ተሻገሩ ፡ ብሎ (Teshageru Belo) - ታምራት ፡ ሃይሌ

ተሻገሩ ፡ ብሎ (Teshageru Belo) - ታምራት ፡ ሃይሌ

 Tamrat Haile‎ | Bedebebeqosh Qenu Endayalf


ተሻገሩ ፡ ብሎ ፡ አዞ ፡ በውኃ ፡ ሚያስበላ

ኧረ ፡ እስቲ ፡ ንገሩኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ይሆን ፡ ወይስ ፡ ሌላ

መፈጸም ፡ አቅቶት ፡ ከአፉ ፡ የወጣውን ፡ ቃል

ይቅርታ ፡ ጠይቆ ፡ ወይ ፡ ረዳት ፡ ፈልጐ ፡ እርሱ ፡ መች ፡ ያውቃል

ይሄ ፡ ግን ፡ የማውቀው ፡ ጀምሮ ፡ ፈጻሚ

ጠላት ፡ የመጣ ፡ እንደው ፡ እራሱን ፡ አስቀዳሚ

እነርሱን ፡ ተዉአቸው ፡ እኔን ፡ ያዙኝ ፡ የሚል

ከአውሬም ፡ መንጋጋ ፡ በጐቹን ፡ የሚያስጥል


አዝ፦ አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው

ድጋፍ ፡ ምሶሶዬ ፡ ማነው

አለኝታ ፡ ጋሻዬ ፡ ማነው

መከታ ፡ አንባዬ ፡ ማነው

ማነው (፫x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው


ለአብርሃም ፡ ተናግሮ ፡ ነግሮ ፡ ለይሳቅ ፡ አጸና

ለይሳቅ ፡ ተናግሮ ፡ ለያቆብ ፡ ፈጸመ ፡ እርሱ ፡ አይዋሽምና

ዮሴፍ ፡ በግብጽ ፡ ምድር ፡ ቢወርድ ፡ ቢገባም ፡ ተሽጦ

የፈርዖን ፡ መንግሥት ፡ ገዢ ፡ አደረገው ፡ ስርአት ፡ ለውጦ

እግዚአብሔር ፡ ደክሟል ፡ አረጀ ፡ ያለ ፡ ማነው

እኔስ ፡ እስከሚገባኝ ፡ ዛሬም ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው

የእኔ ፡ እምነት ፡ ቢፈተን ፡ ቢለዋወጥበት

እግዚአብሔር ፡ ግን ፡ ታምኖ ፡ አለ ፡ እዚያው ፡ ባለበት


አዝ፦ አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው

ድጋፍ ፡ ምሶሶዬ ፡ ማነው

አለኝታ ፡ ጋሻዬ ፡ ማነው

መከታ ፡ አንባዬ ፡ ማነው

ማነው (፫x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው


በልዑል ፡ መጠጊያ ፡ አንባ ፡ መሽጐ ፡ ሚኖር

ሁሉንም ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ያድራል ፡ ከቶ ፡ አይሸበርም

ከአዳኞች ፡ ወጥመድ ፡ ከሚያስደነግጥም ፡ ነገር

ከክፉ ፡ ከልሎ ፡ ይታደገው ፡ የለ ፡ ሕያው ፡ እግዚአብሔር

የቀኑ ፡ ፍላጻ ፡ የሌሊቱ ፡ ግርማ ፡ አደጋና ፡ ጋኔል ፡ ተጓዥ ፡ በጨለማ

ሺ ፡ በሺ ፡ ሲያረግፈው ፡ ሲያስረግጠኝ ፡ ኖርኩኝ

እኔም ፡ ከእርሱ ፡ በታች ፡ መቀጥቀጥ ፡ ተማርኩኝ


አዝ፦ አሁንስ ፡ ተስፋዬ ፡ ማነው (ጌታ ፡ ነው)

ድጋፍ ፡ ምሶሶዬ ፡ ማነው (ጌታ)

አለኝታ ፡ ጋሻዬ ፡ ማነው (ጌታ ፡ ነው)

መከታ ፡ አንባዬ ፡ ማነው (ጌታ ፡ ጌታ ፡ ጌታ)

ማነው (፫x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

ማነው (፫x) ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው

Report Page