ለውዝ እና ጠቀሜታው

ለውዝ እና ጠቀሜታው

Dr. Tena - Bethel


🖐🖐🖐 ሰላም የዶክተር ጤና ቤተሰቦች!! 🖐🖐🖐

በሀገራችን በብዙ መደብሮች የመይጠፋው ለውዝ ተወዳጅ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ጠቀሜታውን እያወቅን እንድንመገበው በዛሬው ጥንክራችን እናነሳለን፡፡

 

ለውዝ

ለውጥ የጥራጥሬ አይነት ሲሆን ከወደ ደቡብ አሜሪካ እንደመጣ ይነገራል፡፡ በተለያዩ ሀገራት የተለያየ ስያሜ አለው፡፡ ለውዝ በፕሮቲን፣ ስብ እና ሌሎች አስፈላጊ ንጥረ ምግቦች እንደ ማግኒዢየም፣ ፋይበር፣ ኮፐር፣ ቫይታሚን ኢ እና አርጂኒን የበለፀገ ነው፤ በአንጻሩ ደግሞ የካርቦሀይድሬት ይዘቱ ዝቅተኛ ነው፡፡ ጥናቶች እናዳመለከቱት ከሆነ ለውዝ ውፍረት ለመቀነስ እና የልብ በሽታ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

 

ነገር ግን ለለውዝ አለርጂክ የሆኑ ሰዎች በጭራሽ መውሰድ የለባቸውም፡፡ ምክንያቱም መሰል አለርጂዎች ህይወትን ሊቀጥፉ ይችላሉ፡፡

 

በቀን ሳይበዛ የተወሰኑ የለውዝ ፍሬዎችን መውሰድ እጅግ ይረዳል፡፡

 

ከለውዝ ጥቅሞች ውስ የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸው፤

-         በብዙ ጠቃሚ ንጥረ-ምግቦች የበለጸገ ነው

-         ከልብ እና ካንሰር በሽታ ይከላከላል

-         የድብርትን ስሜት ይቀንሳል

-         ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣን የመርሳት በሽታ ይከላከላል

-         የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል

-         የደም ውስጥ ስኳር መጠንን ያስተካክላል

-         የሐሞት ጠጠርን ይከላከላል

 

ይህንን መረጃ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ!!

                            

ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦

        የዶክተር ጤና ቴሌግራም ገፅ

                          t.me/DoctorTena

         የዶክተር ጤና ፌስቡክ ገፅ፦

                        fb.com/DoctorTenaEthiopia

 

Report Page