አይ ዘንድሮ
Blessing Frequency Gospel Reggae BandTelegram @protestant_albums
አይ ዘንድሮ የሰው ልጅ ቃል
አንደበቱ በሃሰት ታጭቋል
መንታ ምላስ ሆኖ ነገሩ
ማይገናኝ ስራ አኗኗሩ
አመፀኛዋ አለም
ስንቱን ጎድታው አትቀርም
አይ ዘንድሮ የሰው ልጅ ቃል
አንደበቱ በሃሰት ታጭቋል
የቃል አባዩ ቃላት ከንቱ
ሸምበቆ ታምኖ ስንቱ ወጋ ነፍሱን
ሁለት ፍሬ ከአንዱ ቅርንጫፍ
ዛሬ ቀርቦ ነገ ይሸሽሃል
ግራ እና ቀኝ ስታማትር
ስትፈልግ ሚሆን ምርኩዝ
አይ ዘንድሮ የሰው ልጅ ቃል
አንደበቱ በሃሰት ታጭቋል
ጥሩት ያልከው ገሸሽ ሲል
ሚያጅብ ጠፍቶ አልፎ ሄደ ትቶ
ሁለት ፍሬ ከአንዱ ቅርንጫፍ
ዛሬ ቀርቦ ነገ ይሸሽሃል
አይ ዘንድሮ የሰው ልጅ ቃል
አንደበቱ በሃሰት ታጭቋል
መንታ ምላስ ሆኖ ነገሩ
ማይገናኝ ስራ አኗኗሩ
እንደ ሸክላ ሰውሮ አዘናግቶ ግን ይይዛል
የአመፀኞች ሽንገላ ቃል ከወጥመድ ይበልጣል
ውብ ቃላቸው ፍላፃ ነው ያሳምማል አንዴ ወጥቶ
በአምላኬ ቃል ካልታከመ ስንቱ ወድቋል ተሰውቶ
ማን እንደ ጌታ ማን እንደ ኢየሱስ
ጊዜ ቢለወጥ የማይለወጥ (4)
አይ ዘንድሮ የሰው ልጅ ቃል
አንደበቱ በሃሰት ታጭቋል
መንታ ምላስ ሆኖ ነገሩ
ማይገናኝ ስራ አኗኗሩ
Telegram @protestant_albums