በፋይበር የበለፀገ ምግብ…

በፋይበር የበለፀገ ምግብ…

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐


በብዙ ጤና ነክ ምክሮች ላይ ፋይበር የመመገብን ጠቀሜታ በተደጋጋሚ ሲነሳ ይታያል፡፡ በዛሬው ጥንክራችን ይህንን ብዥታ ለመግለጥ እንሞክራለን፡፡


ፋይበር ምንድነው?

የምግብ ፋይበር የሚባለው ከምንመገበው እፅዋት ውስጥ ሰውነት ሊፈጨው ሊዋሃደን የማይችለው ክፍል ነው፡፡ ፋይበር ስለማይፈጭ እንዳለ ሆኖ የስነ-ልመት አካላቶችን እንደ ጨጓራ፣ ትልቁ እና ትንሹ አንጀትን በማለፍ ከሰገራ ጋር ይወጣል፡፡ሌሎች የምግብ አይነቶች እንደ ካርቦሃይድሬት፣ ስብ፣ ፕሮቲን ሰውነታችን ፈጭቶ ይዋሃደናል፡፡


ፋይበርን በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን፤

1.      የሚሟሟ የፋይበር አይነት

-         ይሄኛው የፋይበር አይነት ውሃ ውስጥ ሲሟሟ የሚዝለገለግ ይሆናል፡፡ የደም ውስጥ ኮሌስትሮል እና ስኳር መጠንን በመቀነስ ይታወቃል፡፡ የሚሟሟው ፋይበር በኦትስ፣ ባቄላ፣ ፖም፣ ገብስ እና ካሮት ውስጥ ይገኛል፡፡   

2.      የማይሟሟ የፋይበር አይነት

-         ሌላው የፋበር አይነት የማይሟሟው ነው፤ ይህ አይነት ለምግብ መፍጨት ስርዓት ተቃሚው ነው፡፡ በውሃ ስለማይሟሟ የስነ-ልመት አካላትን ማለፍ ስለሚችል የሰገራን መጠን ይጨምራል፡፡ ስለዚህ በድርቀት ለሚሰቃዩ ሰዎች መፍትሔ ነው፡፡ ያልተፈተገ እህል፣ ኦቾሎኒ፣ ጥራጥሬዎች፣ አትክልት እንደ ጥቅል ጎመን፣ ድንች፣ አረንጓዴ እሸት በማሟሟ የፋይበር አይነት በለፀጉ ናቸው፡፡

ሁለቱ የፋበር አይነቶች በምግቦች ውስጥ በተለያየ መጠን ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም የተለያዩ በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ጠቀሜታው ላቅ ያለ ነው፡፡


በፋበር የበለፀገ ምግብ ለምን ይጠቅማል?

·        የአንጀትን እንቅስቃሴ ያስተካክላል

·        የአንጀትን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል

·        የደም ውስጥ ኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል

·        የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ያስተካክላል

·        ጤናማ ክብደት እንዲኖር ይረዳል

·        ረጅም እድሜ ለመኖር ይጠቅማል


ፋይበር ከየት ይገኛል?

በቀላሉ የሚገኙ ነገር ግን የፋይበር ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ የምግብ አይነቶች፤

-         ያልተፈተገ እህል

-         ፍራፍሬ

-         አትክልት

-         ባቄላ፣ አተር እና ሌሎች ጥራጥሬዎች

-         ኦቾሎኒ እና ሌሎች ፍሬዎች


እናስተውል!!

ፋይበር እጅግ ጠቃሚ ቢሆንም ከመጠን በላይ ከተወሰደ የሆድ መነፋት፣ ቁርጠት እና አየር (ፈስ) ሊያመጣ ይችላል፡፡ የሚወስዱትን የፋይበር መጠንን ቀስ በቀስ በሳምንታት ውስጥ መጨመር ይመከራል፡፡ እንዲህ ማድረግ የስነ-ልመት ስርዓት ውስጥ ያሉ ተፈጥሮአዊ ጠቃሚ ባክቴሪያዎች እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም ውሃ በደንብ መጠጣት እጅግ ይጠቅማል፡፡ ፋይበር ውሃ ሲያገኝ የተሻለ ይጠቅማል፤ ከዚህ ጋርም ተያይዞ ሰገራን ለማለስለስ እና ለመጨመር ይረዳል፡፡  

   

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

         የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia


Report Page