ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር ፰
@YeBiruk ዲያቆን ቡሩክ ይርጋ ዘውብ✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን
✍"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል"
📚ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ቀናችንን በጸሎት እንጀምር
ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር ፰
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው የአርባዕቱ እንስሳ በዓላቸው ሆነ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
አርባዕቱ እንስሳ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው፤ ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።
❖ የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።
❖ የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው፤ የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።
❖ ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።
❖ የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ፤ አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።
❖ ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ።
❖ ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።
❖ በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ፤ መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።
❖ እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።
❖ ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።
❖ ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።
❖ በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ፤ በእውነት ይገባዋል፤ እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ፤ እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።
❖"ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው።
❖ ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል፤ ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።
❖ ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ኪሩቤል አማላጅነት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለክሙ ኪሩባውያን አፍራሱ። ለመሐይምን ወጻድቅ እንተ ወርቅ አክሊለ ርእሱ። ኀበ ዝ አምላክ ዘትፀውርዎ በአትሮንሱ። ለእለ ጌገዩ ወለእለሂ አበሱ። ሰአሉ መድኃኒተ ወምሕረተ ኅሡ። መንገለ ፈለሱ ወሖሩ አበዊሃ ዘቀደሙ። ለእግዚእ ክብራ ዘመጽአት በበዓልክሙ። ኪሩባውያን አፍራስ ንስእለክሙ። ነጽርዋ ከመ ትሬኢ ኀበ መፍቅዶ ወልድ እሙ። እስመ ብዙኃት አዕይንት ለክሙ
በዚችም ቀን ከአለቆች ለአንዱ ለመላእክት አለቃ አፍኒን የበዓሉ መታሰቢያ ሆነ። ይህም ከሱራፌልና ከኪሩቤል ጋር የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን የሚጠብቅ ነው ስለርሱም ሄኖክ እንዲህ አለ ያንን ቤት ሱራፌልና አፍኒን ዙሪያውን እየዞሩ ይጠብቁታል እነርሱም የልዑልን የጌትነቱን ዙፋን ሲጠብቁ የማያንቀላፋ ናቸው።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ መልአክ አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለከ እንዘ ትቄድስ ትሥልስቶ። ዘታጸንዕ ዘልፈ ለመንበረ አምላክ ዐቂቦቶ። አፍኒን መልአክ ዘምግበሪከ አእኲቶ። ለጌጋየ ሰብእ አመ ትሴሩ ጽሕፈቶ። መጽሐፈ ዕዳየ ኢትኅድግ ባሕቲቶ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በዚችም ቀን የሊቀ ጳጳሳት ዮሐንስ መታሰቢያው ነው ለንጉሥ ቈስጠንጢኖስም መስቀል ተገለጸለት።
❖ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ለቤተ ክርስቲያን የፈፀመውን መልካም ተግባር ያሕል መሥራት የቻለ ንጉሥ በሐዲስ ኪዳን የለም፤ ጻድቁ ንጉሥ ከቅድስት እናቱ እሌኒና ከአረማዊ አባቱ ቁንስጣ በበራንጥያ ተወለደ::
❖ ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ /የመከራ ጊዜ/ ወይም የሰማዕታት ዘመን በመሆኑ ክርስቲያኖች በግፍ የሚጨፈጨፉበት ወቅት ነበር፤ ክርስቲያኖችን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት በተደረገው የ40 ዓመታት ዘመቻ አብያተ-መቃድስና መጻሕፍት ተቃጠሉ፤ ብዙዎቹ በየበርሃው ተሰደዱ፤ ሚሊየኖች በግፍ አለቁ::
❖ የዚሕን ዘመን መከራ በውል ያልተረዳ ሰው ቅዱስ ቆንጠንጢኖስን ሊያከብር አይችልም፤ ምክንያቱም ይህን የመከራ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር አስቁሞ ቀርነ-ሃይማኖት የቆመው ብዙ ሥርዓት የተሠራው ቤተ ክርስቲያንም ያበራችው በዘመኑ ነውና::
❖ ቅዱሱ ንጉሥ ለሁሉም ነቢያት ሐዋርያትና ሰማዕታት አብያተ ክርስቲያናትን ራሱ በመሠረታት በቁስጥንጥንያ አንጿል፤ በዘመኑ ቤተ ክርስቲያን በሰላም ኖራለት በኃይለ መስቀሉ ጠላት ጠፍቶለት ኑሮ በዚህች ቀን አርፏል::
❖ ይህቺ ቀን ታላቁ ንጉሥ በፈለገ ኮቦር ቅዱስ መስቀልን የተመለከተባት ናት፤ መክስምያኖስን ሊወጋ ወደ ሮም በተጉዋዘ ጊዜ በሰማይ ላይ መድኅን መስቀል ተዘርግቶ በላዩ ላይ "ኒኮስጣጣን" የሚል በዮናኒ ልሳን ተጽፎበት ተመልክቷል::
❖ ይህንንም "በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" ማለት ነው ብለው ተርጉመውለታል፤ እርሱም በጋሻው በጦሩ በሰይፉ በፈረሱ ላይ የመስቀል ምልክትን አድርጐ ማሕደረ ሰይጣን መክስምያኖስን ድል ነስቶታል፤ እኛንም በሞገሰ መስቀሉ ይጠብቀን::
በረከት ረድኤቱ ይደርብ፤ በጸሎቱ ይማረን
አርኬ
✍️ሰላም ለቈስጠንጢኖስ መንፈሰ ልቡና ዘአጥበቦ። በአሚነ ክርስቶስ ይጽናዕ ወያስተራትዕ ሕዝቦ። በዛቲ ዕለት አምሳለ ከዋክብት በተማእትቦ። በዲበ ዐራቱ እንዘ ሀለወ ሰኪቦ። በፈለገ ባዶስ ርእየ ወነጸረ ጸልቦ።
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
አባ ቅፍሮንያ
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
❖ በዚችም ቀን የአረማዊ መኰንን ልጅ የነበረ አባ ቅፍሮንያ አረፈ፤ ከዕለታትም በአንዲቱ ስሙ መርቆሬዎስ የሚባል መነኰስ ከአባ ጳኵሚስ ገዳም ወደ ሀገሩ መጣ እርሱ ክርስቲያን እንደሚሆን በእርሱ ላይ ትንቢት ተናገረ።
❖ ከጥቂት ወራትም በኋላ ገዳማትን ሊያጠፋ ምርኮንም ሊማርክ ሠራዊቱን ሰብሰቦ ወደ ግብጽ አገር ዘመተ ወደ አባ ጳኵሚስም ገዳም በደረሰ ጊዜ አበ ምኔቱ ወደርሱ ወጥቶ እኔ ነኝ አለው ቅፍሮንያም ሰምቶ አበምኔቱን ለብቻው አግልሎ እንዲአጠምቀውና የምንኵስናንም ልብስ እንዲአለብሰው ለመነው አበ ምኔቱም እሺ በጎ አለው።
❖ ከዚህም በኋላ ሠራዊቱ ወደ ሀገራቸው በተመለሱ ጊዜ ብቻውን ቀረ በዚያንም ጊዜ የምንኵስናን ልብስ ለበሰ ተጋድሎውንም በመጾምና በመጸለይ ጀመረ።
❖ ሰይጣንም በእርሱ ላይ ቀንቶ ነገረ ሠሪ አስነሣበት በመኳንንቱም ዘንድ ወነጀለው እነርሱም አገራችንን ያጠፋ የመኰንን ልጅ ከዚህ አለ ብለው ገዳሙን ከበቡ እግዚአብሔርም ሠወረው በአጡትም ጊዜ ነገረ ሠሪውን ገደሉት።
❖ ይህም ቅዱስ በገድል ተጠምዶ ኖረ በየሰባት ቀንም ይጾማል ያለ መራራ አደንጓሬ አይመገብም። በዚያም ወራት የምድር አውሬ እንስሶቻቸውን እየገደለ በገዳሙ ላይ ጥፋትን አደረሰ አባ ቅፍሮንያም ወደርሱ መጥቶ እንደ በግ ይዞ አሠረው ዐሥር ዓመትም ቆይቶ ሞተ።
❖ ቅዱስ ቅፍሮንያም የእግዚአብሔር መልአክ እየመራው ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ በአንዲትም ቀን ደረሰ በዚያም ታላቅ ምሥጢርን አየ ከከበሩ ቦታዎችም ተባርኮ ወደ መኖሪያው ተመልሶ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
✍️ሰላም ለቅፍሮንያ እንተ ኮነ ክርስቲያናዌ። ኀዲጎ አባሁ መኰንነ አረማዌ። እስከ መነኰሳት ነበሩ በኅድዓት ወበጽማዌ። አሠረ ከመ በግዕ ዘአልቦ ምንሳዌ። መራዕየ ደብር ዘይቀትል አርዌ።
❖ በዚችም ዕለት የሰማዕት ኤስድሮስ ማኅበር የሆኑ የመቶ ሰማንያ ሁለቱ መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን።
📌 ኅዳር 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን 4ቱ እንስሳ (ኪሩቤል)
2.ቅዱስ አፍኒን ሊቀ መላእክት
3.አባ ቅፍሮንያ ጻድቅ
4.ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ (ዘምስለ ቅዱስ መስቀል)
5.ቅድስት እግዚእ ክብራ
📌 ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
3.አቡነ ኪሮስ
4.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
5.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)
✍️"በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በሁዋላ ዓይኖች የሞሏቸው አራት እንስሶች ነበሩ፤ ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል፤ አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሏቸው"
📖ራዕይ 4 ፥ 6
ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ።
ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን።
ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
ጌታ ሆይ ከብልጽግናቸው ብዛት የተነሳ ብዙ መባ ካገቡት ይልቅ የደሀዪቱን አነስተኛ መባ እንደተቀበልህ ለሁል ጊዜ የሚያገለግሉህ አእላፍ መላእክትን እያሳሰብሁ በችግሬ ጊዜ የማቀርብልህን ምስጋና ተቀበል።
እናንተም ቅዱሳን ነቢያት የወንጌል ሰባኪያን ሐዋርያት ሰማዕታትና ጻድቃን ትጉሃን መላእክት ፍጹማን ደናግል እንዲሁም ደጋጎች መነኰሳት ሆይ ልጅ አዋቂ ሳይለይ የምንሰበሰብበትን የጉባኤ ቦታ ባርኩ።
ይህን መጽሐፍ ወረቀት አዘጋጅቶ ብራና ደምጦ የጻፈውና ያጻፈውም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጐመውን ቃለ ንባቡን በእርጋታ መንፈስ እና በተመስጦ ሕሊና ያዳመጠ በደለኛን ሁሉ የምታስምር የጌታ እናቱ በማርያም ጸሎት ኢየሱስ ክርስቶስ በአንድነት ይማረን።
✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝💚💛❤️✝
✍"ልብህን በእርጋታ አኑረው፤ የሁሉም መጨረሻ እና የሁሉም አገልጋይ ለመሆን በጣም ትጋ ለከንቱ ንግግር ዘገምተኛና ሰነፍ ሁን፤ ነገር ግን የቅዱሳት መጻህፍትን ቃል በማወቅ በመስማት ድኅነትን የሚሰጡ ናቸውና ብልህ ሁን"
📚ታላቁ ባስልዮስ ዘቂሳሪያ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ይቆየን
───────────
Channel
🧲 https://telegram.me/Tewahedo12
FB Like Page (የፌስቡክ ፔጅ)
🧲 http://facebook.com/Tewahedo12
YouTube Subscribe (ሰብስክራይብ)
🧲 https://www.youtube.com/channel/UCvYxUdv1D-5juH_P6iE7XXw
───────────