ ጊዜያቸውን የጠበቁ እንዲሁም ሰፊና ጥልቅ መንፈሳዊ ምስጢርን ያዘሉ ትምህርቶች ይሰጣሉ፡፡ ጊዜው የልም ላሜና የአበባ ወቅት እንደመሆኑ ስለ አበባና ስለ መንፈሳዊ ምስጢሩ ይነገራል፡፡ 

ይኽ የሆነው ቤተክርስቲያናችን የሥርዓት ባለቤት(1ቆሮ14፡40) በመሆኗ ከወቅቱ ጋር ተስማሚ የሆኑ ስብከቶች ለምዕመናን እንዲሰጡ ስለምታዝ ነው፡፡ በዓለማዊ ትምህርት ምንም እንኳ ኮርሶች ቅደም ተከተል የሚሰጡት የጊዜ ሰሌዳ ቢኖራቸውም ቦታቸው ተቀያይሮ ብንማራቸው ያን ያኽል የጎላ ችግር አያስከትሉም፡፡ በቤተክርስቲያን ግን ያለ ጊዜው አንድ ትምህርት ቢሰጥ ‹‹ምን አመጣው?›› ያሰኛል፡፡ 

ለኸሉ ጊዜ አለውና የክረምቱን ለክረምቱ የበጋውን በበጋው ነው እንጂ ደመና በዞረ ቁጥር ስለ ክረምት ፀሐይ በከረረ ቁጥር ስለሙቀት አይነገርም፡፡ ይሄን ያልኩት ምናልባት በተለያየ ዓመታት በዚሁ ተመሳሳይ ወቅት እንዲህ ያለ ወጥ ትምህርት ሲሰጥ የስብከት አጀንዳዎች አናሳ ስለሆኑ ሳይሆን ከላይ በተጠቀሰው መሠረተ ሐሳብ ምክኒያት መሆኑን እንድናስተውል ነው፡፡ ርዕሳችን ምስጢረ ጽጌ በመሆኑ ምስጢራዊ ቁምነገሩ ላይ በማተኮር ስለ አበባ እንነጋገራለን፡፡

ለምን ተፈጠረ?

ፈጣሬ ዓለማት ገባሬ መንክራት ልዑል እግዚአብሔር ፳፪ቱን ስነ ፍጥረት በልዩ አምላካዊ ጥበብ ሲፈጥር ኹለቱን ፍጥረታት ሰውና መላእክትን አእምሮና አንደበት ሰጥቶ አንዲያመሰግኑት የተቀሩት ፍጥረታት ለምክርና ለተግሣፅ ለአንክሮ ለተዘክሮ ለምግበ ሥጋ ለምግበ ነፍስ ሆነውላቸው ‹‹ራሱን ያለምሥክር አልተወም›› ሐዋ ፲፬፡፲፯ ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራው ማሳያ የአምላክነቱ ምስክር ሆነው እንዲያመሰግኑት ተፈጥረዋል፡፡ 

ከእነዚህ ውስጥ አንዱ አባባ ነው፡፡ አበባ በእለተ ማክሰኞ እግዚአብሔር ‹‹ታብቊል/ታብቅል›› ባለው አምላካዊ ቃል መሠረት ምድር ከልምላሜ፤ ከዘር፤ ከፍሬ ጋር በእጅ የሚለቀሙ አትከልትና ፍራፍሬ፣ በማጭድ የሚታጨዱ ሰብሎችንና በምሣር የሚቆረጡ እፅዋትን ስታስገኝ አብሮ የተፈጠረ ዕፅ ነው፡፡ አበቦች የተመለከትናቸው አንደሆነ መልካቸውን ብቻ ማየት ብዙ መንፈሳዊ ቁምነገሮችን ሊያስተምሩን የሚችሉ መምህራን ናቸው፡፡ 

ጌታችንም ኹለት ማይል ያኽል ከፍታ ባለው ተራራ ቆሞ ባስተማረው የተራራው ስብከቱ ስለ መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸው ከመጠን በላይ እንዳያስቡ ‹‹ምን እንበላለን›› ብለው እንዳይጨነቁ በነገራቸው ጊዜ ‹‹ርዕዩ ጽጌታተ ገዳም…የምድር አበቦችን…ተመልከቱ›› ማቴ ፮፡፳፰ በማለት ‹‹ከአንተ በፊት ከአንተም በኋላ እንዳይነሳ አድርጌ ሀብትን እሰጥሃለሁ›› ተብሎ በእግዚአብሔር የተመሠከረለት ሰሎሞን እንኳ ከባህርይው ያይደለ  አውልቆ የሚያስቀምጠው የክብር ልብስ ቢኖረው እንጂ እንደ አበቦች ያልተደከመበት ከፈጣሪ የተለገሰ የባህርይ ልብስ እንደሌለውና አበቦች ሳይፈትሉ ሳይጎለጉሉ እንዲሁ የተቸራቸውን የውበት ልብስ ሊያዩ ስለ ልብስ እላፊ ከመጨነቅ መከልከል እንዳለባቸው አበቦችን ማሳያ አድረጎ በስፋት አስተምሯቸዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም የቆሮንቶስን ምዕመናን በገሠፀበት አንቀጹ ‹‹ተፈጥሮስ እንኳ አያስተምራችሁ ምን?›› በማለት ተናግሯል፡፡

የአበባ መንፈሳዊ ምስጢርና ምሣሌነት 

ይቆየን!

Report Page