እግርህን ልጠብህ

እግርህን ልጠብህ

Solicious18 Wallpapers™
ተመስገን አበራ | እግርህን ልጠብህ

የምትናፈቅ የክረምቷ ጸሀይ

ሙቀቷን ፍትረት ፈልጎ ሰማይ ሰማይ ሲያይ

ብትወጣ ጭጋጉን አልፋ

ብትቀር በደመና ተውጣ

ሕይወት አይቀርም ኡደቱ

በቀዝቃዛው አየር ዙረቱ


አማራጭ የሌላት ነፍሴ ግን

ሺህ ጸሐይ ቢወጣ አይሞቃትም

አሀ አህ ሀ ሀ

ውበቷ ክብሯ አንተ ነህ

ከእልፍ አእላፋት መካከል

አንድም ክብር የለም


ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ

ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ

ነፍሴ ገሰገሰች አንተን አንተን አለች

ነፍሴ ገሰገሰች አንተን አንተን አለች

ነፍሴ ገሰገሰች አንተን አንተን አለች


አትሂድ ከደጄ ወዳጄ ቤቴ ግባ

ወዳጄ በቤቴ ግባ

እግርህን ልጠብህ እባክህ አረፍ በልና

ወዳጄ በቤቴ ግባ

እንግዶች ልሸኝ ገፍተው ከእልፍኝ ያራቁህን

ገፍተው ከእልፍኝ ያራቁህን

ደምቀህ እንዳትታይ በምክር የሚያቀልሉህን

በምክር የሚያቀልሉህን


አሀ አሀ ደጆች ይከፈቱ

አሀ አሀ የክብር ንጉስ ይግባ

አሀ አሀ ይህ የክብር ንጉስ ማነው?

አሀ አሀ የጭፍሮች አምላክ እግዚአብሔር ነው


ያለ አንተ አይሆንልኝም ወዳጄ

ኧረ እንዴት ይሆንልኛል አንተን ገፍቼ

ኑርና ልኑር በሕይወት 

ስትኖር ነው ኖርኩኝ ማለት

ከእኔ መኖር ይልቅ ይሻላል

ሰው ብቻውን ምን ይፈይዳል?


ያለ እኔ መኖር የምትችል

ከአንተ ውጪ መኖር የማልችል

አሀ አህ ሀ ሀ 

ስለሆንኩ አትውሰድብኝ 

እሳቱን ከመቅረዙ ላይ

ዘውትር ይንደድልኝ


ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ

ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደምትናፍቅ

ነፍሴ ገሰገሰች አንተን አንተን አለች

ነፍሴ ገሰገሰች አንተን አንተን አለች

ነፍሴ ገሰገሰች አንተን አንተን አለች


ሰው እንደሚኖረው ለመኖር ተመሳስዬ

ለመኖር ተመሳስዬ

አልቻልኩም በእንጀራ ለመዝለቅ ነፍሴን አታልዬ

ለመዝለቅ ነፍሴን አታልዬ

የትም እንደማልደርስ ገብቶኛል በእኔ እሩጫ

ገብቶኛል በእኔ እሩጫ

እግሬን በፈቃድህ እሰረው እስከ መጨረሻ

እሰረው እስከ መጨረሻ


አሀ አሀ ደጆች ይከፈቱ

አሀ አሀ የክብር ንጉስ ይግባ

አሀ አሀ ይህ የክብር ንጉስ ማነው?

አሀ አሀ የጭፍሮች አምላክ እግዚአብሔር ነው


ተመስገን አበራ | እግርህን ልጠብህ

💌 Bethel Daniel


ተመስገን አበራ | እግርህን ልጠብህ Lyric Video


Report Page