አለኝ ያለ

አለኝ ያለ

Solicious18 Wallpapers™
ሶሬቲ ሞገስ | አለኝ ያለ

ግርግሩ በዝቷል በዝቷል በመንገዱ

ሁሉ ይሰለፋል እንደ አመጣጡ

ተራው የደረሰው ወጥቶ በተራው ይቆማል

ኃብት ንብረቱን ሁሉን ያስቆጥራል


እኔም በተራዬ በአደባባዩ ላይ

ቆምኩኝ በሕዝቡ ፊት ያለኝ ላሳይ

ከቶ ዝም አልልም ስሙኝ አወራለሁ

አለኝ ያለ ሁሉ ምንም እንደሌለው


የለውም አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ

ደኃ እርሱ ነው አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ


የለውም አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ

ደኃ እርሱ ነው አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ


እያለው የሌለው ፍጹም የከሰረ

ጥሮ ግሮ ለፍቶ ባዶ እጁን የቀረ

ዓለምን አትርፎ ከሕይወት የጎደለው

እንደምን ተጎዳ እርሱ ሰው ምስኪን ነው


የለውም አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ

ደኃ እርሱ ነው አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ


የለውም አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ

ደኃ እርሱ ነው አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ


በንዋይ በገንዘብ ሰው እንዴት ይመካል

የሕይወትስ ጌታ በምን ዕንቁ ይተካል

ሊሰማ ለሚወድ አንድ እውነት ይኼ ነው

ከክርስቶስ ውጪ ሙሉነት ባዶ ነው


የለውም አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ

ደኃ እርሱ ነው አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ


የለውም አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ

ደኃ እርሱ ነው አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ


ኃብት ቢሆን ብልጽግና

ያለውና ሚመጣው ገና

ረብ የሌለው እንደ ጉድፍ ነው

ጌታን ከማወቅ አላስተያየው


የለውም አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ

ደኃ እርሱ ነው አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ


የለውም አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ

ደኃ እርሱ ነው አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ


የለውም አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ

ደኃ እርሱ ነው አለኝ ያለ ከኢየሱስ የጎደለ


ሶሬቲ ሞገስ | አለኝ ያለ


"ካሰነበትከኝ" ከተሰኘው የመዝሙር ሰንዱቅ የተወሰደ












































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































































Report Page