used 2

used 2

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ

የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የ2012 በጀት ዓመት

የተለያዩ የሕፃናት እና የአዋቂ አልባሳቶችን፣
የቤት ዕቃዎችን፣ጫማዎች፣
ቀበቶዎች፣
የእጅ ቦርሳዎች፣
አሻንጉሊቶች፣
የሴት የእጅ ቦርሳዎች እና ሌሎች ያልተጠቀሱ የዕቃ ዝርዝር ጨምሮ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፡-

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፣ቲን ነምበር ያላቸው ተጫራቾች ጨረታው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን የእያንዳንዱ ዕቃ ዝርዝር እና ጥቅል ዋጋ ድምር ሰነድ መሙላት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ተደምሮ ከፍተኛ ዋጋ ያስገባ ተጫራች አሸናፊ የሚሆን ይሆናል። የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ሽያጭ ግምት 1.5 ፐርሰንት 7,910.27( ሰባት ሺ ዘጠኝ መቶ አስር ብር ከ27/100) /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። አድራሻችን ሳሪስ ኢካፍኮ አጠገብ በሚገኘው 3ኛ ፎቅ የፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በ50.00 ( ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የመክፈቻው ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለ ተጨማሪ መረጃ፡- ን/ ስ/ ላ/ ክ/ ከተማ ሳሪስ ኢካፍኮ 100 ሜትር ገባ ብሱ የወረዳ 10 አስተዳደር ሕንፃ ፋ/ ኢ/ ል/ ጽ/ ቤት 3 ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 15

ስልክ ቁጥር፡- 01188832-26

የን/ ስ/ ላ/ ክ/ ከተማ የወረዳ 10 ፋይናንስ ቢሮ



Posted: አዲስ ዘመን ግንቦት 30 ቀን 2012

Deadline: June 19, 2020


© walia tender

Report Page