ምን ጎደለብኝ

ምን ጎደለብኝ

Solicious18 Wallpapers™
ሀምሳ አለቃ ስዮም ገብረየስ ቤተሰብ | ምን ጎደለብኝ

ጌታን ይዤ ተደግፌ አላውቅም ተደናቅፌ

እርሱ ምርኩዜ ነው ለኔ ማዳኑን አይታለች ዓይኔ

ስለዚህ ደስ ብሎኝ ዛሬ አቀርባለሁኝ ዝማሬ

ነውና እርሱ ገናና ይድረሰው ክብር ምስጋና


ምን ጎደለብኝ ሁሉ ሞልቶልኛል

ኤልሻዳዩ ጌታ ኢየሱስ ድንቅ አድርጎልኛል

ያጣሁት የለም ሁሉን አግኝቻለሁ

ስሙ ይክበር ለዘላለም በእርሱ ሰው ሆኛለሁ


ስጠራው ጌታ ኢየሱሴ ፈጥኖ ይደርሳል ለነፍሴ

እኔን ችላ ብሎ አያውቅም እርሱ ከቶ አይሰለችም

በደስታ አስተናግዶኛል የጎደለኝ ሁሉም ሞልቷል

የእርሱ ውለታ በዝቶልኛል ልሰግድለት ይገባኛል 


ምን ጎደለብኝ ሁሉ ሞልቶልኛል

ኤልሻዳዩ ጌታ ኢየሱስ ድንቅ አድርጎልኛል

ያጣሁት የለም ሁሉን አግኝቻለሁ

ስሙ ይክበር ለዘላለም በእርሱ ሰው ሆኛለሁ


ከተጣልኩበት አንስቶ ወደ ታላቅ ክብር ጠርቶ

ወግ ማዕረግ አሳይቶ መቅረዜን በዘይት ሞልቶ

ውርደቴን በክብር ሽሮ ጠላቴንም አሳፍሮ

አስቀምጦኛል ለምለም ቦታ አክብሮኛል ይክበር ጌታ


ምን ጎደለብኝ ሁሉ ሞልቶልኛል

ኤልሻዳዩ ጌታ ኢየሱስ ድንቅ አድርጎልኛል

ያጣሁት የለም ሁሉን አግኝቻለሁ

ስሙ ይክበር ለዘላለም በእርሱ ሰው ሆኛለሁ


ነፍሴን ከጥፋት አድኗል እርሱ ለእኔ ድንቅ አድርጓል

ከበደሌ አንጽቶኛል ሞቴንም በሞቱ ሽሯል

ዘላለም ለእርሱ እገዛለሁ ለስሙም እዘምራለሁ

ከፍ ያደረገኝን ኢየሱስ እኔም ከፍ አደርገዋለሁ


ምን ጎደለብኝ ሁሉ ሞልቶልኛል

ኤልሻዳዩ ጌታ ኢየሱስ ድንቅ አድርጎልኛል

ያጣሁት የለም ሁሉን አግኝቻለሁ

ስሙ ይክበር ለዘላለም በእርሱ ሰው ሆኛለሁ


የጎደለኝ ነገር የለም ሁሉ ሞልቶልኛል ዛሬ

በኢየሱስ ሕይወቴ ጸንቷል ተበጥሷል እስራቴ

ስሙ ይክበር ለዘላለም ያላደረገልኝ የለም

ሰው አርጎኛልና ጌታ አቀርባለሁ ለእርሱ እልልታ


ምን ጎደለብኝ ሁሉ ሞልቶልኛል

ኤልሻዳዩ ጌታ ኢየሱስ ድንቅ አድርጎልኛል

ያጣሁት የለም ሁሉን አግኝቻለሁ

ስሙ ይክበር ለዘላለም በእርሱ ሰው ሆኛለሁ


ሀምሳ አለቃ ስዮም ገብረየስ ቤተሰብ | ምን ጎደለብኝ 

Report Page