"ምርጫ"

"ምርጫ"

ⓣⓐⓜⓤ

📝📝 በ

📝📝📝📝 ታምራት

ቀኝ እጁ አይረጋም... ይንቀለቀላል

ጸጉሩን ፣ የቤቱን እምቅ አየር ፣ ጠረጴዛውን ይዳስሳል።

       .....


  ብክን ብክንክን

          አሳብ ተረግዞ

  ማዋለጃው ግን ተወግዞ!

           .....

ባቶቹ በደማም ወልጋዳ ቃላት ተመልተዋል። ቅር ብሎታል... ለምን?... ዛሬ መጻፍ አለበታ ካልሆነ ከውስጠ ሰላም ጉዞው ይገታል።

      .....

 እጁ የለመደ በስንጥር ማቅለምን

 ብዕር እንዳትሰጡት አሳቡ እንዳይዳምን።

(የውስጥ አውቃ አዝማሪት)

     .....

ከግማሽ ሰዓት በፊት የት አካባቢ ነበር የተቀመጠው?

ስንጥሩ እዚያ መኖር አለበት።

.

.

.

 አዎ...! ከባለሚዛኑ ልጅ አጠገብ... የቤቱን በር አጋጭቶ በሩጫ ወደ ቦታው ሄደ... ልጁ በግርምት ያየዋል... በዐይኑ ይቃብዝ ገባ... ከብዙ ፍለጋ በኋላ ስንጥሩን ከሌሎች መሐል ለየው...

.

.

.

አሁን ለጠይሟ ባለሱቅ የሰጠችውን ብዕርና ወረቀት መመለስ ብቻ ነው የቀረው።

.

.

.

ሱቋ አዲስ በገባ ደረቅ ሳሙና ጠረን ታውዳለች...

.

እንደደረሰ ስጦታዎቹን እንቁላል ከያዘ ቅርጫት አጠገብ አስቀመጣቸው..." አ_አ_አመሰግናለሁ" የሚል ቃል አሰምቶ እዚያው መጻፍ ጀመረ...ባቶቹ ላይ አንቀጻቸው ያልተለየ ድርብርብ የቅርብና የዓመታት ሽንትርትር ቃላት ይታያሉ...።

:

ዳጎስ ያለ ማስታወሻ መያዣ የሚገዛ አንገቱን በስካርፍ የከበበ ጎልማሳ ሰፈርተኛ ለጠይሟ ሴት "ይገርምሻል ታላቁ ደራሲ ፊዮዶር ዶስቶቪስኪም ከሚጥል በሽታው ጋር መኖርን ነበር የመረጠው ይኼኛው ደግሞ ከነሽትንትሩ" ብሏት ሪዙን እየመዘዘ...ራሱን እየወዘወዘ ሄደ።

                 ................

    •═════•••🍃❀🍃•••═════•

    🌺http://t.me/tankuaa🌺

    •═════•••🍃❀🍃•••═════•

Report Page