እንደሰው

እንደሰው

hana tekle


ያየናል የማያይ ሲመስል

ይሰማናል በብርቱ ዝም ሲል

አለ የሚረዳን በዙፋኑ

ሚደርስልን በማዳኑ ×2


በድካማችን ሚራራልን

የማይስቅ በውድቀታችን

በሃዘናችን የሚያፅናናን

ኢየሱስ አለ ሚያበረታን


በህመማችን ሚራራልን

የማይስቅ በውድቀታችን

በሃዘናችን የሚያፅናናን

ኢየሱስ አለ ሚያበረታን


እርሱ እራሱ እንደ ሰው ተፈትኖ

ብዙ አልፎበታል ሰውን ሆኖ

ከሃጢአት በቀር ብዙ ሆኖል

የምናልፍበት ይገባዋል


እርሱ እራሱ እንደ ሰው ተፈትኖ

ብዙ አልፎበታል እኛን ሆኖ

ከሃጢአት በቀር ብዙ ሆኖል

የምናልፍበት ይገባዋል


ይራራልናል ያስብልናል

በጊዜው ሰርቶ ደግሞም ያስቀናል

ይመጣል ነገ ዛሬም ያልቅና

ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናትና

ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና

ባዲስ ዝማሬ ባዲሱ ዜማ ×2


በጊዜው በሚያልፍ መከራ

ብናልፍም ተራ በተራ

የማይጥል ጌታን ይዘናል

ልባችን በእርሱ ይፅናናል


በፀጋው ስንቱን ተወተናል

በወጀብ ሰላም ሆነናል

ያልተወን ጌታ ይመስገን

በረፍቱ ከቦ የያዘን


ምንም ብናዝን በዚህ አለም ፈተና

አይለወጥም ለእርሱ ያለን ምስጋና

በመስቀሉ ያለፈውን እያየን

በእምነታችን ዛሬም እንጸናለን


ይራራልናል ያስብልናል

በጊዜው ሰርቶ ደግሞም ያስቀናል

ይመጣል ነገ ዛሬም ያልቅና

ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናትና

ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና

ባዲስ ዝማሬ ባዲሱ ዜማ ×2


ፃድቅ ጌታ እንደ ሰው ተፈትኖ

ብዙ አልፎበታል ሁሉን ሆኖ

ከሃጢአት በቀር ብዙ ሆኗል

ምናልፍበት ይገባዋል


ይራራልናል ያስብልናል

በጊዜው ሰርቶ ደግሞም ያስቀናል

ይመጣል ነገ ዛሬም ያልቅና

ደግሞ እንስቃለን ቆመን በትናትና

ደግሞ እንቆማለን በአዲስ ምስጋና

ባዲስ ዝማሬ ባዲሱ ዜማ ×2

Report Page