ለየት ይላል

ለየት ይላል

Solicious18wp
ሀና ተክሌ | ለየት ይላል


ሰው ይሮጣል ይለፋል አይቆምም ካለበት

ሊደርስ ከምኞቱ ካሰበበት

ጌታውን ግን የረሳ የምድሩ ከርታታ

በሰላም አይኖርም የማታ የማታ


እኔም እሮጣለሁ ሰው ነኝ እና እንደ ሰው

ልደርስ ከምኞቴ ሕልሜ ነው ከምለው

ግና ይህ አይደለም የኔ ቁምነገሬ

ከሰማዩ ጌታ ነውና ነገሬ


ነገሬ ያለው በእርሱ እጅ ነው |x4

የሚያስፈራኝ የሚያሰጋኝ እስኪ ማነው |x4

ነገሬ ያለው በእርሱ እጅ ነው |x4

የሚያስፈራኝ የሚያሰጋኝ እስኪ ማነው |x4


የማይነጥፍ ሰላም ኢየሱስ ሰጥቶኛል

ከከንቱ መባከን ጌታ ታድጎኛል

እኔ አስቀድሜ የእርሱን ቤት ስሰራ

አየዋለሁ በእርሱ የኔ ቤት ሲሰራ


አልሰጋም ለነገም ብሩህ ቀን ይሆናል

ከእርሱ ጋራ ሆኜ የድል ቀን ይበዛል

ምታመነው አምላክ የሌለ አይደለም

ጌታን ጌታን ብሎ ያፈረ ሰው የለም


አሰራሩ ለየት ይላል አሰራሩ |x4

ነገሬ ያለው በእርሱ እጅ ነው

ዘመኔ ያለው በእርሱ እጅ ነው

ሕይወቴ ያለው በእርሱ እጅ ነው

ኑሮዬ ያለው በእርሱ እጅ ነው


የሚያስፈራኝ የሚያሰጋኝ እስኪ ማነው |x4

አሰራሩ ለየት ይላል አሰራሩ |x4


ሞኝ ናት ይሉኛል እኔን ሳይረዱት ቀምሰው

ተመለሽ ይሉኛል ዋጋ ቢስ አድርገው

እኔ አልፈልግም ካልኩኝ ጭቅጭቅ ምንድነው

እምቢ አሻፈረኝ ኢየሱስ ጌታ ነው


ድንቅ ነው ለኔ ጌታ

ድንቅ ነው ለኔ የሱስ

ሞኝነት ቢመስላት ለዓለም

ድንቅ ነው ለኔ ዘላለም


ድንቅ ነው ለኔ ጌታ

ድንቅ ነው ለኔ የሱስ

ሞኝነት ቢመስላት ለዓለም

ድንቅ ነው ለኔ ዘላለም


አሰራሩ ለየት ይላል አሰራሩ |x4


ሀና ተክሌ | ለየት ይላል


Report Page