WHO

WHO

Greatful-Ethiopia

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል አገሮች የሚሰጡት ደካማ ምላሽ ከፍተኛ መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል የዓለም ጤና ድርጅት ቅዳሜ ዕለት አስጠንቅቋል።


የድርጅቱ ኮሚቴ ከስድስት ወር በፊት በሽታውን የዓለም ወረርሽኝ ብሎ ከፈረጀ ወዲህ ባካሄደው ግምገማ ላይ በሰጠው መግለጫ፣ በተለይ ቫይረሱ በአገሮች ላይ በሚያደርሰው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጫና የተነሣ “የሚሰጠው ምላሽ ደካማነት” የከፋ መዘዝ ሊያመጣ ይችላል ብሏል።

ኮሚቴው ዓርብ ዕለት ያካሄደው ስብሰባ ወረርሽኙ ተከስቶ ዓለም አቀፍነቱ ከታወጀ እ.አ.አ ጥር 2020 ወዲህ አራተኛው ነው።

“የዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 ያለው አደጋ በጣም ከፍተኛ ነው ማለቱንም” መግለጫው አመልክቷል።

“ወረርሽኙ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል በሽታውን ለመከላከል በዓለም አቀፍ ደረጃ ማኅበረሰቡ ዘላቂ የሆነ ጥረት ማድረግ እንደሚገባም” መግለጫው ጠቁሟል።

ኮሚቴው አገራት የተረጋገጡ የኮቪድ-19 መከላከለያ መድኃኒቶች እና ክትባቶች ማዘጋጀት እንዲችሉ የዓለም ጤና ድርጅት እገዛ እንዲያደርግ አሳስቧል።  

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ወደ ስብሰባው ሲገቡ የወረርሽኙ ተፅዕኖ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ የሚችል ነው ማለታቸው ተዘግቧል።

በምዕተ ዓመት አንዴ የሚከሰት ይህን መሰል ወረርሽኝ ተፅዕኖ በሚቀጥሉት #አሥርት_ዓመታት ውስጥ የሚዘልቅ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 ከ680 ሺህ በላይ ሰዎችን ሕይወት የነጠቀ ሲሆን፣ ከ18 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ በበሽታው መያዛቸውን እስራኤል ናሽናል ኒውስ ዘግቧል።

ምንጭ #EBC 

@GreatfulEthiopia

Report Page