ብሮንካይተስ (Bronchitis)

ብሮንካይተስ (Bronchitis)

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

የብሮንካቲስ በሽታ ከአየር ቧንቧ መቆጣት ጋር ይያያዛል፡፡ ብዙ ጊዜ ቸል ተብሎ የከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ ይችላል፡፡ ለግንዛቤ እንዲሁም መቼ ወደ ጤና ተቋም መሄድ እንዳለብን እናያለን፡፡

 

ብሮንካይተስ (Bronchitis) ምንድነው?

አየርን ወደ ሳምባ የሚወስደው የአየር ቧንቧ (Bronchial tubes) መቆጣት ብሮንካይተስ (Bronchitis) ይባላል፡፡ በሽታው ያለባቸው ሰዎች በአብዛኛው ወፍራም አክታ ያለው ሳል አላቸው፡፡ ብሮንካይተስ አብሮ ለረጅም ጊዜ ሊኖር ወይም በሳምንታት ሊሻል ይችላል፡፡

 

በጥቂት ቀናት (በአማካይ 10 ቀናት አንዳንዴም ሳምንታት) የሚሻለው የብሮንካይተስ አይነት (አኪዩት ብሮንካይተስ) ብዙውን ጊዜ ከጉንፋን ወይም ሌሎች ቀላል የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሺን የሚመጣ ነው፤ የሚቆይ የጤና እክል ባያመጣም ሳሉ ሊሰነብት ይችላል፡፡ አብሮ የሚኖረው የብሮንካይተስ አይነት (ክሮኒክ ብሮንካይተስ)ግን በከፋ ሁኔታ ጤናን ሊያውክ ይችላል፤ ይህም በቋሚነት የአየር ቧንቧ መቆጣት ያስከትላል፤ ሲጃራ ማጨስ ዋነኛው መንስኤ ነው፡፡

 

በብሮንካይተስ በተደጋጋሚ የሚጠቁ ከሆነ ህክምና ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

 

ምልክቶች

-         ሳል

-         አክታ

-         ድካም

-         ትንፋሽ ማጠር

-         ትኩሳት ወይም ብርድ ብርድ ማለት

-         ደረት ላይ አለመመቸት

 

በምን ምክንያት ይመጣል?

·        አኪዩት ብሮንካይተስ ብዙውን ጊዜ ጉንፋን በሚመጣ ቫይረስ አማካኝነት ይመጣል፤ አንቲባዮቲክ ቫይረስን ስለማይገል አይጠቅምም፡፡

 

·        ክሮኒክ ብሮንካይተስ ደግሞ ሲጃራ በማጨስ ምክንያት ይመጣል፡፡ የአየር ብክለት፣ አቧራ፣ ወይም አካባቢ ላይ ያሉ በካይ ጋዞችም አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል፡፡

 

ተጋላጭነት

·        ሲጃራ ማጨስ

·        የወረደ በሽታ የመከላከል አቅም

·        ለበካይ ነገሮች መጋለጥ

·        ቃር

 

   

ምን ሊያመጣ ይችላል?

አንዳንድ ጊዜ ለሳምባ ምች ሊያጋልጥ ይችላል፡፡ በተደጋጋሚ በብሮንካይተስ የሚጠቃ ሰው በጊዜ ለውጥ ለከባድ የሳምባ በሽታ (Chronic Obstructive Pulmonary Disease) ይጋለጣል፡፡

 

እንዴት መከላከል ይቻላል?

-         ሲጃራ አለማጨስ

-         አስፈለላጊ ክትባቶችን መውሰድ

-         እጅ መታጠብ

-         የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ ጭምብል መጠቀም

 

 

ምርመራ

በመጀመሪያዎቹ ቀናት ላይ ጉንፋንን እና ብሮንካይተስን መለየት ይከብዳል፡፡ ሃኪሞት ሳማባዎትን በማዳመጥ ለመለየት ይችላል፡፡ በተጨማሪም የደረት ራጅ፣ የአክታ ምርመራ፣ የመተንፈስ ብቃት ምርመራ ያስፈልጋል፡፡

 

ህክምና

አኪዩት ብሮንካይተስ ያለ ህክምና በሳምንታት ይድናል፡፡

 

መድሐኒቶች

ብዙውን ጊዜ ብሮንካይተስ በቫይረስ ስለሚመጣ አንቲባዮቲክስ አይረዳም፤ ነገር ግን ተያይዞ የባክቴሪያ ኢንፌክሺን ካለ አንቲባዮቲክስ ይታዘዛል፡፡

 

በተጨማሪም የሳል መድሐኒት፣ የአለርጂ እና የአስም መድሐኒቶች እንደአስፈላጊነታቸው የአየር ቧንቧ መቆጣትን ለመቀነስ ይታዘዛሉ፡፡

 

በቤት ውስጥ ምን ማድረግ ይቻላል?

·        ሳምባን እና የአየር ቧንቧን ሊያስቁጡ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ

·        የአየርን እርጥበት የሚጨምር መሳሪያ (Humidifier) መጠቀም

·        ከቤት ሲወጡ የአፍንጫና አፍ መሸፈኛ ጭምብል መጠቀም


ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                           t.me/DoctorTena

         የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                         fb.com/DoctorTenaEthiopia

 

Report Page