ህገ ወጥ ግንባታን በተመለከተ-አቶ አዲሱ አረጋ

ህገ ወጥ ግንባታን በተመለከተ-አቶ አዲሱ አረጋ


በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ በስፋት እንዳለ ይታወቃል። እነዚህ ህገ ወጥ ግንባታዎች በሌሊት ጭምር በድብቅ የሚፈጸሙ (ጨረቃ ቤቶች) በመሆናቸዉ የከተሞችን ፕላን እና የመሬት ይዞታ አጠቃቀምን የሚቃረኑ ናቸዉ፡፡ በመሆኑም በአንድ በኩል ህገ ወጥ ግንባታን የመከላከል፣ በሌላ በኩል ደሀ ተኮር ፕሮግራሞችን በመዘርጋት ለዜጎች የመኖሪያ ቤት ችግር ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

ዜጎችን መጠለያ የማግኘት እና የትም ቦታ ተዘዋዉረዉ የመኖር መብት አላቸዉ፡፡ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትም ይህን የመኖሪያ ቤት ችግር ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ደሀ ተኮር መመሪያ በማዘጋጀት ለመንግስት ሰራተኞች፣ ለመምህራን ለከተማ ነዋሪዎች፣ ለልማት ተፈናቃይ አርሶ አደር እና አርሶ አደር ልጆች ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ በመቶ ሺህ የሚቆጠር የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታዎችን አዘጋጅቶ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ትላልቅ ከተሞች ለዜጎች በህጋዊ መንገድ አስተላልፏል፡፡ አሁንም እያስተላለፈ ይገኛል፡፡

ይህም ሆኖ ህገ ወጥ ግንባታ ሊቆም ባለመቻሉ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ከተሞች በመሬት አጠቃቀም ዙሪያ ባሉ ህገወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን ማስከበር ስራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ዕርምጃዉ በማንኛዉም ህገ ወጥ ግንባታ ላይ በሁሉም የኦሮሚያ ከፊቼ እስከ ሞያሌ፣ ከደሚ ቢዶሎ እስከ ባቢሌ፣ ከአዳማ እስከ ሻሸመኔ፣ ከአሰላ አስከ መቱ ህገ ወጥ ይዞታዎች እና ግንባታዎችን በመለየት ህብተሰቡን በማወያየት፣ የከተማ መሬትን ለማስተዳደር በወጣዉ ህግና ደምቦች መሰረት ወደ ህጋዊ መስመር መግባት የሚችሉት ህግን ተከትለዉ ወደ ህጋዊ አሰራር እንዲገቡ፣ በተለይም በመንግስት ዞታ እና ማህበራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ የተገነቡት (በትምህርት ቤት፣ ጤና ተቋማት፣ በአረንጓዴ ቦታዎች፣ በፈር ዞኖች የገበያ ቦታዎች መንገድ ሌሎች መሰረተ ልማቶች የሚገነቡባቸዉ ቦታዎች) ማፍረስ ግዴታ መሆኑን በማስረዳት አቅጣጫ ተቀምጦ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡

ሰሞኑን እርምጃ እየተወሰደባቸዉ ካሉ ከተሞች አንዱ በለገጣፎ ለገዳdhii ከተማ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ እና በመደበኛ ሚዲያም ጭምር ህገ ወጥ ግንባታ ላይ እየተወሰደ ያለዉ እርምጃ በለገጣፎ ለገዳdhii ብቻ እየተደረገ ያለ እና ብሄር ለይቶ እርምጃ አስመስሎ እየቀረበ መሆኑን አስተዉለናል ፡፡ ይህ ስህተት ነዉ፡፡ እስካሁን በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 25 ከተሞች በተደረገ እንቅስቃሴም ህግን ብቻ ባማከለ 36,117 ህገ ወጥ ይዞታዎች እና ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን የማስከበር ስራ ተሰርቷል፡፡

በዛሬዉ ዕለትም በለገጣፎ ለገዳdhii ከተማ በመገኘት ከጠቅላይ ሚኒሰትር ጽ/ቤት የፕረስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን፣ የኦሮሚያ ክልል የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሚልኬሳ ሚdhaጋ እንዲሁም ከከተማዋ ከንቲባ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ጋር በመሆን በከተማዉ ያለዉን ተጨባጭ ሁኔታ ተዘዋዉረን ጎብኝተናል፡፡ በቆይታችን በከተማዉ የከፋ ህገወጥ (በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ፣ በአረንጓዴ ቦታዎች፣ በወንዝ ዳር እና ገደላማ ቦታዎች ሳይቀር እንዳለ ለመረዳት ችለናል፡፡ ከተማዋ በህግ ከተቆረቆረች ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ባሉት ጊዜያት 12,381 ህጋዊ ያልሆኑ ቤቶችና ይዞታዎች እንዳሉ ተለይተዋል፡፡ ከዚህ ዉስጥ 1,307 ያህል ቤቶች ህገ ወጥ መሆናቸዉ ተረጋግጦ አምና በተወሰደ እርምጃ እንዲፈርሱ ተደርጓል፡፡ 5,000 በላይ የሚሆኑት ዞታዎች እና ቤቶች ደግሞ በመንግስት ተቋማት፣ በገበያ ቦታዎች፣ በወንዝ ዳር እና ለመንገድ መሰረተ ልማት የማይዉሉ በአጠቃላይ የከተማዉን የመሬት አጠቃቃም ፕላን ጋር ተቃርኖ የሌላቸዉ መሆናቸዉ ስለተረጋገጠ ህግና ደንቦችን ተከትለዉ ወደ ህጋዊ ይዞታነት አንዲዞሩ ተወስኗል፡፡

በለገጣፎ ለገዳdhii ዛሬ ባደረግነዉ ጉብኝት ሰሞኑን በተደረገ ህግን የማስከበር እንቅስቃሴ በመንግስት ይዞታ ስር ባሉ የትምህርት ቤት ቅጥር ገቢ ጨምሮ 347 ቤቶች እና በአጥር የተከለሉ ቦታዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አረጋግጠናል፡፡ የተወሰደዉ ዕርምጃ አንድ ብሄር ላይ ያተኮረ ጥቃት አስመስሎ የማቀረቡም ሁኔታ ሀሰት መሆኑን ሚዲያዎች ባሉበት አረጋግጠናል፡፡

ህገ ወጥ ግንባታ እንደዚህ ሲስፋፋ በየደረጃዉ ያለዉ የአስተዳደር እና ህግ አስከባሪ አካላት ግንባታዉ ሳይከናወን አስቀድመዉ መከላከል አለመቻላቸዉ አንዳንድ ከተሞች ላይም ጉቦ ጭምር በመቀበል ህገወጥነትን በማስፋፋት የተሳተፉ አካላትን ለይቶ ለህግ የማቅረቡ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በዚህ ህገ ወጥ ግንባታ የተሳተፉት አካላት ምንም አማራጭ የሌላቸዉ የደሃ ደሃ የሆኑ ዜጎቻችን ብቻ ሳይሆኑ በተለያዩ ደረጃ በመንግስት ሀላፊነት የሚገኙ አመራሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ የራሳቸዉ ህጋዊ መኖሪያ ያላቸዉ ግለሰቦችና ባለሀብቶች እና የመሬት ደላሎችም ጭምር እተሳተፉበት እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ስለሆነም የደሃ ደሃ የሆኑ ዜጎቻችንን በመጠለያ ዕጦት መንገድ ላይ እንዳይወድቁ ጥናት በመለየት ህግና ሥርዓትን ተከትሎ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ይሰራል፡፡ ከዚህ በተረፈ በመሬት ዙሪያ የሚሰሩ ህገ ወጥነት ላይ ችግሮቹን ከምንቻቸዉ ቀድሞ የመከላለከል ስራ መሰራት አለበት፡፡ ከዚህ በተረፈ መንግስት ህገ ወጥነትን ለመከላከል የሚሰራዉን ያህል የዜጎች በየትኛዉም አካባቢ ተንቀሳቅሶ መስራትና የመኖር ህገ ምግሳተዊ መብት ያለምንም አድልኦ እንዲከበር ይሰራል፡፡ በዚህ ረገድ የሚታይ ማንኛዉንም መዛነፍ ሲታይ በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስረተን የእርምት እርምጃ በመዉሰድ የሚያስተካክል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ ከዚህ በተረፈ ህገ ወጥ ግንባታዎች በቸልተኝነት የሚያዩ እና ብሎም በሌብነት የሚሳተፉ የአስተዳደር አካላት፣ ደላሎች እንዲሁም በህገጥነት ግንባታ ላይ በሚሳተፍ ማንኛዉም ዜጋ ላይ ህግ የማስከበር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

#Addisu_Arega_Kitessa

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page