ስለ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ በጥቂቱ

ስለ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ በጥቂቱ

@Ethiopianbusinessdaily

ስለ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ በጥቂቱ

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 100 ሺ የሚሆኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንዳሉ ቢነገርም ለነዚህ ተሽከርካሪዎች የሀይል መሙያ ጣቢያዎች ግን አናሳ መሆናቸው ይነገራል።

መንግስትም በ10 ዓመቱ ስትራቴጂክ እቅዱ ውስጥ በአዲስ አበባ 1,176 እንዲሁም በክልል ከተሞች 1,050 በአጠቃላይ በሀገሪቱ 2,226 ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን ለማቋቋም እቅድ አስቀምጧል።

በቅርቡም ቶታል ኢነርጂስ በአዲስ አበባ ለቶታል ኢነርጂስ መጀመሪያ የሆነውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ ከፍቷል።

በቦሌ ኤርፖርት መንገድ ላይ ወይም ቦሌ ማተሚያ በመባል የሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ሀይል መሙያ ለሁሉም የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አይነቶች የሚሰራ ሲሆን በ አንዴ ሶስት ተሽከርካሪዎችን ቻርጅ የማድረግ አቅም አለው።

ይህ ከ100,000 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ያላትና ቁጥሩም በፍጥነት እያደገ ለመጣባት ነገር ግን ውስን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ መሠረተ ልማት ላላት ኢትዮጵያ ትልቅ እርምጃ ነው ተብሏል።


🔋 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ አደራረግ ምን ይመስላል?

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (EV) እንደ ተሽከርካሪው አሰራር በሁለት የተለያዩ መንገዶች ቻርጅ ሊደረግ ይችላል።

#AC (Alternating Current) ቻርጀሮች (ከ 3.7 KVA እስከ 43 KVA የሚደርስ ኃይል ያላቸው) ተሽከርካሪዎቻቸውን ለረጅም ጊዜ ቻርጅ ላይ አድርገው መሙላት ለሚፈልጉ ግለሰቦች ተስማሚ ናቸው። እነዚህ ቻርጀሮች በዋነኛነት በቤት ውስጥ፣ በስራ ቦታ እና በፓርኪንግ ውስጥ ይገኛሉ።

#DC (Direct Current)  ቻርጀሮች ደግሞ ከAC ቻርጀሮች ከፍ ያለ ሃይል መሙላት ( ከ24 kW እስከ 350 kW) ይችላሉ። ከፍተኛው ኃይል (350KW) በአሁኑ ጊዜ በጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ብቻ ይገኛል።


⌛ ቻርጅ ለማድረግ ምን ያህል ሰዓት ይፈጃል?

የDC (Direct Current)  ቻርጀሮች በፍጥነት ቻርጅ መሙላት ለሚፈልጉ የኤሌክትሪክ ተሽከካሪ ባለቤቶች ይበልጥ ተስማሚ ሲሆኑ ለአንድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ወደ 80% ሀይል ለመሙላት ከ20 ደቂቃ እስከ 1 ሰአት ይወስዳሉ። 

በተቃራኒው ደግሞ በ Alternating Current ቻርጀሮች የሚሞሉ ተሽከርካሪዎች በዝግታ እና መካከለኛ ፍጥነት ሀይል ይሞላሉ። በዝግታ ሲባልም ከ10-14 ሰዓታትን እንዲሁም በመካከለኛው የፍጥነት ወሰን ከ4 እስከ 6 ሰዓታት ይፈጃል።

በቅርቡ በመዲናዋ የተመረቀው የቶታል ኢነርጂስ የ AC እና DC ቻርጅ ማገናኛዎችን (ቻርጀሮች) ሲኖሩት፤ በዚህም ሁሉንም የተሽከርካሪ አይነቶች ያገለግላል ተብሏል።

ቶታል ኢነርጂዎች የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ከ20% እስከ 80% እንዲሞሉ ይመክራል። ምክንያቱም ከ 80% በላይ በሚሞሉ ጊዜ ቻርጅ የማድረግ ፍጥነት በእጅጉ እንደሚቀንስ እና እንደውም ከ 80% እስከ 100% ለመድረስ የሚወስደው ጊዜ ከ 20% ወደ 80% ለመድረስ ከሚወስደው ጊዜ ጋር ይመሳሰላል ሲል ኩባንያው አስረድቷል።

Report Page