ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት ፯

ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት ፯

@YeBiruk ዲያቆን ቡሩክ ይርጋ ዘውብ

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

           አሜን

✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"         

📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

         ቀናችንን በጸሎት እንጀምር


ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት ፯


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ሰባት በዚች ቀን ጠመው ከሚባል አገር የሆነ የከበረ አባት አባ ባውላ አረፈ።

   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

             አባ ባውላ

   ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

❖ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ መስተጋድል መነኲሴ ሆነ የሚኖረውም በላይኛው ግብጽ በአለ በእንጽና ገዳም ነው ስሙ ሕዝቅኤል የሚባል ረድእ አለው፤ እርሱም ስለ ትሩፋቱና ስለ ተጋድሎው ምስክር ሆነ ይህ አባ ባውላ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ራሱን ሰባት ጊዜ ገድሏልና።

❖ ለዚህም መጀመሪያው ራሱን በዕንጨት ላይ ዘቅዝቆ በመስቀል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት እንደ ተሰቀለ ኖረ፤ ደሙም በአፍንጫው ፈሰሰ ነፍሱንም አሳለፈ እግዚአብሔርም ከሞት አነሣው።

❖ ሁለተኛው ዓሣዎችና ዓንበሪዎች እንዲበሉት ራሱን ከባሕር ጨመረ እነርሱ ግን አልነኩትም በባሕርም ሠጥሞ ብዙ ወራት ኑሮ ሞተ፤ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዳግመኛ ከሞት አስነሣው።

❖ ሦስተኛም፡ ጊዜ ራሱን በአሸዋ ውስጥ ደፍኖ ሞተ ጌታችንም አስነሣው፤ አራተኛም በውስጡ ስለታሞች ድንጋዮች ካሉት ረጅም ተራራ ላይ ወጥቶ ራሱን ከተራራው ላይ ወደ ታች ወርውሮ ተንከባለለ የተሳሉ ደንጊያዎችም በሥጋው ሁሉ ገብተውበት ሞተ፤ ረድኡም ያለቅስለት ነበረ ጌታችንም መጥቶ ከሞት አሥነሣው አጽናናውም።

❖ አምስተኛ ከረጅም ዛፍ ላይ ወጥቶ ከስለታም ደንጊያ ላይ ራሱን ወረወረ ከሁለትም ተከፈለና ሞተ ያን ጊዜም ጌታችን አስነሣው፤ ስድስተኛ ራሱን በእግሮቹ ውስጥ አሥሮ አርባ መዓልትና አርባ ሌሊት እንዲህ ሁኖ ሞተ እግዚአብሔርም መልአኩን ልኮ ከሞት አነሣው አጽናናውም።

❖ ሰባተኛ ከውኃ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ እጆቹን ዘርግቶ አርባ መዓልት አርባ ሌሊት በመቆም ሞተ ክብር ይግባውና ጌታችንም አስነሣው እንዲህም ብሎ አጽናናው ወዳጄ ባውላ ሆይ ራስህን ሰባት ጊዜ እስከምትገድል ድረስ ሰውነትህን አደከምክ እንግዲህ ድካምህ ይብቃህ።

❖ አባ ባውላም ለመድኃኒታችን እንዲህ ብሎ መለሰለት ጌታዬ ሆይ ስለ ከበረው ስምህ እደክም ዘንድ ተወኝ አንተ አምላክ ስትሆን ስለኛ በመከራ ደክመህ ስለ ሰው ወገን ሞትክ ለእኛ ይህ አይገባንም ነበር በቸርነትህ ይህን የማዳንህን ሥራ ሠራህልን እንጂ፤ ጌታችንም ከአጽናናው በኋላ ከእርሱ ወደ ሰማይ ወጣ።

❖ ከዚህም በኋላ አባ ብሶይ ወደ እንጽና ገዳም ሒዶ ከአባ ባውላ ጋር ተገናኘ ጌታችንም ለአባ ባውላ ተገልጾለት ሥጋህ ከአባ ብሶይ ሥጋ ጋር በአንድነት ይኑር አለው ሁለቱም በአረፉ ጊዜ ሥጋቸውን በአንድነት አኖሩ።

❖ ወገኖቹም የአባ ብሶይን ሥጋ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊወስዱ በወደዱ ጊዜ በመርከብ ጫኑት መርከቢቱ ግን መንቀሳቀስን እምቢ አለች።


❖ ከዚህም በኋላ ተመልሰው የአባ ባውላን ሥጋ አምጥተው በመርከብ ላይ ጫኑት ያን ጊዜ መርከቢቱ ተጓዘች፤ እንዲህም የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወደ አስቄጥስ ገዳም አድርሰው በአባ ብሶይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት አኖሩ እስከ ዛሬም በዚያ ይኖራሉ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

                  አርኬ

✍️ሰላም ለርእስከ ዘመንፈስ ቅዱስ አጽንዓ። ከመ ትሰቀል ቊልቊሊተ መጠነ መዋዕል አርብዓ። ባውላ ጻድቅ ዘትጼኑ ቆዐ። ውስተ ገድል ጽኑዕ ዘአልቦ ምምዓ። ወደቀ ስብዐ ወተንሣእከ ስብዐ።

በዚችም ቀን የቅዱሳን ሰማዕታት የሚናስና የሐናሲ መታሰቢያቸው ነው በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

                  አርኬ

✍️ሰላም ለሚናስ ለእግዚአብሔር ስምዑ። ወለሐናሲ ካልኡ። እምቀደምቶሙ ፈድፋደ እስመ ኃይሉ ወጸንዑ። ወአመ ይቤሎሙ ወልድ ቡሩካነ አቡየ ንዑ። ውስተ ቤተ ወይን ኪያየ ያብኡ።

📌 ጥቅምት 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1.አባ ባውላ መስተጋድል

2.አባ ሕዝቅኤል ጻድቅ

3.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት

4.ቅዱስ ሐናሲ ሰማዕት

📌 ወርሐዊ በዓላት

1.ሥሉስ ቅዱስ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ)

2.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

3.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ)

4.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት

5.አባ ባውላ ገዳማዊ

6.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

7.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)

✍️"እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፤ ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታል፤ ስለ እኔ ግን ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል፤ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል? "

📖ማቴ. 16፥24

ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ እምእለ ተፀመድኩ ዘልፈ ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውክፈ እምእለ አብዑ ብዑላን ዘተርፈ።

ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን ሰማዕታት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን ደናግል ዓዲ ወመነኮሳት ኄራን ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን እስከ አረጋዊ ልሂቅ እምንኡስ ሕፃን።

ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ ዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ ወለዘሰምዐ ቃሎ በእዝነ መንፈስ በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኲሉ እምባእስ ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።


ጌታ ሆይ ከብልፅግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።

እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።

ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።

✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝


✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"

📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ


             ወስብሐት ለእግዚአብሔር

                             ይቆየን 


───────────

                   Channel

 🧲 https://telegram.me/Tewahedo12

       FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)

🧲 http://facebook.com/Tewahedo12  

       YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)

🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw

 ───────────


Report Page