ካሮት

ካሮት

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐


ካሮት ለእይታ እንደሚጠቅም በሁሉም ዘንድ ሲነገር እንሰማለን፡፡ ዛሬ ካሮትን የመመገብ ጥቅምን ጥናቶችን በመጠቆም እናያለን፡፡


ካሮት

ከጣፋጭ ጣዕሙ ባሻገር ካሮት በቤታ ካሮቲን፣ ቫታሚን፣ ሚነራል እና አንታኦክሲዳንት የበለጸገ ነው፡፡


የጥናት የተረጋገጡ የካሮት የጤና ጥቅሞች፤


1.      ካሮት ለተሸለ እይታ

-         ጥናቶች እንደሚያሳዩት ካሮት ውስጥ ያለው ሉቲን እና ላዮኮፔን የተባሉ ንጥረ-ነገሮች እይታን ከመጠበቅ ባሻገር በምሽት ጊዜ ለማየት ይጠቅማል፡፡


2.      ካሮት ለተሸለ በሽታ የመከላከል አቅም

-         ካሮት በውስጡ የተለያዩ ንጥረ-ነገሮች እንደ ቫይታሚን ሲ፣ አንታይኦክሲዳንት ይይዛል፤ ይህም የሰውነትን መከላከል አቅም ይጨምራል፡፡ ሁልጊዜ ካሮት መመገብ ሰውነትን ከበሽታ አምጪ ተዋህሲያን ይጠብቃል፡፡


3.      ካሮት ክብደት ለመቀነስ

-         ክብደት ለመቀነስ ካሰቡ ምግቦ ውስጥ በፋይበር የበለፀጉ የምግብ አይነቶችን ማካተት ያስፈልጋል፡፡ ካሮት የሚዚው የፋይበር መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ለዚህ ይጠቅማል፡፡


4.      ካሮት የምግብ መፈጨት ለማስተካከል

-         በፋይበር የበለፀገ በመሆኑ የስነ-ልመት ስርዓትነ ለማሳለጥ ይጠቅማል፡፡ ድርቀትንም ይከላከላል፡፡


5.      ካሮት ኮሌስትሮልን ለመከላከል እና የልብን ጤንነት ለመጠበቅ

-         አሁንም በፋይበር ይዘቱ ምክንያት የበዛ መጥፎ ኮሌስትሮልን ለመቀነስ ይጠቅማል፡፡ ተያይዞም የልብን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል፡፡


6.      ካሮት የደም ግፊትን ለመቀነስ

-         መጥፎ ኮሌስትሮልን ከመቀነስ ጋር ተያይዞ ካሮት በፖታሺየም የበለፀገ ነው፡፡ ፖታሺየም በደም ስሮች ውስጥ ያለውን ውጥረት በመቀነስ የደም ዝውውርን ያስተካክላል፤ ተያይዞም ግፊትን ይቀንሳል፡፡


7.      ካሮት ለጤናማ ፀጉር

-         አንደኛውና ዋነኛው የካሮት ጥቅም ጠፀጉርን ጤንነት መጠበቅ ነው፡፡ ለፀጉር አስፈላጊ የሆነውን  ቫይታሚን በማድረስ ፀጉርን ጠንካራ፣ ወፍራም እና የሚምር ያደርገዋል፡፡


8.      ካሮት ለሚያበራ ቆዳ

-         ካሮት ዘወትር መጠቀም ቆዳን የሚያምር ያደርጋል፡፡ ካሮትን ብርቱካናማ ቀለም የሰጠው ቤታ ካሮቲን ቆዳን በማፍካት ውበትን ያጎናፅፋል፡፡


9.      ካሮት የቆዳ መጠማደድን ለመከላከል

-         ካሮት ውስጥ የሚገኘው ቤታ ካሮቲን ሰውነታችን ውስጥ ሲገባ ወደ ቫይታሚን ኤ ይለወጣል፡፡ ቫይታሚን ኤ የቆዳን ልስላሴ እና ጤንነት ይጠብቃል፡፡  


10.  ካሮት ለጤናማ ጥርስ

-         ካሮት የጥርስን መቦርቦር የሚከላከል አትክልት ነው፡፡ ጥሬ ካሮት ማኘክ እንደ በተፈጥሮአዊ መንገድ ጥርስን መቦረሽ ይቆጠራል፡፡


11.  ካሮት ቆዳን ልስላሴ ለመጠበቅ

-         ቆዳዎ ደረቅ ከሆነ ካሮት ሁነኛ መፍትሔ ነው፤ ምክንያቱም በፖታሺየም የበለፀገ ስለሆነ፡፡ የካሮት ጁስ መጠጣት ሰውነትን እና ቆዳን የውሃ መጠን ያስተካክላል፡፡ ዕንዲሁም ከካሮት የተሰሩ የቆዳ ውጤቶች ጠቃሚ ናቸው፡፡


12.  ካሮት የቆዳን ጠባሳ ለመቀነስ

-         በተለያዩ ምክንያቶች ቆዳ ላይ የሚቀረውን ጠባሳ ለመቀነስ እንደሚረዳ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ጁሱን ወይም የቆዳ ክሬሙን መጠቀም ይቻላል፡፡


13.  ካሮት ቆዳን ከፀሃይ ለመከላከል

-         ካሮት ቆዳን ከፀሃይ ጨረር ይከላከላል፡፡ ሰውነት ውስጥ ሲገባ ወደ ቫይታሚን ኤ የሚለወጠው ቤታ ካሮቲን ለቆዳ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የሞቱ የቆዳ ሴሎችን ይጠግናል፤ እንዲሁም ቆዳን ከጨረር ጥቃት ይከላከላል፡፡



ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

         የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia




Report Page