አልተጋነነም

አልተጋነነም

Tekeste Getnet

Telegram @protestant_albums

 

አልተጋነነም የእስካሁኑ

የተነገረው በየቀኑ

አትጨረስም ተብራርተህ

ከተባለልህ በላይ ነህ


ትልቅ ከሁሉም ይልቅ

ማንንም ደግሞ የማይንቅ

አለ በማደሪያው/ በሰማያት አለ

ቸርነቱ ያልተጓደለ


አማኝ አልሻም ማጋነኛ

ታላቅነትህን ለማስረጃ

አይቸዋለው በህይወቴ

ማእረጌ ሆነህ ገብተህ እቤቴ


የቱ ተነግሮ የቱ ይተዋል

ስራህ ልዩ ነው ከአይምሮ ያልፋል

የጠቢብ ጥበብ ያዋቂው

አንተን አይገልጥህ ተራኪው


ትልቅ ከሁሉም ይልቅ

ማንንም ደግሞ የማይንቅ

አለ በማደሪያው/ በሰማያት አለ

ቸርነቱ ያልተጓደለ


ከሚገርመኝ ከሚደንቀኝ ነገር አንዱ

እግዚአብሄር እኔን መውደዱ

እግዚአብሔር እኔን መውደዱ

እግዚአብሔር ሰውን መውደዱ

እግዚአብሔር ትንሹን መውደዱ

 

ከሚገርመኝ ከሚደንቀኝ ነገር አንዱ

እግዚአብሔር ደሃውን መውደዱ

እግዚአብሔር እኔን መውደዱ

እግዚአብሔር ሰውን መውደዱ

እግዚአብሔር እኔን መውደዱ

Telegram @protestant_albums

Report Page