ሃሌሉያ - Illasha Fekadu

ሃሌሉያ - Illasha Fekadu

Illasha Fekadu - ሃሌሉያ / Hallelujah


ለክፋት የሆነው አለፈኝ

ለመልካም ልሆን ዘገየሁ

ከእኔ ይልቅ አወቅህልኝ

ካላየሁት ክፉ ተጠበቅሁ


ለምስጋና ተረፍሁ ለሃሌሉያ

ልትመሰገንብኝ ወሰንክልኝና

የተጠመደልኝ ሳይዘኝ አመለጥሁ

እንደ ምህረትህ ከጥፋቶቼ ዳንሁ


ሃሌሉያ /ብዙ ጊዜ


ያማረኝን ሁሉ ከመያዝ እጆቼ

በአንተ ተከለከሉ

ያፈቀርሁትን ወጥመድ ሳይገባኝ ሰበርህ

እያለቀስሁ አመለጥሁ


ለምስጋና ተረፍሁ ለሃሌሉያ

ልትመሰገንብኝ ወሰንክልኝና

የተጠመደልኝ ሳይዘኝ አመለጥሁ

እንደ ምህረትህ ኦ ...


ሃሌሉያ /ብዙ ጊዜ


የታሠርሁበትን ሰንሠለት በጠስህ

የትናንት አመፃዬን ታገስህ

ምን እላለው?!

አንደበት ደካማ ነው

እንዲያው ተመስገን!


ሃሌሉያ ...

Report Page