ሰይጣንን_ያየ

ሰይጣንን_ያየ

ⓣⓐⓜⓤ

📝📝 በ

 📝📝📝📝 ታምራት


“ከእናንተ መሐል ማነው ሰይጣንን ያየ?” ጠየቁ ጋሽ እንትና... ተያየን... ማሂ ፈርታለች እንባዋን ዓይኖቿ ላይ አቀባብላ አስቀመጠች...ፈሪ ናት ቆንጆ ፈሪ... ባትፈራ አገባት ነበር... ባሴ ይቁለጨለጫል ማንን እንደሚያስደነግጥ አስቦ ፈገገ ... ሚጢጢ ባሴን ታየዋለች የተቆላ ቡና ከሚመስል ፊቱ ጋር ተንኮሉ ተዳምሮ ሰይጣን መስሎ ታያት።

እናቷ ጋር የሚመጡት አባ ሰይጣን የውሸት አባት ነው ሲሉ ሰምታለች ታዲያ ከባሴ በላይ ማን ውሸታም አለ?... እኔ ጋሽ እንትናን አልወዳቸውም... ባቴ ላይ እንትፍ ብዬ እድፌን አድበለብላለሁ... ጭቃ መሳይ ነው... እቴቴ ጠፍጥፌ ነው የሰራሁህ የሚሉኝ ትዝ ብሎኝ ቡ.ፍ.ፍ አልኩ...ስላቅ ሳቅ ተቦትርፎ ጉራማይሌ ድዶቼ ሲታዩ ጋሽ እንትና ገላመጡኝ... እነሚጢጢ ጋር የሚመጡት አባ ግን የተሰራነው ከአፈር ነው አሉኝ ሚጢጢን አፈር ብዬ ስሰድባት ሰምተው... የመሬትን ደም ፍለጋ ቁፋሮ ጀመርኩ...

ጋሽ እንትና ቁንጮዬን ጎትተው...“አንተን እኮ ነው ሰይጣንን አይተኸዋል?”ብለው አጉረጠረጡብኝ...

“አይተኸዋል ወይ?”

“አ..አ..አዎ”

“የት?”

“እዚሁ”

“ኧ!” ዞር ዞር አሉ።

“የታል?”

“እ..እየጎተተኝ ነው!”

ጥፊ እንዳይመረግብኝ እንደካልሲ ኳስ በቲሸርቴ ተጠቀለልኩ... ባሴ ከኋላ ሆኖ በትናንሽ እጆቹ ግራ እግራቸውን ያዘው... ጮኹ ጋሽ እንትና የሚስታቸውን ስም እየጠሩ...

ተገረምኩ . . .

ለካስ መጮኽ ይችላሉ . . .

ሮጡ ጋሽ እንትና. . . ለካስ መሮጥ ይችላሉ . . .

በፊት ከአበሩ ቤት ጀምረው ቆቁ ሱቅ እስኪደርሱ በእጆቼ ጣቶች ሙሉ ደቂቃ ይወስድባቸው ነበር . . . ያበሩን ደጅ የተቀመጠ መወዘቻ ሾተው ሮጡ . . .

ጨረቃም እየተከተለች ሳቀችባቸው። ቂ . ቂ . ቂ

“ፐ! እንመልምላቸው ለቡድናችን” አለኝ ባሴ . . .።

............


 •═════•••🍃❀🍃•••═════•

   🌺http://t.me/tankuaa🌺 

  •═════•••🍃❀🍃•••═════•

Report Page