ተአምረኛው ፌጦ

ተአምረኛው ፌጦ

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

ለብዙ ችግሮች ሁነኛ መድሐኒት ስለሆነው ፌጦ እናወራለን፡፡ ስለፌጦ  ጥቅም የማያቅ ባይኖርም ሰብሰብ አድርገን ይዘን ቀርበናል፡፡

 

የፌጦ የጤና ጥቅሞች

ፌጦ (Lapidium sativum) በርካታ በሽታዎችን በመቀነስ ረገድ ትልቅ ድርሻ አለው። በሃበሻ አባባልም "ለሁሉም ፌጦ መድሃኒት ነው" እንል የለ። ለማንኛውም ይህችን ታነቡ ዘንድ ጋበዝን።

1.     ለመተንፈሻ አካል ችግር

-         ለጉንፋን፣ አስም፣ ሳል፣ ራስ ምታት፣ ለጉሮሮ ቁስል ሁለት ማንኪያ ፌጦ ፈጨት አድርገው ከማር ጋር በመለወስ ይዋጡት፡፡

 

2.     በብረት (iron) ማነስ ምክንያት የሚከሰትን አኒሚያ የተሰኘ በሽታን ለማቃለል

-         ከፍተኛ የብረት ማዕድን የያዘው ፌጦ በአንጀታችን ውስጥ በቀላሉ ስለሚመጠጥ በደም ውስጥ የሚገኘውን የሂሞግሎቢን መጠን ይጨምራል፡፡

 

3.     የቆዳ ችግርን ለማስተካከል

-         በፀሐይ የተቃጠለ ቆዳ፣ የተቆጣ ቆዳ፣ ደረቅ ቆዳ ካሎት የተፈጨ ፌጦ ከማር ጋር ቀላቅለው ይቀቡት ችግሩን ለማባረር ይረዳዎታል፡፡

 

4.     ለአንጀትና ለሆድ ዕቃ ሕክምና

-         ለተቅማጥ፣ ለሆድ ድርቀት እና ለምግብ ያለመንሸራሸር ወይም የመፈጨት ችግር ሁነኛ መፍትሔ ነው፡፡ በተላይ የፌጦ ፍትፍት ምርጥ ነው፡፡

 

5.     ደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን ያጠናክራል

-         ጠቃሚ የሆኑ የተለያዩ አሲዶችን ማለትም ፋቲ አሲድ፣ አስፓርቲክ አሲድ፣ ግሉታሚክ አሲድ፣ ሊኖሊክ አሲድ፣ ኦሊክ አሲድ፣ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ ያሉት በመሆኑ ደም ግፊትን ይቀንሳል፣ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅምን ያጠናክራል፣ የደም ስኳር መጠንን ይቀንሳል፣ ለአእምሮ እና የልብ ጤናን ከመጠበቅ በተጨማሪ ድባቴንና ጭንቀት አዲዮስ ያሰኛል፡፡

 

6.     በአየርና በኬሚካል ሳቢያ የሚከሰትን የካንሰር ዓይነት ነጥሎ ይዋጋል

-         ፀረ-ብግነት እና ቫይታሚን ኢ ስለያዘ በአየርና በኬሚካል ሳቢያ የሚከሰትን የካንሰር ዓይነት ነጥሎ ይዋጋል፡፡ የሕዋሳትን ውድመት በመከላከሉም ያለዕድሜ ማርጀትን ይከላከላል፡፡

 

7.     የወር አበባ አመጣጥን ያስተካክላል

-         ፌጦ የወር አበባ አመጣጥን ያስተካክላል፡፡ እንዲሁም ለምታጠባ እናት የጡት ወተቷን ይጨምራል፡፡


8.     የፀጉር መነቀልን ይከላከላል

-         መጥፎ የሰውነትን ጠረን ከማስወገዱ በተጨማሪ የፀጉር መነቀልን ይከላከላል፡፡


9.     የአይን ጤንና ያሻሽላል

 

ምን ያህል መወሰድ እንዳለበት በሳይንስ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም የመድሐኒት ያህል በትንሹ ብቻ መጠቀም ይመከራል፡፡

ምንጭ - ኢትዮ-ሳይንስ

 

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

         የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia

 

Report Page