usd har ዳሸን ባንክ

usd har ዳሸን ባንክ


ዳሸን ባንክ ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ የባንኩ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም 

  1.  ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ ለተሽከርካሪው 20%/ ሀያ በመቶ/ እንዲሁም ለሞተር ብስክሌት ብር 5,000 (ብር አምስት ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታው ዕለት ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡ 
  2. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀናት ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም፡፡ 
  3. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  4. አሸናፊ ተጫራቾች በአሸነፉበት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፈላል፡፡ 
  5. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎች ያሉበትን ሁኔታ ሳሪስ ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ሕንፃ ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 19 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ 2፡00 እስከ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ብቻ መመልከት ይቻላል፡፡ 
  6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ. ም. ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን ፤ ቦታውም ልደታ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የዳሸን ባንክ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ ይሆናል፡፡ 
  7. በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን ሲፒኦ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
  8. የጨረታው አሸናፊ የተሽከርካሪዎችን ስም ለማዘዋወር የሚያስፈልግ ማንኛዉንም ወጪ ይሸፍናል፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-518-03-51 ወይም 0911-37-18-78መደወልይቻላል፡፡ 

ሁልጊዜም አንድ እርምጃ ቀዳሚ! 

__________________

Posted:ሪፖርተር መስከረም 24፣2013

Deadline:19 ተከታታይ የስራ ቀናት

__________________
© walia tender

Report Page