ምንም ብሆን - Sofia Shibabaw

ምንም ብሆን - Sofia Shibabaw

 Sofia Shibabaw‎ | Sema Belew


የኔን ፡ ጠያፉን ፡ ሕይወት

ውበትን ፡ ጨምሮበት

ሳላውቅ ፡ ባለማመን ፡ ስላደረኩት

አገኘሁ ፡ ምህረት (፪x)

ምንም ፡ ብሆን ፡ ጌታ ፡ ጌታዬ ምሮኝ

ምንም ፡ ብሆን ፡ ቃሉ አሳምሮኝ

ምንም ፡ ብሆን ፡ ደሙ ፡ አሳምሮኝ

ደጉ ፡ ኢየሱስ ፡ ደርሶልኛል

ከሰይጣን ፡ አፍ ፡ አውጥቶኛል

ደጉ ፡ ኢየሱስ ፡ ደርሶልኛል

ከጉድ ፡ ከእፍረት ፡ አውጥቶኛል

በምህረቱ ፡ ባለጠጋ

ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ተጠጋ

ምንም ፡ ብሆን ፣ ምንም ፡ ብሆን

አልጣለኝም ፡ ጌታ ፡ አለሁ ፡ በእርሱ ፡ ጎን (፪x)

ከቤቴ ፡ እንዳትገባ ፡ ብዬው ፡ የነበረው

በፍቅር ፡ መጣና ፡ ታሪኬን ፡ ቀየረው

አንድ ፡ ሁሉት ፡ ብሎ ፡ የሚቆጠር ፡ ጽድቄ

ምን ፡ ነበረኝና ፡ ከአብ ፡ፊት: ርቄ

በመካከል ፡ ገብቶ ፡ ጠበቃዬ ፡ ዋሴ

ደጉ ፡ ኢየሱሴ

ግርማን ፡ ከሚያሳጣኝ ፡ ሥራዬ ፡ ተሽሮ

ዛሬስ ፡ እገኛለሁ ፡ ቆሻሻዬን ፡ ሁሉ

ደሙ ፡ አሳምሮ

ቃሉ ፡ አሳምሮ

መንፈሱ ፡ አሳምሮ

ምንም ፡ ብሆን ፡ ጌታዬ ምሮኝ

ምንም ፡ ብሆን ፡ ቃሉ አሳምሮኝ

ምንም ፡ ብሆን ፡ ደሙ ፡ አሳምሮኝ

ደጉ ፡ ኢየሱስ ፡ ደርሶልኛል

ከሰይጣን ፡ አፍ ፡ አውጥቶኛል

ደጉ ፡ ኢየሱስ ፡ ደርሶልኛል

ከጉድ ፡ ከእፍረት ፡ አውጥቶኛል


በምህረቱ ፡ ባለጠጋ

ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ተጠጋ

ምንም ፡ ብሆን ፣ ምንም ፡ ብሆን

አልጣለኝም ፡ ጌታ ፡ አለሁ ፡ በእርሱ ፡ ብሆን (፪x)

የት ፡ አለኝ ፡ በጐነት ፡ የለኝ ፡ መልካምነት

ልናገር ፡ በድፍረት ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ምልበት

የተላለፈብኝ ፡ የመርገም ፡ ሀረጌ

አየሁት ፡ በክንዱ ፡ ሲሰብረው ፡ ጌታዬ

እኔነቴን ፡ አልፎ ፡ ለመጣው ፡ ሊፍክር

ኧረ ፡ እንዴት ፡ አልዘምር

ምንም ፡ ብሆን ፡ ይህን ፡ አረገልኝ ፡ ጌታ

እስቲ ፡ ላመስግነው ፡ ከውስጥ ፡ ከመንፈሴ

ተሰብሯል ፡ ቀምበሬ

የድል ፡ ቀን ፡ ነው ፡ ዛሬ

ያክብረው ፡ ከንፈሬ

ምንም ፡ ብሆን ፡ ጌታዬ ምሮኝ

ምንም ፡ ብሆን ፡ ቃሉ አሳምሮኝ

ምንም ፡ ብሆን ፡ ደሙ ፡ አሳምሮኝ

ደጉ ፡ ኢየሱስ ፡ ደርሶልኛል

ከሰይጣን ፡ አፍ ፡ አውጥቶኛል

ደጉ ፡ ኢየሱስ ፡ ደርሶልኛል

ከጉድ ፡ ከእፍረት ፡ አውጥቶኛል

በምህረቱ ፡ ባለጠጋ

ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ተጠጋ

ምንም ፡ ብሆን ፣ ምንም ፡ ብሆን

አልጣለኝም ፡ ጌታ ፡ አለሁ ፡ በእርሱ ፡ ብሆን (፪x)

በቃ ፡ ልጅ ፡ ነኝ ፡ እኔ

ተሰብሯል ፡ ኩነኔ

ተጥሏል ፡ ከሳሼ

ማጥ ፡ ውስጥ ፡ አልገኝም ፡ ዳግም ፡ ተመልሼ

በምህረቱ ፡ ባለጠጋ

ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ተጠጋ

ምንም ፡ ብሆን ፣ ምንም ፡ ብሆን

አልጣለኝም ፡ ጌታ ፡ አለሁ ፡ በእርሱ ፡ ብሆን (፪x)


Report Page