ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸው የለስላሳ መጠጦች

ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸው የለስላሳ መጠጦች

Dr. Tena - Bethel

 

 




🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!!  🖐🖐🖐


ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸው መጠጦች በአብዛኞች ሲዘወተሩ እናያለን፡፡ እነዚህ መጠጦች ጤና ላይ ከግተኛ ተጽዕኖ ስላላቸው ባይወሰዱ ይመከራሉ፡፡ ዛሬ እነዚህ የለስላሳ መጠጦች በምን መልኩ ጤናችንን ሊያውኩ እንደሚችሉ እናያለን፡፡


 

ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸው የለስላሳ መጠጦች ጤናን እነዴት ያውካሉ?


ከመጠን በላይ ከተወሰደ ስኳር ጤና ላይ ተፅዕኖ ሊፈጥር ይችላል፡፡ አንዳንድ የስኳር አይነቶች ደግሞ የባሰ ሊጎዱ ይችላሉ፤ እናም የለስላሳ መጠጦች ውስጥ ያለው የስኳር አይነት ከሚያመጣው የጤና ችግር አንፃር በጣም መጥፎ የሚባል ነው፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጤና ላይ ሊያመጣ የሚችለውን ችግር በቀጣይ እናያለን፡፡


1.     የለስላሳ መጠጦች ስለማያጠግቡ ክብደት ከመጨመር ጋር ሊያያዙ ይችላሉ


2.     ጉበት ከፍተኛ የስኳር መጠንን ወደ ስብ ይለውጣል


3.     ስኳር ቦርጭ ያመጣል


4.     የለስላሳ መጠጥን በብዛት መውሰድ ለስኳር በሽታ ያጋልጣል


5.     የለስላሳ መጠጦች ከስኳር በቀር ምንም አይነት ጠቃሚ ንጥረ-ነገር አይዙም


6.     ስኳር የምግብ ልመት ሂደትን ሊያዛባ ይችላል


7.     የለስላሳ መጠጦች ሱስ ያስይዛሉ


8.     ስኳር የበዛባቸው መጠጦች ለልብ በሽታ ተጋላጭነትን ይጨምራሉ


9.     በካንሰር የመያዝ እድልን ይጨምራሉ


10. በለስላሳ መጠጦች ውስጥ ያለው ስኳር እና አሲድ ለጥርስ እና አፍ ጤንነት እና ንፅህና ጠንቅ ነው


11. ለሪህ በሽ ተጋላጭነትን ከፍ ያደርጋል


12. ከመርሳት በሽታ ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ይነገራል


 በመሆኑም የስኳር መጠናቸው ከፍ ያሉ የለስላሳ መጠጦች ጤናን በብዙ መልኩ ያውካሉ፡፡ ከጥርስ መበስበስ እስከ ለልብ እና ስኳር በሽታ መጋለጥ ድረስ በተለያየ መልኩ ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፣ እነዚህን መጠጦች በመቀነስ ከተቻለም ባለመውሰድ ጤናማ ህይወትን እንምራ!!


  ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!


   ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

       የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

        የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia

Report Page